የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አብዱልቃድር ገልገሎ (ዶ/ር)፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም. በተከናወነው የችግኝ ተከላ ላይ ከተለያዩ ጤና ተኮር መንግሥታዊና ሌሎች ተቋማት ለተውጣጡ ሠራተኞችች የተናገሩት፡፡ ነገን ዛሬ እንትከል በሚል መሪ ቃል በተከናወነው የችግኝ ተከላ፣ ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘው እንደተናገሩት፣ ዕፅዋት ምግብና መድኃኒት ውበትም ናቸው፡፡ ስለሆነም እኛ የጤናው ዘርፍ ሠራተኞች ደግሞ ለዚህ አገራዊ ተልዕኮ ግንባር ቀደም ሆነን መገኘት አለብን ብለዋል።
አያይዘውም ሁሉም በጋራ የሚኖኖርባትን መሬት መንከባከብ እንደሚገባ፣ ተክሎ ብቻ መሄድ ሳይሆን ለፍሬ እንዲበቁ ለማድረግ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡