Wednesday, October 4, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ዓለም ባንክ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ገበያ ትስስር ድጋፍ ሊያደርግ መሆኑ ተገለጸ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች የሥራ ዕድል ፈጠራና የገበያ ትስስር እንዲኖራቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል መግባቱን የኢንዱስትሪያል ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የጽሕፈት ቤትና የትራንስፎርሜሽን ኃላፊ አቶ ፍፁም ከተማ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በዓለም ባንክ ድጋፍ የተገነባው የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ምዕራፍ ሁለት ፕሮጀክት መጠናቀቁንም ገልጿል፡፡ በቅርቡ ለልማት የገቡ ድርጅቶች እየሠሩት ያሉትን ሥራዎችና ዘርፉ የፈጠረውን የሥራ ዕድል የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት አጃይ ባንጋ በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ እንደሚገኙና ትናንት ሐምሌ 25 ቀን 2015 ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ጉብኝት ይገኝበታል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ‹‹ከዓለም ባንክ ጋር ያለው ግንኙነት መሠረተ ልማት ግንባታ ላይ ያተኮረ ብቻ አይደለም›› ያሉት አቶ ፍፁም፣ ቴክኒካል እገዛ ከማድረግ በተጨማሪ ዘለቄታዊ የልማት ሥራዎችም ላይ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በጉብኝታቸው የተነሱት ዋና ሐሳቦችም በፓርኮቹ የሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎችና የገበያ ትስስር ላይ ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ በየደረጃው ክትትል እንደሚያደርጉ ፕሬዚዳንቱ ቃል መግባታቸውን ጠቁመዋል፡፡

የጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎችን የጎበኙት ፕሬዚዳንቱ፣ ወደ ፊት በሚገነቡ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች ለማልማት በዘላቂነት ድጋፍ ለማድረግ ዕቅድ እንዳላቸው መግለጻቸውን ተናግረዋል፡፡

የባንኩ ፕሬዚዳንት የሥራ ዕድል ፈጠራው 90 በመቶ የሚሆነው ለሴቶች መሆኑን አድንቀው፣ ባንኩ ትኩረት ሰጥቶ የሚደግፍ መሆኑን መናገራቸውን አቶ ፍፁም አስረድተዋል፡፡

በዋናነት ድጋፍ ለማድረግ ቃል የገቡት ዘርፎች በዝርዝር ባይገለጽም፣ ይሁን እንጂ በአጠቃላይ ፓርኮች ልማት ላይ ድጋፍ እንደሚያደርጉ መግለጻቸውን ተነግሯል፡፡

የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ምዕራፍ ሁለት ዓለም ባንክና ገንዘብ ሚኒስቴር ባደረጉት ስምምነት መሠረት ፈንድ ተደርጎ የተገነባ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ማሳደግ ረገድ ትልቅ ሚና እንዳላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች