Friday, September 29, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ እየጠራ ያለውን ሞባይል ስልካቸውን ተመለከቱ፣ የህዳሴ ግድቡ ተደራዳሪ መሆናቸውን ሲያውቁ ስልኩን አነሱት]

 • ሃሎ…
 • ጤና ይስልጥኝ ክቡር ሚኒስትር?
 • ጤና ይስልጥልኝ ክቡር ተደራዳሪ… የጥረትዎን ፍሬ በማየትዎ እንኳን ደስ አለዎት፡፡
 • እንኳን አብሮ ደስ አለን፣ ምን ልታዘዝ ታዲያ?
 • የውኃ ሙሌቱንና አጠቃላይ የግድቡን የግንባታ ሁኔታ በተመለከተ ቃለ መጠይቅ ጠይቀውኝ ሰጥቼ ነበር።
 • ለየትኛው ሚዲያ ነው የሰጡት?
 • ለብሔራዊ ቴሌቪዥናችን ነው።
 • እሺ፣ ምን ተፈጠረ ታዲያ?
 • ክቡር ሚኒስትራችን ስለግድቡ ሙሌት መጠናቀቅ ያስተላለፉት መልዕክት ላይ የነበረውን መጠነኛ የመረጃ መፋለስ ለማረም በቃለ መጠይቁ ላይ ማብራሪያ ሰጥቼ ነበር።
 • እሺ።
 • ነገር ግን ቴሌቪዥን ጣቢያው በዚህ ጉዳይ የሰጠሁትን ማብራሪያ ቆርጦ በማውጣት እንዳይተላለፍ አድርጎታል፣ የሚገርመው ይህንን ሲያደርጉ እኔን አላማከሩኝም።
 • አውቃለሁ ክቡር ተደራዳሪ።
 • ምኑን ነው የሚያውቁት ክቡር ሚኒስትር?
 • የሰጡት ማብራሪያ ተቆርጦ እንደወጣ አውቃለሁ፡፡
 • እንዴት እርስዎ አወቁ? ለእኔ እንኳን አልነገሩኝም እኮ፡፡
 • የጣቢያው ኃላፊ ደውሎልኝ ነበር።
 • ለምን?
 • ክቡር ሚኒስትራችን የመጨረሻው የግድቡ ሙሌት ተጠናቋል ማለታቸው ትክክል አይደለም የሚል ማብራሪያ ሰጥተውናልና ማስተላለፍ ይችሉ እንደሆነ ለመጠየቅ ነበር የደወሉት።
 • የእርስዎን ትዕዛዝ ጥሰው ነው የሰጠሁትን ማብራሪያ የቆረጡት ማለት ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • እንደዚያ አይደለም።
 • ታዲያ ማብራሪያውን ለምን ቆርጠው አወጡት?
 • እኔ ነኝ ቆርጠው እንዲያወጡ ያዘዝኳቸው።
 • እርስዎ ራስዎ ክቡር ሚኒስትር?
 • አዎ፡፡
 • ለምን?
 • ምክንያቱም ክቡር ሚኒስትራችንን ክብር የሚነካ በመሆኑ ነው።
 • እንዴት?
 • ምክንያቱም የሰጡት ማብራሪያ ክቡር ሚኒስትራችን እንደተሳሳቱ የሚገልጽና ክብራቸውን የሚነካ ነው።
 • እንዴት አድርጎ ነው ክብራቸውን የሚነካው?
 • ጥንቁቅ ናቸዋ? አይሳሳቱም።
 • እኔም እኮ መልዕክታቸው ብዥታን ፈጥሯል እንጂ ተሳስተዋል አላልኩም።
 • ቢሆንም የሰጡትን ማብራሪያ አለማስተላለፍ በራስ ላይ እንደ መተኮስ ነው።
 • እንዴት?
 • የአክቲቪስቶች መጫወቻ ነው የሚያደርጋቸው።
 • ግን እኮ ማኅበረሰባችን ላይ የተፈጠረውን መደናገር የማስተካከል ኃላፊነት አለብን፡፡
 • እሱን እረዳለሁ።
 • ታዲያ ለምን እንዳይተላለፍ ከለከሉ? ወይም ደግሞ እንደ ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊነትዎ ለምን ማብራሪያ አልሰጡበትም።
 • እሱን ማድረግ አልችልም፣ ተገቢ ነው ብዬም አላስብም።
 • ለምን?
 • ክቡር ሚኒስትራችን ይቀየሙኛል።
 • ለምን ይቀየማሉ?
 • ምክንያቱም ያስተላለፉት መልዕክት በበርካቶች ላይ ብዥታ መፍጠሩን ሳያውቁ ቀርተው አይደለም ዝምታን የመረጡት።
 • እህ… ስለዚህ ራሳቸው ስህተቱን ካላረሙ ትክክል ናቸው እያሉኝ ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ትክክል ሊሆኑም ላይሆኑም ይችላሉ፣ ነገር ግን…
 • ነገር ግን ምን?
 • እርሳቸው ዝምታን ከመረጡ እኛ እንዴት ብለን ተሳስተዋል እንላቸዋለን?
 • ስለዚህ ምን ማድረግ ነው የሚሻለው?
 • አብረዋቸው የሄዱ ሚኒስትሮች ያደረጉትን ማድረግ ነው የሚሻለው።
 • ሌሎቹ ምንድነው ያደረጉት?
 • አንዳንዶቹ ዝም ነው ያሉት፣ የተቀሩት ደግሞ መልዕክቱን ተቀብለው ‹‹የመጨረሻ ሙሌት›› ነው ብለዋል።
 • እና ምንድነው የሚሻለው?
 • ዝም!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...

ማን በማን ላይ ተስፋ ይኑረው?

በአንድነት ኃይሉ ችግሮቻችንን ለይተን ካወቅን መፍትሔውንና ተስፋ የምናደርግበትን ማወቅ እንችላለን፡፡...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ለሁለት ሳምንት ያክል የፓርቲ ስብሰባ ላይ ቆይተው አመሻሹ ላይ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ባለቤታቸው በአግራሞት ተቀብለው ስለቆይታቸው ይጠይቋቸው ጀመር]

እኔ እምልክ...? ውይ... ውይ... በመጀመሪያ እንኳን በሰላም መጣህ፡፡ እሺ ...ምን ልትጠይቂኝ ነበር? ይህን ያህል ጊዜ የቆያችሁት ለስብሰባ ነው? ስብሰባ ብቻ አይደለም። ከስብሰባ ውጪ ምን ነበር? በተለያዩ መሪ ሐሳቦች የተዘጋጁ ሥልጠናዎችን...

[ክቡር ሚኒስትሩ ለሁለት ቀናት የተካሄደውን የፓርቲያቸውን የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ አጠናቀው ወደ ቢሯቸው ሲመለሱ ቢሯቸው ውስጥ አማካሪያቸው አንድ ጽሑፍ በተመስጦ እያነበበ አገኙት]

ምንድነው እንደዚህ መስጦ የያዘህ ጉዳይ? መጡ እንዴ ክቡር ሚኒስትር፣ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያወጣውን መግለጫ እያነበብኩ ነው፡፡ ግን እኮ ፊትህ ላይ የመገረም ስሜት ይነበባል፡፡ አዎ፣ መግለጫው ላይ...

[የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሩ ክቡር ሚኒስትር ሌሊቱን በእንቅልፍ ልባቸው በህልም እየተወራጩ ሳለ የሞባይል ስልካቸው ጥሪ አነቃቸው። አለቃቸው ስለነበሩ ስልኩን በፍጥነት አነሱት]

በሌሊት ስለደወልኩኝ ይቅርታ፡፡ ችግር የለውም ክቡር ሚኒስትር፣ ምን ልታዘዝ? አንድ የአውሮፓ ባለሥልጣን ነገ በጠዋት ወደ አዲስ አበባ ይገባል። እሺ። ሌሎች የመንግሥት አመራሮች ስላልቻሉ እርስዎ መንግሥትን ወክለው ቦሌ ኤርፖርት...