Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ  በአቤቱታዎች ብዛት ተጥለቅልቄያለሁ አለ

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ  በአቤቱታዎች ብዛት ተጥለቅልቄያለሁ አለ

ቀን:

  • ሥራውን ለማቃለል የሥነ ሥርዓት ደንብ ማዘጋጀቱንቋል

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ በሕገ መንግሥት ጉዳዮች አቤቱታ ብዛት መጥለቅለቁን አስታወቀ፡፡ ጉባዔው ይህን በጉዳዮች የመጥለቅለቅ ችግር ለመፍታት ያግዘኛል ያለውን የሥነ ሥርዓት ደንብ ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

ለተቋሙ ምንም እንኳ ዋነኛ የሚባሉ የሕገ መንግሥት ጉዳዮችን የሚመለከቱ ይዘት ያላቸው አቤቱታዎች በብዛት እየመጡለት ባይሆንም፣ ከፍተኛ የሆነ ቁጥር ያላቸው አቤቱታዎች እየቀረቡለት መሆኑን ገልጿል፡፡

ከሰሞኑ በተዘጋጀው ረቂቅ የሥነ ሥርዓት ደንብ ላይ ውይይት ሲደረግ፣ በመድረኩ የተገኙት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምሕረት፣ ‹‹ጉባዔው በጉዳዮቹ ተጥለቅልቋል በሚባልበት ደረጃ ላይ ይገኛል፤›› ብለዋል፡፡

ከ5,000 በላይ የሕገ መንግሥት ይጣራልኝ አቤቱታዎች በጉባዔው የተመዘገቡ መሆናቸውንና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በዓመት የሚታዩት አቤቱታዎች ከ150 አይበልጡም ነበር ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ በተያዘው ዓመት ቢያንስ 1,000 ጉዳዮችን ለማየት ዕቅድ መያዙን አስረድተዋል፡፡

ይሁን እንጂ አሁንም በዓመት 150 ጉዳዮች እየታዩ የሚቀጥሉና ብዛታቸውም በዚህ መሠረት ከቀጠለ፣ በአሁኑ ወቅት ለጉባዔው የቀረቡት አቤቱታዎች ለማየት 23 ዓመታት ይፈጃል ብለዋል።

አጣሪ ጉባዔው በመሠረታዊነት የመዋቅር ችግርና የሕግ ማዕቀፍ አለመኖሩንና በተለይም በሕገ መንግሥቱ  አንቀጽ 84 መሠረት የማስፈጸሚያ ደንብ እንደሚወጣ ቢገልጽም፣ እስካሁን ድረስ ከ20 ዓመታት በላይ ያለ ምንም የሥነ ሥርዓት ደንብ ሲሠራ መቆየቱ መሰናክል መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም የጉባዔው አባላት ሌላ መደበኛ ሥራ ያላቸው በመሆናቸው፣ ጉዳዮቹ በትርፍ ጊዜ እንጂ በመደበኛ ሥራ ስለማይከናወኑ ሌላኛው ማነቆ ነው ብለዋል።

በሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ አሁን እየታዩ ያሉት ጉዳዮች በ2011 እና በ2012 ዓ.ም. የቀረቡ ናቸው የሚሉት አቶ ቴዎድሮስ፣ ዜጎች በፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጠባቸውን ጉዳዮች ወደ ጉባዔው ይዘው እየመጡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡  ትክክለኛ ያልሆነ ተስፋ ይዘው የሚመጡ የኅብረተሰብ ክፍሎችን፣ የፍርድ ቤቶችን አሠራር በማሻሻል ወደ ጉባዔው የሚመጣውን አቤቱታ ቁጥር በመቀነስ የጉባዔው ሥራ ሊታገዝ ይገባል ብለዋል።

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ የቀረቡለትን አቤቱታዎች መርምሮ በየወሩ ውሳኔ መስጠት እንዳለበት የተደነገገ ቢሆንም፣ የተከማቹ አቤቱታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ በመሆናቸው በተፈለገው ጊዜ ምላሽ መስጠት አለመቻሉን የገለጹት ደግሞ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንትና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሮ አበባ እምቢአለ ናቸው፡፡

ወ/ሮ አበባ እንደገለጹት፣ ከ1991 እስከ 2015 ዓ.ም . ባለው ጊዜ ከቀረቡት 8,027 አቤቱታዎች መካከል ለ4,340 ያህሉ የውሳኔ ሐሳብ ተሰጥቶባቸው 170 ያህሉ የሕገ መንግሥት ትርጉም የሚያስፈልጋቸው በመሆናቸው ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀርበዋል።

አብዛኛውን ጊዜ ወደ ጉባዔው እየመጡ ያሉት ጉዳዮች በፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጣቸው ናቸው የሚሉት ወ/ሮ አበባ፣  አንኳር የሆኑ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወደ ጉባዔው  እየቀረቡ አለመሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በዚህም የተነሳ የሕገ መንግሥት አጣሪ ጉባዔ ከሰበር ችሎት ቀጥሎ ሌላኛው ፍርድ ቤት በመሆኑ፣ በዝግጅት ላይ ያለው የሥነ ሥርዓት ደንብ ይህን ችግር ለመፍታት የተዘጋጀ ነው ብለዋል።

የአሠራር ሥነ ሥርዓት ደንቡ  የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄዎችና አቤቱታዎችን የማጣራት ሥራን በፍጥነት፣ በግልጽነትና ለተገልጋይ ቀላል በሆነ መንገድ ለመተግበርና የሕገ መንግሥት አተረጓጎም ሥርዓቱን የተሻለ ለማድረግ እንደሚያስችል አክለዋል፡፡

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሥራ ከጀመረበት ከ1991 ጀምሮ እስከ 2015 በጀት ዓመት ድረስ ከተለያዩ ተቋማት፣ ቡድኖች፣ ግለሰቦችና የፖለቲካ ፓርቲዎች 8,027 አቤቱታዎችን  መቀበሉን አስታውቋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...