Wednesday, December 6, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምየኖቤል ሰላም ተሸላሚው በኮንጎ ለፕሬዚዳንትነት ሊወዳደሩ ነው

የኖቤል ሰላም ተሸላሚው በኮንጎ ለፕሬዚዳንትነት ሊወዳደሩ ነው

ቀን:

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተካሄዱ ግጭቶች፣ በሴቶች ላይ የደረሰውን መደፈርና ፆታዊ ጥቃትን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከታቸው፣ እ.ኤ.አ. በ2018 የኖቤል ሰላም ተሸላሚ የሆኑት የማህፀን ሐኪሙ ደኒስ ሙክዌገ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት መሆን እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው፣ የ68 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋው ሙክዌገ በመጪው ታኅሣሥ በሚካሄደው ምርጫ ለፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር ዝግጁ መሆናቸውን ያስታወቁት፣ ከትናንት በስቲያ ሰኞ በኪንሻሳ ከተማ ለተሰበሰቡት ደጋፊዎቻቸው ባሰሙት ንግግር ነው፡፡

የወቅቱን ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ቲሺሴኬዲን ለመፎካከርና ሥልጣኑን ለመጨበጥ ቆርጠው መነሳታቸውንም አስተጋብተዋል፡፡

ከአምስት ዓመት በፊት በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተሸንፈው የነበሩት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ማርቲን ፋይሉም እንደሚወዳደሩም ገልጸዋል፡፡

የኖቤል ሰላም ተሸላሚው በኮንጎ ለፕሬዚዳንትነት ሊወዳደሩ ነው | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

‹‹የሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት ለመሆን ዕጩ ተወዳዳሪያችሁ ሆኜ ለመቅረብ ወስኛለሁ፡፡ አመሰግናችኋለሁም፤›› ያሉት እኚሁ የማህፀን ሐኪም ሙክዌገ እ.ኤ.አ. በ1990 በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተካሄደው ግጭት ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ሴቶችን፣ ኪንሻሳ በሚገኘውና ራሳቸው ባቋቋሙት ፓንዚ ሆስፒታል ተገቢው እንክብካቤና ሕክምና እንዲያገኙ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡

‹‹ሴቶችን የሚፈውሰው ሰው›› የሚል ቅጽል ስም የተሰጣቸው ሙክዌገ፣ ፆታዊ ጥቃት የሚያደርሱትን በመቃወም ለሁለት አሠርታት ባደረጉት ትግል ይታወቃሉ፡፡

በአሁኑ ጊዜ የማዕከላዊው አፍሪካ አገር፣ በርካታ የሚሊሺያ ታጣቂዎች አማካይነት የፀጥታው ሁኔታ ከዕለት ወደ ዕለት እያሽቆለቆለ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ያመለከተው ዘገባው፣ ታጣቂዎቹ የምሥራቁን የአገሪቱን ክፍል ለመቆጣጠር እየተንቀሳቀሱ ናቸው ብሏል፡፡

ፕሬዚዳንት ትሺሴኪዲ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው ሁከቱን ለመቆጣጠር ሲጥሩ እንደነበር ያመለከተው ዘገባው፣ በአገሪቱ ተሰማርቶ የነበረው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰላም አስከባሪ ኃይል ውጤታማ ባለመሆኑ አገሪቱን ለቆ እንዲወጣ ቢወስኑም ሳይሳካ ቀርቷል ብሏል፡፡

ከአንድ ወር በፊት የተመድን ኃይል ለመቃወም አደባባይ በወጡት ላይ የአገሪቱ ሠራዊት በወሰደው የኃይል ዕርምጃ 56 ሰዎች መገደላቸውም ከፍተኛ ነቀፌታን አስከትሏል፡፡

ሙክዌገ ባለፈው ወር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ‹‹የደረሰው ጭፍጨፋ አስደንጋጭና የሚያናድድ ነው፤›› ያሉ ሲሆን፣ የአገሪቱ የፀጥታና የመከላከያ አገልግሎት ሙያዊ እንዲሆን ‹‹እጅግ ትልቅ ለውጥ›› እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

በታኅሣሥ 10 ቀን 2016 ዓ.ም. ለማካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት፣ የፓርላማና የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እየተቃረበ ባለበት ወቅት፣ እንደ ፀጥታና ምጣኔ ሀብታዊ ችግሮች ባሉ ጉዳዮች ላይ ያለው ክርክር አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2018ቱ ምርጫ በትሺሴኪዲ የተሸነፉ የተቃዋሚ መሪ ማርቲን ፋዩሉ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ለፕሬዚዳንትነት እንደሚወዳደሩም አስታውቀዋል፡፡

የሙክዌገ ሥራ በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ ምሥጋና እና አድናቆት ያገኘ ሲሆን፣ በግጭቶች ወቅት የሚፈጸሙት ዘግናኝ የፆታዊ ጥቃት ወንጀሎች አስፈላጊው ትኩረት እንዲያገኙም አስደርጓል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...