Saturday, June 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊአካል ጉዳተኞች በአገራዊ ምክክር ተሳትፎ እንዲያደርጉ ከስምምነት ተደረሰ

አካል ጉዳተኞች በአገራዊ ምክክር ተሳትፎ እንዲያደርጉ ከስምምነት ተደረሰ

ቀን:

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን በአገሪቱ እየታዩ ላሉ ፖለቲካዊ ችግሮች በዘላቂነት መፍትሔ ይሰጣል ተብሎ በሚጠበቀው አገራዊ ምክክር ላይ፣ ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማድረግ ከኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር ስምምነት አደረገ፡፡

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን፣ ረቡዕ ነሐሴ 10 ቀን 2015 ዓ.ም. ከኮሚሽኑ ጋር ያደረገው የመግባቢያ ስምምነት፣ በቀጣይ በሚደረገው አገራዊ ምክክር አካል ጉዳተኞች ከወረዳ እስከ ክልል በሚኖራቸው ውክልና እንዲሁም በውይይት መድረኮች ተገቢ ቦታ እንዲያገኙ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የፌዴሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዓባይነህ ጉጆ ስምምነቱን አስመልክቶ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ በሚከናወኑ ፖለቲካዊም ሆነ ሌሎች ጉዳዮች የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎ ዝቅ ያለ ነው፡፡

- Advertisement -

በአገሪቱ የሚገኙ አብዛኛው አካል ጉዳተኞች በትምህርት፣ በጤናና በፖለቲካዊ ጉዳዮች፣ በሥራ ዕድል ተደራሽነት፣ በአካባቢያዊ ተደራሽነት፣ በመረጃ እንዲሁም በተለያዩ መሠረታዊ ጉዳዮች ተሳታፊ ባለመሆናቸው ምክንያት ቅሬታ እያቀረቡ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአገሪቱ የሚታየውን የሰላም ሁኔታ እንዲሁም ከሕገ መንግሥት አንፃር ያሉትን ክፍተቶች በመገምገም ለመንግሥት በሚያቀርበው ሐሳብ አካል ጉዳተኞች የሚሳተፉ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

አገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በቀጣይ ለሚያደርገው ውይይት የልየታ ሥራ እያከናወነ መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ ይህንንም ልየታ ሲያደርግ አካል ጉዳተኞችን ማሳተፍ እንደሚኖርበት ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በአካል ጉዳተኞች በኩል ያለውን ቅሬታ ለመፍታትና መፍትሔ ለመስጠት ኮሚሽኑ በቀጣይ ከአካል ጉዳተኞች ጋር በስፋት ተወያይቶ ምክረ ሐሳቡን ለመንግሥት የሚያቀርብ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ውይይቱም መቼና የት እንደሚካሄድ ለማወቅ እንዳልተቻለና በኮሚሽኑም ዕቅድ መሠረት እንደሚከናወን፣ ኮሚሽኑ በአዋጁ መሠረት የተሰጠው ጊዜ ሦስት ዓመት ያህል እንደሆነ፣ እስካሁንም አንድ ዓመት ከስድስት ወራት ያህሉን ሥራ ላይ ማዋሉን አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ኮንቬንሽንን ከ12 ዓመታት በፊት ተቀብላ የፈረመች ሲሆን፣ የአካል ጉዳተኞች የሥራ ሥምሪት አዋጅ፣ የሕንፃ አዋጅ፣ የቀረጥ ነፃ መመርያና አካል ጉዳተኞችን ከ60 በመቶ በላይ የቅጥር ድርጅት ከታክስና ቀረጥ ነፃ መሆን አለበት የሚሉት በአገር ውስጥ መውጣታቸው ይጠቀሳል፡፡

ይሁን እንጂ አካል ጉዳተኝነትን በተመለከተ በጽንሰ ሐሳብ ደረጃ ከባህል፣ ከሃይማኖት፣ ከሕክምና እንዲሁም ከመብትና ከመሳሰሉት ዕይታዎች አንፃር ጉራማይሌ የሆኑ አረዳዶችና አመለካከቶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም አሁን በአካል ጉዳተኞቹ በኩል ትግል እየተደረገባቸው ስለሚገኙ የእኩል ተሳትፎ ጥያቄዎች ሁሉም ሰው የተስተካከለ አመለካከት ይኖረዋል ተብሎ እንደማይገመት ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...