Saturday, September 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናግንባር ወይም ቅንጅት ለመፍጠር እንዲያግዝ የተመሠረተውን ትብብር ሌሎች ሁለት ፓርቲዎች ተቀላቀሉት

ግንባር ወይም ቅንጅት ለመፍጠር እንዲያግዝ የተመሠረተውን ትብብር ሌሎች ሁለት ፓርቲዎች ተቀላቀሉት

ቀን:

  • ፓርቲዎች አገራዊ ውይይት እንዲጀመር ለመንግሥት ደብዳቤ አስገቡ

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተመዝግበው በሕጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ሦስት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ወደ ግንባር ወይም ቅንጅት ለማደግ ያስቸለናል በማለት የመሠረቱትን የትብብር ስምምነት፣ ሁለት ተጨማሪ ፓርቲዎች ተቀላቅለውት አምስት አደረሱት፡፡

በጋራ ለመሥራት ትብብር ከመሠረቱት ከኢሕአፓ፣ ከመኢአድና ከእናት ፓቲዎች ጋር ‹‹ኢትዮጵያን ማስቀጠል ይችላል›› ያሉትን ትብብር የተቀላቀሉት ፓርቲዎች፣ የአማራ ግዮናዊ ንቅናቄና አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ናቸው፡፡

አምስቱ ፓርቲዎች የህልውና አደጋ ውስጥ ገብታለች ያሏትን ኢትዮጵያ ችግሯን የሚፈታ ሁሉን አቀፍ ውይይት በገለልተኛ ወዳድ አፍሪካዊት አገር መዲና እንዲካሄድ፣ ከቀናት በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በመግለጫው ወቅት ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ለቀው የወጡ አመራሮችና አባላት ተሳትፈዋል፡፡

‹‹አገርን መታደግ የተሰኘ ውይይት›› መሣሪያ ያነገቱና ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የሚያደርጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሳተፉበት ውይይት እንዲደረግ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር)፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ፣ ለፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ  ዘውዴና ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ደብዳቤ ማስገባታቸውን የፓርቲዎቹ አመራሮች አስታውቀዋል፡፡ ፓርቲዎቹ መንግሥትም ሆነ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጥሪውን ተቀብለው ተግባራዊ ዕርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል፡፡

የታሰበው አገራዊ ውይይት የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ችግሩን በአስቸኳይ ሊፈታው ስለማይችል፣ ‹‹መንግሥት አገር ከመፍረሷ በፊት ውይይት በማድረግ መፍትሔ ሊያበጅ ይገባል፤›› ብለዋል፡፡

በመግለጫው ላይ የተገኙት የኢዜማ የቀድሞ አመራር አቶ የሸዋስ አሰፋ፣ በቀጣይ ከፓርቲዎቹ ጋር የመቀላቀል ወይም በአዲስ ድርጅት የመምጣት ዕቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

‹‹በዴሞክራሲ አቋራጭ መንገድ የለም፤›› ያሉት አቶ የሽዋስ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሐሳብ የሚነጋገሩበት አገራዊ ውይይት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡  አክለውም ኢትዮጵያ ውስጥ የጠንካራ ሰው ታሪክ እንጂ የጠንካራ ተቋም ታሪክና አገዛዙ ሲሳሳት ቆም ብሎ የሚያስቆም ተቋም ባለመኖሩ፣ አሁን ያለው አማራጭ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያደርጉት ምክክር ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የምክክር ኮሚሽኑ በቀጣይ አንድ ዓመት ወይም በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት ዓላማውን ያሳካል ቢባል እንኳ፣ ዜጎች በከፍተኛ ሥጋትና የሞት ጥላ ሥር ነው ያሉት ደግሞ የእናት ፓርቲ ፕሬዚዳንት ሰይፈ ሥላሴ አያሌው (ዶ/ር) ናቸው፡፡

‹‹አገር ዓይናችን እያየ ልትፈርስና የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ልንገባ የምንችልበት አደጋ ተጋርጦብናል፤›› ያሉት ሠይፈ ሥላሴ (ዶ/ር)፣ ‹‹ይሁን እንጂ የለም በሚል ብቻ ተሸፍኖ ስላለፈና ሟርት ብለን ስለጠራነው ችግሩ አይቀሬ ስለሆነ አደጋውን ልናየው ይገባል፤›› ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...