Wednesday, June 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየውጭ ጣልቃ ገብነት እስከሌለ ድረስ መንግሥት ችግሮችን በሰላም ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን ጠቅላይ...

የውጭ ጣልቃ ገብነት እስከሌለ ድረስ መንግሥት ችግሮችን በሰላም ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገሩ

ቀን:

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚታዩ ግጭቶችን የውጭ ጣልቃ ገብነት እስከሌለ ድረስ በሰላማዊ መንገድና በድርድር ለመፍታት መንግሥት ቁርጠኛ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መናገራቸውን የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ገለጸ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት ለመጀመሪያ ጊዜ ከሠራተኛ ማኅበራት መሪዎች ጋር ረቡዕ ነሐሴ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው ባካሄዱት የውይይት መድረክ ላይ መሆኑን፣ የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የኢሠማኮ መሪዎች ምላሽ እንዲሰጥበት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቀረቧቸው ጥያቄዎች መካከል ከፀጥታ ችግር ጋር የተያያዘ ጉዳይ አንዱ እንደነበር አቶ ካሳሁን አስረድተዋል፡፡ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ መፈታታቸው ጠቀሜታ እንዳላቸው፣ የሰሜኑን ጦርነት መንግሥት በሰላም ለመፍታት የወሰደው ዕርምጃ ትክክለኛና ኢሠማኮም የሚደግፈው መሆኑን፣ ይህ ዕድል በሌሎች ክልሎች አሁን የሚታዩ ግጭቶችም በተመሳሳይ እንዲውል ጥያቄ ማቅረባቸውን አስረድተዋል፡፡

በተለይ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ያሉ ግጭቶችን በምሳሌነት በመጥቀስ በሰላማዊ መንገድ በድርድር ሊፈቱ እንደሚገባ ኢሠማኮ ላቀረበው ጥያቄ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በየትኛውም መንገድ ቢሆን መንግሥት ሰላም የሚሻ መሆኑን እንደገለጹላቸው አቶ ካሳሁን ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

ሰላም ከሌለ ለሠራተኛ ውጭ ሆነ ለሁሉም ሕዝብ ችግር በመሆኑ ጉዳዩ እንደሚያሳስብ የተናገሩት አቶ ካሳሁን፣ በአንዳንድ ድርጅቶች ውስጥ ሠራተኞች በታጣቂዎች እንደሚገደሉና እንደሚታገቱ በመጥቀስ ጭምር ግጭቶች በሰላም መፈታታቸው ተገቢ መሆኑን በማመን ጥያቄውን ማቅረባቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ማብራሪያ፣ ጥያቄዎቹ መቅረባቸው ትክክል መሆኑን በመግለጽ፣ መንግሥት ሁሉም ነገር በሰላም እንዲፈታ የሚፈልግ መሆኑን እንዳረጋገጡላቸው አቶ ካሳሁን ገልጸዋል፡፡ ‹‹ሰላምን የሚጠላ ስለሌለ ካልተገደድን በስተቀር ለእኛ ሰላም ከሁሉም በላይ ነው፤›› በማለት መንግሥት ለሰላም ቅድሚያ እንደሚሰጥ ጭምር መናገራቸውን ከቶ ካሳሁን ገለጻ ለማወቅ ተችሏል፡፡

‹‹እናንተም ምርትና ምርታማነት ተረጋግጦ ሥራዎችን ከመሥራት አንፃር ጥያቄውን ማንሳታችሁ ትክክል ነው፤›› እንዳሏቸው የተናገሩት አቶ ካሳሁን፣ ‹‹የውጭ ጣልቃ ገብነት ከሌለ በስተቀር እርስ በርሳችን በውይይት ችግሮቻችን የማንፈታበት ምክንያት አይኖርም፤›› በማለት መንግሥት የሚፈጠሩ ችግሮችን በሰላም ለመፍታት ሙሉ እምነት እንዳለው እንደነገሯቸው አመልክተዋል፡፡ ሰላምን ለማምጣት ግን የሁሉንም ርብርብ ይፈልጋል የሚል መልዕክታቸውን ለሠራተኞች መሪዎች የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ መንግሥት ሰላምን እንደሚሻ ተናግረዋል ብለዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ ከፀጥታ ችግር ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ከቀረቡ ጥያቄዎች ባሻገር፣ የሠራተኞች አንገብጋቢ የተባሉ ጥያቄዎችንም በሠራተኞች መሪዎች አማካይነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጥታ ቀርቧል ሲሉ አቶ ካሳሁን አስረድተዋል፡፡ ሦስት ሰዓታት እንደፈጀ በተነገረለት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ፣ ኢሠማኮ ሊመለሱ ይገባል ብሎ ላቀረባቸው የተለያዩ ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዎንታዊ ምላሽ የሰጡ መሆናቸውን አቶ ካሳሁን አብራርተዋል፡፡

‹‹ሊመልሱልን ይገባል ላልናቸው ጥያቄዎች ሁሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተፈጻሚ ይሆኑ ዘንድ አቅጣጫ ሰጥተዋል፤›› ያሉት አቶ ካሳሁን፣ ያደረጉት ውይይትም ጥያቄዎቻቸው በአግባቡ ሊመለሱ የሚችሉ መሆናቸውን ማረጋገጫ ያገኙበት መድረክ እንደነበረም አስታውሰዋል፡፡

ኢሠማኮ በዚህ መድረክ በዋናነት በዋጋ ንረት ምክንያት በሠራተኛው ላይ እየተፈጠረ ያለውን ጫና ለማርገብ፣ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲተገበርና የደመወዝ የሥራ ግብር እንዲቀንስ ጥያቄ ማቅረቡን ለማወቅ ተችሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...