- እሺ እስኪ ስለገጠመህ ሁኔታ አጫውተኝ?
- ሁኔታ አሉት ክቡር ሚኒስትር?
- ያው ሙከራ እንጂ አላገቱህም ብዬ እኮ ነው?
- ዕድለኛ ሆኜ ለቀቁኝ እንጂ መታገቱንማ ታግቻለሁ።
- እኮ… እንዴት እንደለቀቁህ እንድታጫውተኝ እኮ ብዬ ነው ያስጠራሁህ።
- ነግ በእኔ ብለው ነው?
- ነግ በእኔ ማለት?
- ነገ እኔንም ቢያግቱኝ ብለው ልምድ ሊካፈሉ ከሆነ ማለቴ ነው።
- አዎ፣ እኔን በቀጥታ ማገት ባይችሉ እንኳ በተዘዋዋሪ የሚያደርጉት አይታወቅምና ልምድ መካፈሉ ይበጃል።
- ቢሆንም እኔ በዕድል ስለሆነ የተረፍኩት፣ እንደ ልምድ የማካፍለው ወይም የሚጠቅም አልመሰለኝም።
- በዕድል ነው የተረፍኩት ስትል ምን ማለትህ ነው? እንዴት ተረፍክ?
- እንድከታተል ያዘዙኝን የፕሮጀክት ሥራ አጠናቅቄ እየተመለስኩ አንድ አነስተኛ ከተማ ከመድረሴ በፊት እንድቆም አዘዙኝ።
- እሺ…?
- ያስቆሙኝ ታጣቂዎች በመሆናቸው ዕገታ ሊሆን እንደሚችል ጠርጥሬ ሳልደናገጥ፣ የእነሱው ሰው መሆኔን መግለጽ እንዳለብኝ ከራሴ ተማክሬ ወረድኩ።
- እሺ…?
- ያው በአያቴ በኩል ብሔራችን አንድ ነው ብዬ በቋንቋቸው አካ* አልኳቸው።
- እሺ…
- ከት ብለው ሳቁብኝ።
- ለምን?
- መጀመሪያ አልገባኝም ነበር።
- በኋላስ ምን ገባህ?
- ከመካከላቸው አንደኛው እየሳቀ ሞልተናል ሲለኝ ገባኝ።
- ምንድነው የገባህ? ምን ማለቱ ነው?
- የእናንተው ነኝ ማለትህ ከሆነ ሞልተናል እያለኝ ነው።
- እህ… ከዚያስ?
- ከዚያማ እንዳልተሳካልኝና አደጋ ውስጥ እንደሆንኩ ገመትኩኝ።
- ከዚያ ምን ተፈጠረ?
- ይዘውኝ ወደ ጫካ ውስጥ ወሰዱኝና ምንም እንዳልሠጋ መክረውኝ መታገቴን አረዱኝ።
- እሺ… አልተጨነክም?
- ለምን እንደሆነ አላውቅም፣ ምናልባት በእነሱ በኩል የመጫወት ዓይነት አዝማሚያ በማየቴ ነው መሰል ብዙም ፍርኃት አልተሰማኝም ነበር፡፡
- እሺ በኋላ ምን ተፈጠረ?
- ያው በመጀመሪያ መታገቴን አሳወቁኝ።
- እሺ ቀጥሎስ?
- ቀጥሎ ደግሞ የሚጠበቅብኝን እስካሟላ ድረስ ከእነሱ ጋር እንደምቆይ ነገሩኝ።
- ምን ማለታቸው ነው፡፡
- ያው ከዕገታው የምትለቀቀው የምንጠይቅህን ስታሟላ ነው ማለታቸው ነዋ።
- ማሟላት የሚጠበቅብህ ምንድነው?
- ገንዘብ መክፈል ነዋ?
- ምን ያህል እንድትከፍል ጠየቁህ?
- አንተ አማካሪ ስለሆንክ ብዙ ታወጣለህ አሉኝ።
- እሺ… ስንት አሉ?
- ሁለት ነጥብ አምስት አሉኝ?
- ሁለት ነጥብ አምስት ምን?
- ሚሊዮን፡፡
- እንዴ ከየት ታመጣለህ?
- ለዚያ ነው እኔም ሳቅ ያመለጠኝ።
- እየሰሙህ ሳቅህ?
- ሳቅ ብቻ አይደለም።
- እ… ምን አልካቸው?
- ለገበታ ለአገር ነው ወይ አልኳቸው።
- ምን? አንተ ለሕይወትህ አትፈራም እንዴ?
- ሳላውቀው ነው ያመለጠኝ።
- እና ምን አደረጉህ? ቀጠቀጡህ?
- ኧረ በጭራሽ?
- እና ምን ተፈጠረ?
- በዚህ ምክንያት ነው የለቀቁኝ?
- እንዴት?
- ይኼ አማካሪ አይደለም ብለው።
- እና ምንድነህ ነው አሉህ?
- አጋር፡፡
- የምን አጋር?
- የትግሉ።
- ይኼ ቀልድ ነው።
- ቀልድ አይደለም።
- እና ምንድነው?
- ዕድል ነው!
- Advertisment -
- Advertisment -