Saturday, September 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅሞኞቹ

ሞኞቹ

ቀን:

በድሮ ጊዜ ነው ጥንት፡፡ ሁለት ሞኝ ባልና ሚስት ነበሩ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ዶሮ አረዱና ሚስትዮዋ ሠርታ ሊበሉ ሲሉ ለጥርሳቸው መጎርጎሪያ የሚሆን ሣር የሌለ መሆኑን ያስተውሱና ሊያመጡ ወደ ዱር ሔዱ፡፡ ወደ ዱር ሲሔዱ መንገድ ላይ አንድ ተማሪ አገኛቸው ተማሪውም፡-

“ወዴት ትሔዳላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው፡፡

“ዶሮ አርደን ሠርተን አስቀምጠን ለጥርሳችን መጎርጎሪያ ሣር ልናጭድ ነው”

“ቤታችሁ የት ነው”

“ያ እዚያ ማዶ እመንገዱ ዳር ያለው ነው” ብለው ነግረውት ወደ ሳር አጨዳ ተጓዙ፡፡

ተሜም እቤታቸው ሔደና ዶሮ ወጣቸውን ግጥም አድርጎ በልቶ ጠፋ፡፡ ባልና ሚስት ሣራቸውን አጭደው ተሸክመው እቤት ደረሱና ቢያዩ የወጡ ድስት ባዶውን ሆኖ ዝንብ ወርሮታል፡፡ በዚህ ጊዜ ዶሮ ወጣቸውን ዝንብ ነው የበላው ብለው በማመን በቤቱ ውስጠ ውር ውር የሚለውን ዝንብ መግደል ጀመሩ፡፡ ዝንቦች በእንስራው፣ በምጣዱ፣ በማሰሮው ላይ ሲያርፋ እነሱን አገኛለሁ በማለት የቤቱን ዕቃ ሁሉ ሲያነክቱት ቆዩ፡፡ በመጨረቫ አንዲት ዝንብ እሴትዬዋ ግንባር ላየ አረፈች፡፡ በዚህ ጊዜ ሴትዬዋ ዝንቧ ተነስታ እንዳትበር ቀስ ብላ በምልክት ባልዋን ጠቆመችው፡፡ ሰውየውም በያዘው ቆመጥ አስተካክሎ ግንባሯን ሲላት ጊዜ ውኃ ሳትል አረፈች ይባላል፡፡

ዘሪሁን አስፋው ‹‹የሥነ ጽሑፍ መሠረታውያን›› (1992)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...