Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትከኢትዮጵያ አትሌቶች አቅም ጋር ያልተመጣጠነው የዓለም የግማሽ ማራቶን ሩጫ ውጤት

ከኢትዮጵያ አትሌቶች አቅም ጋር ያልተመጣጠነው የዓለም የግማሽ ማራቶን ሩጫ ውጤት

ቀን:

በየዓመቱ አዳዲስ ኩነቶችን እያካተተና እያሻሻለ የመጣው የዓለም አትሌቲክስ፣ የውድድር መድረኮችን ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡ የአንድ ቀን የአትሌቲክስ ውድድሮችን ጨምሮ፣ በሁለት ዓመትና በየዓመቱ የሚከናወኑ ውድድሮች በዓለም አትሌቲክስ አዘጋጅነት በተለያዩ ከተሞች ይስተናገዳሉ፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዓለም አትሌቲክስ ዕውቅና አግኝተው መከናወን ከጀመሩ ውድድሮች መካከል፣ ከቀናት በፊት የተጠናቀቀው የዓለም የጎዳና አትሌቲክስ ሻምፒዮና ይጠቀሳል፡፡

እሑድ መስከረም 20 ቀን 2016 ዓ.ም. በላቲቪያ ሪጋ የተከናወነው የመጀመርያው የዓለም የጎዳና ሩጫ፣ በርካታ የዓለም ከዋክብት አትሌቶች ተሳትፈውበታል፡፡ ለመጀመርያ ጊዜ በተከናወነው በዚህ ሻምፒዮና የ5 ኪሎ ሜትር፣ የማይል፣ እንዲሁም የግማሽ ማራቶን ውድድሮች ተሰናድተዋል፡፡

ከኢትዮጵያ አትሌቶች አቅም ጋር ያልተመጣጠነው የዓለም የግማሽ ማራቶን ሩጫ ውጤት | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
የጎዳናው ሩጫ ሲጀመር

ምንም እንኳን ውድድሩን ዘግይቶ የጀመረ ቢሆንም፣ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከትራክ ውድድሮች ይልቅ፣ ወደ ጎዳና ፊታቸውን ላዞሩ አትሌቶች ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡ ከዚህም ባሻገር በርቀቱ ልምድ ያካበቱ በርካታ አትሌቶች መኖራቸው ሰፊ የውድድር ዕድል እንዲፈጠርላቸው መንገድ ጠርጓል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በመጀመርያው የጎዳና ሩጫ ሻምፒዮና ሁለት ወርቅ፣ አራት ብር፣ እንዲሁም አንድ ነሐስ፣ በድምሩ 7 ሜዳሊያዎች በመሰብሰብ ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡  

ኢትዮጵያ በ5 ኪሎ ሜትር ወንዶች ሐጎስ ገብረ ሕይወት ወርቅ፣ እንዲሁም በሴቶች በማይል ውድድር በድርቤ ወልተጂ ሁለተኛ ወርቅ ተገኝቷል፡፡

ሐጎስ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 12፡59 የሆነ ጊዜ የፈጀበት ሲሆን፣ የቦታው ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቦለታል፡፡ ሌላኛው የወርቅ ባለድል ድርቤ 4፡20፡98 በሆነ ጊዜ የዓለም ክብረ ወሰን መጨበጥ ችላለች፡፡

ዮሚፍ ቀጄልቻ በ5 ኪሎ ሜትር፣ ፍሬወይኒ ኃይሉ በማይል ውድድር በወንዶች፣ እንዲሁም በሴቶች ግማሽ ማራቶን በአጠቃላይ አራት የነሐስ ሜዳሊያዎች ተገኝተዋል፡፡

በሴቶች 5 ኪሎ ሜትር እጅጋየሁ ታዬ ብቸኛውን የነሐስ ሜዳልያ ማምጣት የቻለች ኢትዮጵያዊት አትሌት ናት፡፡

በአንፃሩ ኬንያ በመጀመርያው ውድድር አምስት የወርቅ፣ ሦስት የብርና አራት የነሐስ በድምሩ 12 ሜዳሊያዎች በማግኘት ከዓለም አንደኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች፡፡

የምንጊዜም የኢትዮጵያ አትሌቶች ተፎካካሪ የሆኑት ኬንያዊውያን፣ በሁለቱም ፆታ በግማሽ ማራቶን ወርቅ፣ በ5 ኪሎ ሜትር ወርቅ መሰብሰብ ችለዋል፡፡

ሁለቱ አገሮች ተመጣጣኝ የሆኑና በሁሉም ርቀቶች በርካታ አትሌቶች እንዳላቸው ይታመናል፡፡ በተለይ በጎዳና ሩጫ ከበቂ በላይ አትሌቶቹ የታደሉ ናቸው፡፡ ለዚህም ማረጋገጫነት በተለያዩ ውድድሮች ላይ የሚካፈሉ አትሌቶችን መመልከት በቂ ነው፡፡

ሆኖም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በሻምፒዮና የሚጠበቀውን ውጤት ማምጣት አለመቻሉ ይነሳል፡፡ እንደ ባለሙያዎች አስተያየት ከሆነ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በተለይ በግማሽ ማራቶን የበላይነትን መውሰድ ይገባው እንደነበር ያነሳሉ፡፡

በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ለውድድሩ የሰጠው ዝቅተኛ ግምት፣ በሻምፒዮናው የታሰበውን ማሳካት አለመቻሉን ያነሳሉ፡፡

ስማቸው እንዳይጠቀስ ያልፈለጉ ባለሙያው፣ ‹‹ኬንያውያን ለውድድሩ የሰጡት ትኩረትና ኢትዮጵያውያን የሰጡት ግምት ለየቅል ነው፤›› ሲሉ ይጠቅሳሉ፡፡

ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ እንደ በጎ ጎን ቢጠቀስም፣ ከተፎካካሪዋ ኬንያ ጋር ያለው ውጤት መራራቁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለሻምፒዮናዎች የሚሰጡት ትኩረት መታየት እንዳለበት ያሳየ ሆኗል፡፡

በርቀቱ የተለያዩ አማራጭ አትሌቶች ቢኖሩም፣ እንዲሁም አትሌቶቹ በቂ ዝግጅት ባለማድረጋቸው የተጠበቀውን ውጤት ማምጣት አለመቻሉ እንደምክንያት ይጠቀሳል፡፡

ከዚህም ባሻገር አብዛኛዎቹ አትሌቶች በዓለም ሻምፒዮና ላይ የቆዩ መሆናቸው፣ እንዲሁም መስከረምና ጥቅምት ወራት ማራቶን የሚከናወንባቸው በመሆናቸው፣ አብዛኛው አትሌት በሻምፒዮናው ለመካፈል አለመቻሉ ተጠቁሟል፡፡

በአንፃሩ ኬንያውያን አትሌቶች የዓለም ሻምፒዮናቸውን ሳይቀር መጠቀማቸው ለሻምፒዮናው የሰጡትን ትኩረት የሚያመለክት ነው ተብሏል፡፡ በዚህም መሠረት በቡዳፔስት ዓለም ሻምፒዮና በዳይመንድ ሊግ ጭምር ሲሳተፉ የከረሙ ተወዳዳሪዎችን በመጀመርያ የጎዳና ሻምፒዮና ማሳተፍ ችለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በርካታ አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች ማፍራት ብትችልም፣ በሻምፒዮና ላይ የሚሠሩ ጥቃቅን ስህተቶች ቡድኑን ዋጋ ሲያስከፍለው መመልከት እየተለመደ መጥቷል፡፡

ለዚህም የአሠልጣኞች ከዘመኑ ጋር ያለመጓዝና ራሳቸውን በዕውቀት ያለማሳደግ ችግር መሆኑን አብዛኛዎቹ ያነሱታል፡፡ ይህም አሠልጣኞቹ ዘመኑ የሚዋጀውን የሥልጠና ሒደት መከተል እንደሚገባቸው አስተያየታቸውን የሚሰጡ አሉ፡፡ ይህም በቴክኖሎጂ በመታገዝና ልምድን በሥልጠና ማዳበር እንደሚገባ ይነሳል፡፡.   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...