ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ የሰላም ልዑክ አባላትን ይዘው መቐለ ከተማ በደረሱበት ወቅት፣ የትግራይ የሃይማኖት አባቶችና ካህናት በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ አለመገኘታቸውን ተከትሎ የተናገሩት፡፡ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ በተቀበሏቸው ጊዜ ባደረጉት ውይይት የክልሉ ብፁዓን አበው ለምን እንዳልተገኙ አለመገለጹን አውስተው፣ ለሰላም ጥረት ማድረጉ አስፈላጊነቱን አመልክተዋል፡፡