Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) ከዩክሬን ፕሬዚዳንት የጉብኝት ጥሪ ቀረበላቸው

ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) ከዩክሬን ፕሬዚዳንት የጉብኝት ጥሪ ቀረበላቸው

ቀን:

ከሩሲያ ጋር ከባድ ጦርነት ውስጥ የምትገኘው የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘሌንስኪ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የጉብኝት ጥሪ አቀረቡ፡፡

ሁለቱ መሪዎች ሰኔ 13 ቀን 2015 ዓ.ም ጦርነቱ ከተጀመረ ለመጀመሪያ ጊዜ ባደረጉት የስልክ ውይይት በሁለትዮሽ፣ በዓለም አቀፍ የጋራ ጉዳዮች፣ እንዲሁም በዩክሬንና በሩሲያ መካከል የሚካሄደው ጦርነት መፍትሔ ላይ መወያየታቸውን የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቢሮ በድረ ገጹ ያወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ‹‹የጥቁር ባህር (Black Sea) የእህል አቅርቦት›› እየተባለ በሚታወቀው ስምምነት መሠረት 300 ሺሕ ቶን፣ እንዲሁም በዩክሬን የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ስምምነት መነሻ መሠረት ደግሞ 90 ሺሕ ቶን ስንዴ ለኢትዮጵያ ማቅረቧን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በነበራቸው የስልክ ውይይት ማስረዳታቸው በመግለጫው ተካቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) በትዊተር ገጻቸው ባሠፈሩት አጭር ጽሑፍ፣ ከፕሬዚዳንቱ ጋር ባደረጉት የስልክ ንግግር የሁለትዮሽና የጋራ ጉዳይ በሆኑ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች፣ እንዲሁም ዩክሬን ከሩሲያ ጋር የገባችበት ጦርነት በሰላም እንዲቋጩ መነጋገራቸውን ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዩክሬን ፕሬዚዳንት ጋር ስለነበራቸው የስልክ ውይይት ዘርዘር ያለ መግለጫ ግን አልሰጡም፡፡

ፕሬዚዳንት ዜሌኒስኪ ዩክሬን ከኢትዮጵያ ጋር በዲጂታል ቴክኖሎጂና በደኅንነት ጉዳዮች ተባብራ መሥራት እንደምትፈልግ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መነጋገራቸው በፕሬዚዳንቱ ቢሮ መግለጫ የተጠቀሰ ሲሆን፣ ዩክሬን የዓለም የምግብ አቅርቦት በበቂ ሁኔታ እንዲንቀሳቀስ ትሠራለች ማለታቸው ተዘግቧል፡፡

በፕሬዚዳንቱ ቢሮ ድረ ገጽ እንደተመላከተው ሁለቱ መሪዎች በስልክ ውይይታቸው፣ የአፍሪካ አገሮችን ከዩክሬን ጋር የሚያገናኙ የውይይት መድረኮች መፈጠር እንዳለባቸውም አጽንኦት ተሰጥቷል፡፡

‹‹የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ አኅጉር ድምፅ ለዩክሬን በጣም ወሳኝ ነው፤›› ማለታቸው በመግለጫው የተነገረላቸው ፕሬዚዳንቱ፣ ሩሲያ የጥቁር ባህር ስምምነት እየተባለ ከሚታወቀው የእህል አቅርቦት ጥላ መውጣቷን ወቅሰዋል ተብሏል፡፡

ሁለቱ መሪዎች የዓለም የሰላም ኮንፈረንስን በተመለከተም ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2022 ሩሲያና ዩክሬን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ቱርክ ጋር በመሆን በጥቁር ባህር በኩል ደኅንነቱ የተጠበቀ መተላለፊያ ለመክፈት በመስማማታቸው፣ እህል ለተለያዩ አገሮች እየተላከ እንደነበር ይታወሳል።

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዩክሬን ባለፈው ዓመት ያመረተችው ጠቅላላ እህል 55 ሚሊዮን ቶን ብቻ መሆኑን፣ ከዚህ ውስጥ 47 ሚሊዮን ቶን የሚሆነውን ኤክስፖርት ማድረጓንና የስንዴ ድርሻ 17 ሚሊዮን ቶን ብቻ እንደሆነ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ ሩሲያ ግን 156 ሚሊዮን ቶን እህል አምርታ 60 ሚሊዮን ቶን ኤክስፖርት ስታደርግ፣ 48 ሚሊዮን ቶን ስንዴ እንደሆነ አክለዋል፡፡ የሩሲያ ድርሻ በዓለም የስንዴ ገበያ 20 በመቶ መሆኑን፣ የዩክሬን ደግሞ ከአምስት በመቶ እንደማይበልጥ ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...