አዲሱ የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ኦጃይ ባንጋ፣ በአዲስ አበባ የቦሌ ለሚ 2 ኢንዱስትሪ ፓርክን በጎበኙበት ወቅት የተናገሩት፡፡ በባንኩ ድጋፍ በተገነባው ፓርክ ለወጣቶች በተለይ ለሴቶች ሥራ የሚያስገኙ ፋብሪካዎችን እና ሥራን የሚፈጥሩ የኢንዱስትሪ መንደሮች ዕውን መሆናቸው በጣም ጥሩ ሥራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያን ከጅቡቲ የሚያገናኘውን ፈጣን መንገድ ለመገንባት የሚያስችለውን ገንዘብ በቅርቡ በመፈራረማቸውም ደስተኛ መሆናቸውንም ሳይገልጹ አላለፉም፡፡