እንካ ሰላንቲያ
በአጥቢያ!
ምን አለህ በአጥቢያ ?
ስንት ቤት ተናግቷል ባጉል ድግስ ሳቢያ።
በድር!
ምን አለህ በድር?
ሕይወትን ያዛባል ያልታቀደ ብድር።
በአጠበ!
ምን አለህ በአጠበ?
ስለ ነገ አይሰጋም ዛሬ የቆጠበ፡፡
በቅንጦት!
ምን አለህ በቅንጦት?
የቆጠቧት ሳንቲም ታድናላች ከእጦት።
ተግተህ የቆጠብካት ሣንቲም ጠብታ
ያመሻሽ መድን ናት የታኅሣሥ ገበታ።
በሁነኛ
ምን አለ በሁነኛ?
ተግቶ የቆጠበ አይሆንም ጥገኛ።
በሰበብ!
ምንአለህ በሰበብ?
መሰሰት አይደለም የመቆጠብ ጥበብ።
በአጣ!
ምንአለህ በአጣ?
ከቶ መቼም ቢሆን ያለ አቅድ አታውጣ።
ኃይለመለኮት መዋዕል ‹‹እንካ ሰላንቲያ››
******
- Advertisement -
- Advertisement -