Tuesday, February 18, 2025
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናከሕግ ውጭ በሲቪሎች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የዘፈቀደ እስሮች እንዳሳሰቡት ኢሰመኮ አስታወቀ

ከሕግ ውጭ በሲቪሎች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የዘፈቀደ እስሮች እንዳሳሰቡት ኢሰመኮ አስታወቀ

ቀን:

spot_img

ከተጠናቀቀው ዓመት ሐምሌ ወር ጀምሮ በአማራ ክልል የተፈጠረውን የትጥቅ ግጭት ተከትሎ፣ በሲቪሎች ላይ ከሕግ ወይም ከፍርድ ውጭ (Extra Judicial Killing) የሚፈጸሙ ግድያዎች እጅግ አሳሳቢ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ባለፈው ዓርብ መስከረም 4 ቀን 2016 ዓ.ም. ከግጭቱ ጋር ተያይዘው ስለተከሰቱትና ‹‹አሳሳቢነታቸው የቀጠለ የሰብዓዊ  መብቶች ጥሰቶች›› ብሎ በገለጸው ሪፖርት የተከሰቱትን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡

በፌዴራል መንግሥት ኃይሎችና በታጣቂ ቡድኖች (በተለምዶ ፋኖ ተብለው የሚጠሩ) መካከል በሚደረጉ የተኩስ ልውውጦች በእርሻ ሥራ ላይ፣ በመንገድ ላይና በቤታቸው ይገኙ የነበሩ ሰዎች መሞታቸውን ከዓይን ምስክሮች ተረዳሁ ብሎ ኮሚሽኑ ሪፖርቱን ያወጣ ሲሆን፣ ከፍርድ ውጪ የሚደረጉ ግድያዎችም እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን አሳውቋል፡፡

ኮሚሽኑ በመንግሥት የፀጥታ አካላት ተፈጸሙ ስላላቸው ከሕግ ውጪ ግድያዎች ምሳሌ ሲጠቅስ፣ ከሐምሌ 2 ቀን እስከ ጳጉሜን 4 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ደብረ ማርቆስ፣ ደብረ ታቦር፣ ማጀቴና ሸዋሮቢትን ጨምሮ በዘጠኝ ከተሞች በስፋት እንደተፈጸመ ጠቁሟል፡፡

ግድያዎቹ ከተፈጸሙባቸው ሰዎች መካከል ቤት ለቤት በተደረጉ ፍተሻዎችና በመንገድ ላይ የተያዙ ሰዎችን ጨምሮ ‹‹የጦር መሣሪያ ደብቃችኋል›› የተባሉ ሰዎችን እንደሚያካትት ኮሚሽኑ በሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡ ከሕግ ውጪ ግድያን ኮሚሽኑ በራሱና በአስቸኳይ ጊዜ መርማሪ ቦርዱ አማካይነት ተጨማሪና የተሟላ ምርመራ ሊደረግበት እንደሚገባም አሳስቧል፡፡

በአማራ ክልል የሚካሄደው የትጥቅ ግጭት በክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች መስፋፋቱንና ‹‹በነዋሪዎች ላይ የሚደርሰው ጉዳትም ተባብሶ መጠቀሉን›› ኮሚሽኑ ከነዋሪዎች፣ ከተጎጂ ቤተሰቦችና ከዓይን ምስክሮች መረጃ በመውሰድ እንደተረዳ አሳውቋል፡፡

የቦታዎችን ስሞች በመጥቀስ በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ከተሞችና የገጠር ቀበሌዎች የሚገኙ ሲቪል ሰዎች መሞታቸውንና ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን፣ እንዲሁም ንብረታቸው መውደሙን እንደተረዳ ባወጣው ሪፖርት ገልጿል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር መጨረሻ ጀምሮ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ የአስቸኳይ ጊዜ መምሪያ ኮማንድ ፖስት በይፋ ካሳወቃቸው እስሮችና ቦታዎች በተጨማሪ ‹‹በአማራ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልልና በአዲስ አበባ ከተማ ‹‹የዘፈቀደ እስሮች›› ተፈጽመዋል፤›› ብሏል በሪፖርቱ፡፡

በአማራ ክልል በሚገኙት የባህር ዳር፣ ደብረ ታቦር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ጎንደር፣ ላሊበላ፣ መካነ ሰላም፣ ቆቦና ሸዋ ሮቢት ከተሞች፣ በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማና በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች ‹‹የዘፈቀደ እስሮች እየተፈጸሙ›› እንደሚገኙ ኮሚሽኑ በሪፖርቱ አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የጤናው ዘርፍ ባለፉት ስድሥት ወራት

የወባ በሽታ ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ዋነኛ የጤናና...

የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት በባለሙያ ዓይን

(በጎ ጎኖችና እርምት የሚፈልጉ ጉዳዮች) በዮሐንስ መኮንን በጥር ወር 2016 ዓ.ም....

በልዩነት ውስጥ ሆነንም እስኪ እንነጋገር

በገነት ዓለሙ ዴሞክራሲ መብቶችና ነፃነቶች የሚሠሩበት የሕዝብ አስተዳደር ነው፡፡ ሰብዓዊ...

ለጤናማ የትራፊክ ፍሰትና ለመንገድ ደኅንነት ቅጣት መጣል ብቻውን መፍትሔ አይሆንም!

በአዲስ አበባ ከተማ ለተሽከርካሪዎች ምቹ የሆኑ መንገዶችን እየተመለከትን ነው፡፡...