Sunday, June 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየግልና የመንግሥት የድኅረ ምረቃ መግቢያ አፈታተን ሥርዓት ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ

የግልና የመንግሥት የድኅረ ምረቃ መግቢያ አፈታተን ሥርዓት ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ

ቀን:

  • የመጪው ትምህርት ዘመን ፈተና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል

የግልና የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በየግላቸው ይሰጧቸው የነበረውን የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና፣ በተመሳሳይ ሥርዓትና ማዕከላዊ በሆነ መንገድ እንዲሆን የትምህርት ሚኒስቴር ወሰነ፡፡

ለዚህም ተቋማቱ በ2016 የትምህርት ዘመን ለማስተማር የመዘገቧቸውን የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተናዎቻቸው (Graduate Admission Test)፣ ለተቀራራቢና ተመሳሳይ ፕሮግራሞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፈተና ማዕከል እንዲሰጥ ተወስኗል፡፡

በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ተፈርሞ ሐምሌ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተጻፈውና ሪፖርተር የተመለከተው ደብዳቤ፣ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች አቀባበል ላይ ‹‹ተቀራራቢ ሥርዓት መከተል›› እንደሚያስፈልግ በማስፈር የተደረጉ ለውጦችን ይገልጻል፡፡

- Advertisement -

የትምህርት ሚኒስቴር አደረግኩት ባለው ክትትል፣ ድኅረ ምረቃ ለመማር ያመለከቱ ተማሪዎችን የመመዘኛ ፈተና ሳይሰጡ የሚመዘግቡ የመንግሥትና የግል ተቋማትን እንዳገኘ በደብዳቤው አስፍሯል።

የትምህርት ተቋማቱ የድኅረ ምረቃ መርሐ ግብሮችን ሲከፍቱ የሚታየውን ክፍተት ለማስተካከል የሚወሰዱ ዕርምጃዎች እንዳሉ ሁሉ፣ እንዲሁም ተማሪዎችን መዝኖ በሚኖረው የአቀባበል ሥርዓት ላይ ‹‹እንደ አገር የመግቢያ ፈተናን መስጠትም አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል፤›› ይላል ደብዳቤው፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል ለተቀራራቢና ተመሳሳይ ፕሮግራሞች የሚሰጠው የመግቢያ ፈተና፣ ከመስከረም 20 እስከ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. እንዲሰጥ ተወስኗል፡፡

በውሳኔው መሠረት ለቀጣይ ትምህርት ዘመን ተቋማቶቹ በድኅረ ምረቃ የሚቀበሉባቸውን መርሐ ግብሮች ዝርዝር እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ለትምህርት ሚኒስቴር እንዲያሳውቁ ታዘዋል፡፡

በማስቀጠልም የመንግሥትም ሆኑ የግል ተቋማቶቹ በተፈቀደላቸውና ለትምህርት ሚኒስቴር ባስገቧቸው የድኅረ ምረቃ መርሐ ግብሮች፣ ለትምህርት ፈላጊ ተማሪዎች ማስታወቂያ በማውጣት መዝግበው፣ የተመዘገቡትን ዕጩ ተማሪዎች ዝርዝር እስከ መስከረም 10 ቀን 2016 ዓ.ም. ለትምህርት ሚኒስቴር እንዲያሳውቁ ሲል ደብዳቤው ያዛል፡፡

በተለይ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዓመት ሁለት ጊዜ የድኅረ ምረቃ ትምህርት ምዝገባ የሚያካሂዱና የትምህርት ዘመናቸውም በመስከረምና በጥር ወራት በሁለት ወቅት የሚጀምሩ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በደብዳቤው መሠረት የትምህርት ሚኒስቴር በጥር ወር ስለሚደረጉት ምዝገባዎች ዕቅድ አላወጣም፡፡

የግል ከፍተኛ ትምርት ተቋማት ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተገኝ አለሜ ትዕዛዙ በደብዳቤ እንደደረሳቸው፣ እንዲሁም ማኅበራቸው በትናንትናው ዕለት ውይይት አድርጎ የፈተናውን ማዕከላዊ መሆን ቢደግፍም በተወሰኑ ውሳኔዎች ላይ ቅሬታ እንዳለው ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

‹‹ፈተናው በዓመት አንድ ጊዜ ከሚሆን ቢያንስ ሁለት ጊዜ ቢሆን መማር ለሚፈልጉት ዓመት ሙሉ ከሚጠብቁ ቶሎ ዕድል ይፈጥራል፤›› ያሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ማኅበራቸው በፈተናው አገር አቀፍ መሆን ቢያምንምና በጽንሰ ሐሳቡ ላይ ልዩነት ባይኖርበትም፣ በአሠራሩ ላይ ያለውን ልዩነት ለሚኒስቴሩ በደብዳቤ ሊያሳውቅ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ ሌላ ቅሬታ ሊያቀርቡበት የሚችሉት ጉዳይ ፈተናውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል እንዲዘጋጅ መወሰኑን እንደሆነ ገልጸው፣ በሌሎች ክልሎች በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችም መሰጠት እንዳለበት ተናግርዋል፡፡

በተላለፈው ውሳኔ ላይ ማኅበሩ ያለውን ቅሬታና ድጋፍ በደብዳቤ በማሳወቅ ውይይት እንዲደረግበት ትምህርት ሚኒስቴር እንደሚጠየቅ ዋና ሥራ አስኪያጁ አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...