Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየትግራይ ክለቦች ወደ አገራዊ ውድድሮች እንዲመለሱ የክልሉ ፌዴሬሽን አዘዘ

የትግራይ ክለቦች ወደ አገራዊ ውድድሮች እንዲመለሱ የክልሉ ፌዴሬሽን አዘዘ

ቀን:

  • መቐለና ወልዋሎ ለብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ደብዳቤ አስገብተዋል

በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከአገራዊ ውድድሮች የቀሩት የትግራይ ክልል ክለቦች በዘንድሮ አገራዊ ውድድሮች እንዲካፈሉ የትግራይ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን መወሰኑ ተገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ በተለያዩ የውድድር ደረጃዎች ሲካፈሉ የነበሩት የክልሉ ክለቦች፣ ባቋረጡበት እንዲቀጥሉ ፍላጎት እንዳላቸው ቢገለጽም፣ በአንፃሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአዲሱ የውድድር ዘመን አንድ ደረጃ ወርደው እንዲሳተፉ መወሰኑ  ይታወሳል፡፡

ውሳኔውን ተከትሎም የክልሉ ፌዴሬሽን ጨምሮ በርካታ ክለቦች ውሳኔውን በመቃወም እንደማይቀበሉ ሲገልጹ ከርመዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ቀድሞ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲካፈሉ የነበሩት መቐለ ሰብዓ እንደርታ፣ ስሑል ሸረና ወልዋሎ ዓዲግራት በከፍተኛ ሊግ የመሳተፋቸው ጉዳይ አጠራጣሪ ሆኖ ቆይቷል፡፡

ሆኖም የክልሉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማንኛውም የክልሉ ክለብ ለአገራዊ ውድድር ተሳትፎ እንዲመዘገብ መመርያ ማስተላለፉ ተሰምቷል፡፡

በዚህም መሠረት ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት መቐለ ሰብዓ እንደርታና ወልዋሎ ዓዲግራት በከፍተኛ ሊግ ለመሳተፍ ለብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ደብዳቤ ማስገባታቸውን የፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በቀጣይ ቀናት ሌሎችም ክለቦች ተመሳሳይ ውሳኔ ይወስናሉ የሚል ግምት እንዳላቸው አክለዋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ፣ በትግራይ የሚገኙ ክለቦች ላለፉት ሦስት ዓመታት በአገር አቀፍ ውድድሮች ሳይሳተፉ መቅረታቸውን ተከትሎ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ውድድር እንዲመለሱ መጥራቱ ይታወሳል፡፡

ይህንን ተከትሎ የፌዴሬሽን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ ክፍል 11 ማጠቃለያ ድንጋጌዎች አንቀጽ 91 መሠረት፣ ያልተጠበቁ ድንገተኛና ከአቅም በላይ አስገዳጅ ሁኔታዎች በሚለው አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት፣ ‹‹ያልተጠበቀ፣ ድንገተኛና ሊመልሱት የማይቻል ሁኔታ ሲያጋጥም ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በጉዳዩ ላይ የመወሰን ሥልጣን ይኖረዋል፤›› እንደሚል ይጠቅሳል፡፡

ውሳኔዎች የፊፋና የካፍ አግባብነት ያላቸውን ደንቦችን፣ እንዲሁም የሚመለከታቸው አስገዳጅ ሕጎችን ከግምት ያስገባ እንደሆነ ያስቀምጣል፡፡

የትግራይ ክልል ክለቦች ደንቡ ላይ ከተጠቀሰው ከአንድ ጊዜ በላይ ከውድድር ውጪ የነበሩ በመሆኑ እንደ አዲስ ከክልል ክለቦች ሻምፒዮና መጀመር እንዳለባቸው ያስቀምጣል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...