Saturday, September 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -

ማስተካከያ

ቀን:

በቀን 11/11/2015 ዓ.ም. ለሚዲያችሁ በሰጠነው የስልክ ቃለ መጠይቅ ላይ ዕርምት እንድታደርጉ መጠየቅን ይመለከታል፡፡

ግልፀኝነት መርሕ ተገቢነትን በመከተል፣ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤታችን ከላይ በተጠቀሰው ቀን በስልክ ለሪፖርተር ሚዲያ መረጃ መስጠቱ ይታወሳል፡፡ ነገር ግን የተሰጠው መረጃና የተዘገበው ዘገባ የሚጣረሱ ስለሆኑ፣ እንደሚከተለው ታርመው እንዲገለጹልን እንጠይቃለን፡፡

በዕለቱ በሰጠነው መረጃ ካርታ እያለን የመኖሪያ ቤት ፈርሶብናል ብለው አቤቱታ ያቀረቡ 64 አቤት ባዮች ጉዳይ እንጂ፣ ከ100,000 በላይ ተብሎ ስለተዘገበው አኃዝ ያነሳነው ነገር ሳይኖር፣ እኛ በዕለቱ መረጃ እንደሰጠን ተደርጎ መዝገቡ፣ ስህተት በመሆኑ እንዲታረም፡፡

ወደ ተቋሙ እየመጡ ያሉ ቅሬታዎች ከተለያዩ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ እንደሆኑ ምላሽ የሰጠን ሲሆን፣ ሚዲያው ግን ሌሎች ጉዳዮችን ወደ ጎን በመተው በሕገወጥ ግንባታ ምክንያት ቤታቸው እየፈረሰባቸው ያሉ አቤት ባዮች ብቻ እንደሆኑ ተደርጎ የተገለጸው ተገቢ ባለመሆኑ እንዲታረም፡፡

የ64 አቤት ባዮችን ጉዳይ አስመልክቶ ለሸገር ከተማ አስተዳደር የተጻፈው ደብዳቤ በሒደት ላይ ያለ በመሆኑ መረጃ ማለት ደግሞ ሙሉና እውነተኛ መሆን ስላለበት በሒደት ላይ የሚገኝ አቤቱታ አንድም መረጃ ተብሎ ሊሰጥ አይችልም፡፡ ሁለትም ፍትሕን ሊያዛባ ስለሚችል ቀድሞ ውጤቱን መተንበይ ጉዳት ካልሆነ፣ ለማንም ጠቀሜታ ስለሌለው፣ የአቤት ባዮችን ዕጣ ፈንታ እንደተነበይን ተደርጎ መዝገቡ ከመረጃ ነፃነት መርሕ ውጭ በመሆኑ የእኛ ሐሳበ ባለመሆኑ እንዲታረም፡፡

አቶ ቶሌራ ገመቹ የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ የአስተዳደር በደል ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተብሎ የተዘገበው አቶ ቶሌራ በላይ በሚለው እንዲታረም፡፡

በአጠቃላይ ሚዲያ የሚያገኘውን መረጃ ሳይቀንስ፣ ሳይጨምር እንደወረደ ለኅብረተሰቡ ማስተላለፍ የሚጠበቅበት ሥነ ምግርባ፣ ተዓማኒነቱን የሚጨምርና ገለልተኝነቱን የሚያረጋግጥበት በመሆኑ ከላይ የተቀመጡ መታረም ያለባቸው ጉዳዮች ታርመው ለኅብረተሰቡ በመተላለፍ እንዲገለጽልን እንጠይቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የኦሮሚያ ጽሕፈት ቤት

ከዝግጅት ክፍሉ፡- ለመገናኛ ብዙኃን መረጃ በመስጠት ተባባሪ ከሆነው የኢትዮጵያ ዕንባ ጠባቂ ተቋም፣ በተጠቀሰው ዕለት እንደ ወትሮው ሁሉ ሪፖርተር በስልክ መረጃ ተቀብሎ፣ ጽሑፉን ሲያዘጋጅ ለተፈጠረው ስህተት ተቋሙንና አንባብያንን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ የተፈጠሩት ስህተቶች ከላይ ከተቋሙ በተገለጸው መልኩ ተስተካክለው እንዲነበቡ እየጠየቅን መረጃ በመሰብሰብ ሒደት ለተፈጠረው የመረጃ መዛባት በድጋሚ ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...