Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ሰይጣን ሰለጠነ

ትኩስ ፅሁፎች

ሰይጣን ሰለጠነ

ቀንዶቹን ነቃቅሎ፣ ጭራውንም ቆርጦ፣

ከሰው ልጆች ጋራ አንድነት ተቀምጦ

ሊኖር ነው ጨምቶ

ከሰው ልጆች ጋራ ሊጋባ ተጫጭቶ።

ሰይጣን ሰለጠነ፣

ዘመናዊ ሆነ።

ፊደል ቆጠረና ዳዊትም ደገመ፣

በስመ አብ ብሎ ውዳሴ ማርያምን፣

አንቀጸ ብርሃንን መልካ መልኩን ሁሉ፣

አጠና ፈጠመ።

ከዚህም በኋላ ጾም ጸሎት ጀመረ፤

በመጨረሻውም አቡን ተክሌ አጥምቀው

ክርስትና አነሱት።

ግና ተቸገረ፤

እንዲያው በየዕለቱ

ጨርሶ አላወቀም ለማን እንደሆነ ጾምና ጸሎቱ፤

ቢጨንቀው ጊዜና ቆይቶ ሰንብቶ፣

ክርስቲያን የሆነ አንድ ሰው አግኝቶ፣

ተወዳጀውና ብሶቱን ነገረው ሁሉንም ዘርዝሮ፣

በጣፈጠ ቋንቋ በ‘ውነት አሳምሮ።

«አትቸገር» አለው ክርስቲያን ወዳጁ አፅናናው መልሶ፣

ሰይጣኑ ካሰበው አለመጠን ብሶ፤

«ይህስ ቀላል ነገር ችግርም የለው፣

እንደኛው ክርስቲያን ሆንክ ማለት ነው።»

  • ዮሐንስ አድማሱ ‹‹እስኪ ተጠየቁ››
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች