Saturday, September 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየሽብር ወንጀል ክስ በተመሠረተባቸው ጋዜጠኞችና ግለሰቦች ላይ ለቀጣይ ዓመት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ

የሽብር ወንጀል ክስ በተመሠረተባቸው ጋዜጠኞችና ግለሰቦች ላይ ለቀጣይ ዓመት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ

ቀን:

የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን ጨምሮ በእነ ወንደወሰን አሰፋ (ዶ/ር) መዝገብ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦች፣ የ‹‹ዳኛ ይቀየርልን›› ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ፣ ለቀጣይ ዓመት ለጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ሕገ መንግሥትና የፀረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ትናንት ማክሰኞ ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. በፖሊስ በቁጥጥር ሥር ያልዋሉና የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎችን ይዞ ለማቅረብ ተጨማሪ ጊዜ የተጠየቀ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ለጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ይዞ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ፖሊስ የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎች ይኖሩበታል ተብሎ በተገለጸው አድራሻቸው ካልተገኙ፣ ከአካባቢው አስተዳደር ተጠርጣሪዎቹ በተጠቀሰው አካባቢ የማይኖሩ መሆኑ ተጠቅሶ ማስረጃ እንዲያቀርብ ችሎቱ አዟል፡፡

የሽብር ወንጀል ክስ ከተመሠረተባቸው 51 ተጠርጣሪዎች መካከል 23ቱ በቁጥጥር ሥር ውለውና ማረሚያ ቤት ሆነው ክሳቸውን እየተከታተሉ ሲሆን፣ 28ቱ ደግሞ በሌሉበት ጉዳያቸው እየታየ ነው፡፡

ተከሳሾቹ ለችሎቱ በጽሑፍ ባቀረቡት ማመልከቻ የችሎቱ ሰብሳቢ ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ በጋራ ‹‹ተስማምተንበታል›› ያሉትን ጽሑፍ ለማንበብና እንያንዳንዳቸው ተከሳሾች የመሀል ዳኛውን በተመለከተ በቃል ለማስረዳት እንዲፈቀድላቸው ያቀረቡትን ጥያቄ ችሎቱ ውድቅ አድርጎታል፡፡

ተከሳሾቹ በመሀል ዳኛው ላይ ያቀረቡት የ‹‹ይነሱልን›› ጥያቄ ሰነድ እንደሚያሳየው ‹‹ዳኛው እንዲነሱ የጠየቅንበት ምክንያት ዳኛው በግላቸው የፌስቡክ አካውንት በሚያጋሩት ‹አማራ የሚባል ብሔር የለም› የሚል የአማራን ሕዝብ ህልውና የሚክድ የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ ጽሑፎችና የአማራ ሕዝብ ከሌሎች ወንድም ሕዝቦች ጋር በጥላቻ እንዲተያይና ግጭት ውስጥ እንዲገባ የሚያደርጉ ቀስቃሽ ጽሑፎችን በማቅረባቸው ነው፤›› ብለዋል፡፡

በሰባት ጠበቆች የተወከሉት ተከሳሾች ባነሱት አቤቱታ፣ የመሃል ዳኘው በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ትርክት አራማጅ መሆናቸውንለችሎቱ ተናግረዋል፡፡

ከማለዳው አራት ሰዓት አካባቢ በተጀመረው ችሎት ጋዜጠኞች ዘግይተው እንዲገቡ የተደረገ ሲሆን፣ የተከሳሾች ቤተሰቦች ለጊዜው እንዳይገቡ ችሎቱ ከልክሎ ነበር፡፡ ክልከላውን የተቃወሙት ተከሳሾች ባቀረቡት አቤቱታ፣ ቤተሰቦቻቸው የችሎቱን ሒደት እንዲከታተሉና ችሎቱ በትልቅ አዳራሽ እንዲደረግ ጠይቀው፣ ችሎቱ ቤተሰብ በሌለበት መጀመሩ አግባብ አለመሆኑን አስረድተዋል፡፡ የተከሳሽ ጠበቆችና ተከሳሾች ሕገ መንግሥታዊ የሆነው መብት በማንኛውም መልኩ መጣስ እንደሌለበትና ቤተሰቦቻቸው ችሎቱን እንዲታደሙ እንዲፈቀድላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡ ይሁን እንጂ የተሰየሙት ዳኞች ከዚህ በፊት የነበረውን ችሎት የሚያውክ ተግባር መፈጸሙን አብራርተው፣ የተከሳሾች ጠበቆች የችሎት ታዳሚዎች ሕግ ሲጥሱ የመከታተል ኃላፊነት እንዳለባቸውም ተናገረዋል፡፡

የተከሳሾች ጠበቆች በበኩላቸው፣ በችሎት ወቅት እየገቡ የችሎቱን ሒደት የሚበጠብጡና ተልዕኮ የሚሰጣቸው አካላት ስለመኖራቸው፣ ከተከሳሽ ወገኖች መረጃ እንደደረሳቸው ተናግረዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን አቤቱታ ሰምቶ ታዳሚ እንዳይገባ የሰጠውን ትዕዛዝ በማንሳት የተከሳሽ ቤተሰቦች እንዲታደሙ ተደርጓል፡፡

ሌላው ፍርድ ቤቱ በዕለቱ የገጸው፣ ተከሳሾቹ በፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አካማይነት፣ ፎቷቸውን ከጦር መሣሪያ ጋር በማድረግ ‹‹ለሽብር ወንጀል ተንቀሳቅሰዋል›› በሚል፣ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፣ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን፣ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽንና ኦሮሚያ ብሮድካስት ኔትወርክ የተላለፈው መግለጫ፣ ከሚዲያ ተቋማቱ ድረገጽ እንዲወርድ የሰጠውን ትዕዛዝ በተቋማቱ ከኦሮሚያ ብሮድካስት ኔትዎርክ ውጭ ሌሎቹ ሚዲዲዎች በማክበር ከድረገጻቸው ላይ እንዲወርድ ማድረጋቸውን ነው፡፡ ከአራቱ ሚዲያዎች ለችሎቱ የተላከው የደብዳቤ ግልባጭም ለተከሳሽ ጠበቆች ተሰጥቷል፡፡

ችሎቱ የተከሳሾቹን የ‹‹ዳኛ ይነሳልን›› ጥያቄ በሚመለከት በቃል ለማቅረብ ያቀረቡትን አቤቱታን ውድቅ አድርጎ፣ ለጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...