Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህል‹‹ሻና ቶቫህ ዑመቱካህ!››

‹‹ሻና ቶቫህ ዑመቱካህ!››

ቀን:

‹‹ሻና ቶቫህ ዑመቱካህ!… ሻና ቶቫህ ዑመቱካህ!›› ኢትዮጵያውያኑ ቤተ እስራኤሎችም ሆኑ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ እስራኤላውያን ከትናንት በስቲያ ዓርብ ምሽት ጀምሮ እስከ ዛሬ ዕለተ እሑድ ድረስ ያስተጋቡት፣ ኃይለ ቃል ነው፡፡ በዕብራይስጥ ቋንቋ መልካምና የተስማማ ዓመት ይሁንልህ፣ ይሁንልሽ እንደማለት ነው፡፡ ይህ የመልካም ምኞት መግለጫው መንሥኤም እስራኤል አዲሱን 5784 ዓመተ ዓለምን ቅዳሜ መስከረም 5 ቀን 2016 መጀመሯ ነው፡፡

‹‹ሻና ቶቫህ ዑመቱካህ!›› | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
በእስራኤል ኤምባሲ የኢትዮጵያና
የእስራኤል አዲስ ዓመት

በአይሁድ የዕለት አቆጣጠር መሠረት ቅዳሜ የገባው ዓርብ ምሽት ላይ ሲሆን፣ ‹‹ሮሽ ሃሻናህ›› የሚባለው የዓመት መነሻ ርዕሰ ዓመት፣ ቤተ እስራኤሎች ለሥርዓተ አምልኮ በሚገለገሉበት የግዕዝ ቋንቋ ‹‹ሠረቀ ብርሃን›› – የአዲስ ዘመን ብርሃን ወጣ ይሰኛል፡፡

መስከረም 5 ቀን ማታ አዲሱን የአይሁድ አዲስ ዓመት 5784 ዓመትን የጀመሩበት ትሽሪ 1 ‹የጨረቃ ጥቅምት 1› ቀመሩ የፀሐይና የጨረቃን ጥምር አቆጣጠር የሚከተል ነው፡፡

ሮሽ ሃሻናህ፣ የሚውልበት ወቅት በእስራኤል የበልግ ማለትም የፀደይ (በኢትዮጵያ የሚገኙት ግን ወቅቱ መፀው) ወቅታቸው ላይ ነው፡፡  

‹‹ሻና ቶቫህ ዑመቱካህ!›› | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
የሕይወት ዑደትን አመልካቹ ባለ ክቡ
ቻላህ ዳቦ በማር ይበላል

 ድርሳናት እንደሚገልጹት፣ የትሽሪ ወር አዳምና ሔዋን የተፈጠሩበት ወር፣ የዓለም የልደት ቀንም ነው፡፡ ምሽቱ ቀንደ መለከት (ሾፋር) የሚነፉበት ምክንያት አንደኛው የእስራኤል ሕዝብ ለመሰብሰብ የሚደረግ መሆኑን ለማመልከት ነው፡፡

በሮሽ ሃሻናህ በዕለቱ የጣፈጡ ምግቦች ይበሉበታል፡፡ ‹‹የጣፈጡ ነገሮች ማር በአፕል እየተነከረ የሚበላው ዓመቱና ቀሪው ዘመን ያማረና የጣፈጠ እንዲሆን ነው፡፡

ከ5783 ዓመተ ዓለም ወደ 5784 በዓመቱ የመጀመርያ ወር ትሽሪ 1 (የጨረቃ ጥቅምት 1) ላይ የተሸጋገረው የአይሁድ አዲስ ዓመት ወሩን በጨረቃ፣ ዓመቱን በፀሐይ ይቆጥራል፡፡

ከነሐሴ መካተቻ እስከ መስከረም የመጀመርያ ሳምንት በየዘመኑ የሚመላለሰው ሮሽ ሃሻናህ፣ ከአራቱ የአይሁድ አዲስ ዓመቶች አንዱ ነው፡፡ ሌላኛው በኒሳን ወር (የጨረቃ ሚያዝያ) የሚከበረው አይሁድ ከግብፅ የወጡበት ዕለት የሚታሰብበት ነው፡፡ በቶራህ- ዘሌዋውያን እንደተጻፈው፣ ሮሽ ሃሻናህ የመጥቅዕ (ደወል/ቀንደ መለከት) በዓል ተብሎም ይታወቃል፡፡

በዕብራይስጥ በርእሰ ዓመቱ ሮሽ ሃሻናህ መልካም ምኞት ሲገለጽ ‹‹ሻና ቶቫህ›› መልካም ዘመን፣ ‹‹ሻና ቶቫህ ዑመቱካህ›› ማለትም መልካምና የተስማማ ጣፋጭ አዲስ ዓመት ይሁን! ይላል፡፡

በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩት ቤተ እስራኤሎች በየምኩራቦቻቸው በመገኘት በዓሉ ቀንደ መለከት (ሼፋር) በመንፋት አክብረውታል፡፡

በሮሻ ሃሻና ብርሃን ሠረቀ በተለይ ከሚበሉ ምግቦች ማር፣ ፖም፣ የዓሣ ራስ፣ ቴምር፣ ካሮት ይገኙበታል፡፡ በአንድ ጽሑፍ ላይ እንደተጠቀሰው፣ እነዚህ ምግቦች በዓውደ ዓመት የሚበሉት ለምሳሌ የዓሣ ራስ፣ ራስ እንጂ እግር አይደለንም ለማለት፣ ማር መጪው ሕይወት ፈጣሪ እንደማር እንዲያጣፍጠው፣ ፖም ብዙ ፍሬዎች ስላለው ሕይወታችን እንደ ፖም ፍሬ እንዲያበዛና እንደ ማር እንዲጣፍጥ፣ ቴምር ጠንካራ ስለሆነ ጥንካሬን ለመመኘት፣ ካሮት ደግሞ አምላክ መልካም ፍርድን እንዲያስቀምጥ ለመመኘት ነው።

በክብረ በዓሉ ወቅት የሚበላው ባህላዊው ዳቦ ቻላህ ክብ ነው፡፡ ይህም የሕይወት ዘላለማዊ ዑደትን ያመለክታል። ቻላህን በማር መበላቱም አዲሱ ዓመት ጣፋጭ እንዲሆን ከመመኘት ባለፈ ተስፋንም ያሳያል ይላሉ።

የአዲስ አበባው ዝግጅት

በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ የኢትዮጵያና የእስራኤል አዲስ ዓመት መድረስ ምክንያት በማድረግ በዋዜማው ጳጉሜን 6 ቀን 2015 ዓ.ም. በቅጥር ግቢው ከጋበዛቸው እንግዶቹ ጋር አክብሯል፡፡  ከተገኙት መካከል የኢትዮጵያና የእሥራኤል የሃይማኖት አባቶች፣ ቤተ እስራኤላውያን፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ ይገኙበታል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አቶ አለልኝ አድማሱ ባሰሙት ዲስኩር፣ እስራኤልና ኢትዮጵያ በታሪክ፣ በባህልና በዲፕሎማሲ የረዥም ጊዜ ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው፣ የሁለቱ አገሮች የዘመን መለወጫ ጊዜም ተቀራራቢ መሆኑ አንዱ የግንኙነቱ ማሳያ ነው ማለታቸው ተዘግቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...