Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበድንበሮች አካባቢ በሚደረጉ ልማቶች ላይ ያተኮረው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ ተካሄደ

በድንበሮች አካባቢ በሚደረጉ ልማቶች ላይ ያተኮረው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ ተካሄደ

ቀን:

  • ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ኅብረት የ650 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አገኘች

የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ በድንበሮች አካባቢ የሚደረጉ ልማቶች ላይ በመምከርና የቀጣናውን ድንበሮች ለማልማት በተዘጋጀ ፍኖተ ካርታ ላይ በመወያየት 18ኛውን የሚኒስትሮች ስብሰባ አካሄደ፡፡

ስብሰባው የተካሄደው በኢኒሼቲቩ ሰብሳቢና በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፣ እንዲሁም በቀጣናው የሚገኙ የገንዘብ ሚኒስትሮችና የልማት አጋሮች ተወካዮች በተገኙበት ትናንት ማክሰኞ መስከረም 22 ቀን 2016 ዓ.ም. በስካይላይት ሆቴል ነው፡፡

ሰብሳቢው አቶ አህመድ ሽዴና የልማት አጋር ተወካዮች የመክፈቻ ንግግር ካደረጉ በኋላ፣ የስብሰባውን ሒደት ለመዘገብ የተገኙ የሚዲያ አባላትን በማስወጣት በፍኖተ ካርታው ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ የዓለም ባንክ ተወካዮች ፍኖተ ካርታውን እንዳቀረቡ ታውቋል፡፡

በድንበር አካባቢ የሚደረጉ ልማቶችንና በምሥራቅ አፍሪካ የግሉን ዘርፍ ተሳታፊነት ለማሳደግ ያቀደው ስብሰባው፣ ሚኒስትሮቹ በቀረበላቸው ፍኖተ ካርታ ላይ ሰፋ ያለ ስብሰባ እንደሚያደርጉበትና ግብዓታቸውን በማከል ወደ ቀጣይ እንቅስቃሴ እንደሚገባበት ተገልጿል፡፡

‹‹ሚኒስትሮቹ በተዘጋጀው ፍኖቶ ካርታ ላይ ይሁንታቸውን እንዲሰጡ የሚጠየቁ ሲሆን፣ በቀጣይ ይሁንታቸውን ከሰጡ በኋላ ወደ ትግበራ ይኬዳል፤›› ይላል ሪፖርተር የተመለከተው ገንዘብ ሚኒስቴር ያዘጋጃቸው ሰነድ፡፡

በመጨረሻም የዓለም ባንክ በተጠናቀቀው የ2015 ዓ.ም. መገባደጃ ላይ ከአዲስ አበባ ጂቡቲ ለሚካሄደው መንገድ ግንባታ እንዲውል የሰጠው የ730 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍን በሚመለከት የስምምነት ፊርማ በማኖር ስብሰባው ተጠናቋል፡፡

በስብሰባው ላይ ተገኝተው ከነበሩት መካከልም የአውሮፓ ኅብረት ዓለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር ዮታ ኡርፒላይነን ሲሆኑ፣ ከገንዘብ ሚኒስትሩ ጋር በነበራቸው ሌላ ስብሰባ ኅብረቱ ለኢትዮጵያ ባፀደቀው የ650 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ላይ ተፈራርመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...