Sunday, June 23, 2024

[ክቡር ሚኒስትሩ እረፍት አደርጋለሁ ብለው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ቢገቡም ባለቤታቸው በፖለቲካ ወሬ ጠምደው ይዘዋቸዋል]

 • ቆይ አንቺ ምን አሳሰበሽ?
 • እንዴት አያሳስበኝም?
 • አንቺን የገጠመሽ ችግር በሌለበት ለምንድነው ስለ አገሪቱ ፖለቲካ የምትጨነቂው?
 • እኔን የገጠመኝ ችግር እንደሌለና እንደማይኖር በምን አወቅህ?
 • ባለቤትሽ የመንግሥት ሰው ሆኖ እንዴት አንችን ችግር ሊገጥምሽ ይችላል?
 • እስኪ አትቀልድ።
 • አልቀለድኩም!
 • እንዴት? አገሪቱ ችግር ውስጥ መሆኗ የእኔ ችግር አይደለም ማለት ነው?
 • እንደዚያ ማለቴ አይደለም።
 • እና ምን እያልክ ነው?
 • በቀጥታ አንቺ ጋር የሚደርስ ችግር አይኖርም ማለቴ ነው።
 • የአገሪቱ ፖለቲካ ከዛሬ ነገ ይሰክናል ብንልም አልሆነም። ሁሉ ነገር ከድጡ ወደ ማጡ እየሄደ እየተመለከትኩ ነገ ችግሩ እኔ ጋር እንደማይደርስ ምን ማረጋገጫ ይኖረኛል?
 • አይ… እንደምትይው የተፈጠረ ነገር የለም።
 • እንዴት? ችግር የለም እያልከኝ ነው?
 • ፈተና አልገጠመንም ወይም ችግር የለም አላልኩም።
 • ምን እያልክ ነው ታዲያ?
 • ፈተና ቢገጥመንም ፈተናዎችን ወደ ዕድል እየቀየርን መጓዛችን ይቀጥላል እያልኩ ነው።
 • ይህን ነገር አንተም መንግሥትም ትሉታላችሁ እንጂ አንዲት ፈተና ወደ ዕድል ተቀይራ አልተመለከትንም።
 • በእኛ በኩል፣ ማለቴ በመንግሥት በኩል ያለው ትልቁ ችግር እሱ ነው።
 • ምኑ?
 • ያጋጠሙንን ፈተናዎችን እንዴት ወደ ዕድል እየቀየርናቸው እንደሆነ የሚያሳይ መረጃ ለሕዝብ እየሰጠን አለመሆኑ በእኛ በኩል የሚስተዋል ትልቅ ክፍተት ነው።
 • እኔ ግን ከግጭት ወደ ግጭት፣ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወደ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስንገባ እንጂ ወደ ዕድል የተቀየረ ነገር አላየሁም።
 • በእኛ በኩል በቂ መረጃ እየቀረበ ባለመሆኑ አንቺም ሆንሽ ሌላው ማኅበረሰብ ዕድሎቹን ለማየት እንደተቸገረ ይታወቃል።
 • እናንተ መረጃ ካልሰጣችሁ የአገሪቱ ችግሮች ወደ ዕድል ሲቀየሩ ለማኅበረሰቡ አይታዩም ማለት ነው?
 • እንደዚያ ማለቴ ሳይሆን…
 • ወይስ ለእኛ የሚታየው ለእናንተ አይታይም?
 • እንዴት?
 • ለእኛ የሚታየው የሰው ሕይወት እያጠፋ ያለ ግጭት ከቦታ ቦታ ሲስፋፋ ነው። ለእናንተ ግን የሚታያችሁ ሌላ ነገር ይሆን?
 • ፈተናዎች አሉ ቢሆንም ፈተናዎቹን ወደ ዕድል እየቀየርናቸው ነው ወደፊት የሚገጥሙን ፈተናዎችም ወደ ዕድል ይቀየራሉ።
 • እሱ ነገር እኮ ነው የሚገርመኝ?
 • ምኑ?
 • ሰዎች እየታሠሩና እየተሰወሩ ነው።
 • ይህንንም ወደ ዕድል እንቀይረዋለን።
 • ሰዎች መታሠራቸው ሲቆም ሳይሆን ከተፈቱ በኋላ አገር ጥለው ሲሰደዱ ነው የምናየው።
 • እሱን እኮ ነው የምልሽ?
 • ምን?
 • ወደ ዕድል እየቀየርነው ነው።
 • የሰዎች መታሰርን?
 • እህ…!
 • የታል የቀየራችሁት?
 • ይኸው ራስሽ ተናገርሽው አይደል እንዴ?
 • ምን አልኩኝ?
 • የታሠሩ ሰዎች ከአገር እየወጡ ነው አላልሽም?
 • ከአገር እየተሰደዱ ነው ያልኩት።
 • ያው ነው።
 • አሃ… እንዲህ ነው ወደ ዕድል የምትቀይሩት?
 • እንደዚያ አላልኩም።
 • እና ምና እያልክ ነው?
 • ቢታሠሩም ሲፈቱ የውጭ ዕድል ይገጥማቸዋል እያልኩ ነው።
 • እህ… ታሥረው የነበሩ አንድ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ከአገር ከወጡ በኋላ ፖለቲካ በቃኝ ማለታቸውንስ እንዴት ነው የምታየው?
 • እንደ ዕድል!
 • አሁን ዕድል የምትሉት ምን እንደሆነ በደንብ ገብቶኛል።
 • ምኑን ነው ዕድል የምንለው?
 • ፈተናዎቹን !

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሐዘን ለመድረስ ጎረቤት ተገኝተው ለቀስተኛው በሙሉ የሚያወራው ነገር አልገባ ብሏቸው ወደ ቤታቸው ከተመለሱ በኋላ ባለቤታቸውን ስለጉዳዩ እየጠየቁ ነው] 

ጎረቤታችን ሐዘን ለመድረስ ብሄድ ለቀስተኛው በሙሉ በሹክሹክታ ያወራል። ግን የሚያወሩት ነገር ሊገባኝ አልቻለም። ምንድነው የሚያወሩት? እኔ ምን አውቄ? እንዴት? የሚያወሩትን ምንም አልተሰማሽም? እኔ እንድሰማ የፈለጉ አይመስልም ግን ... ግን...

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...