Wednesday, December 6, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሥራ መልስ በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ከባለቤታቸው ጋር በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን የፓርላማ መክፈቻ እየተከታተሉ ነው]

  • ምን… ምንድነው ያሉት?
  • ምነው ምን ሆንሽ?
  • መንግሥት የጀመረው የማዕድ ማጋራት የዜጎችን የኑሮ ደረጃ በማሻሻል ረገድ አስተዋጽኦ አድርጓል ነው ያሉት?
  • አዎ፣ እንደዚያ ነው ያሉት።
  • እንዴት?
  • ምን እንዴት አለው?
  • ያለነው በመኖሪያ ቤታችን አይደል እንዴ?
  • ነው።
  • ስለዚህ እንዴት ማለት እንችላለን።
  • ምን ለማለት ፈልገሽ ነው?
  • ያለነው ፓርላማ አይደለም ማለቴ ነው።
  • እንዴት?
  • ምን እንዴት አለው?
  • አልገባኝም?
  • እዚያ እንዴት ተብሎ አይጠይቅማ?
  • መንግሥት ማዕድ እያጋራ መሆኑ የሚታወቅ ሀቅ አይደለም እንዴ? ምን ተብሎ ይጠየቃል?
  • ማዕድ ስታጋሩማ እኛም እናያለን።
  • ታዲያ ምንድነው ያስገረመሽ?
  • መንግሥት ዓውደ ዓመት ሲመጣ የሚያጋራው ማዕድ ፓርላማ ላይ ስለተነገረ አይደለም የተገረምኩት።
  • ታዲያ ምንድነው ያስገረመሽ?
  • መንግሥት ማዕድ ማጋራቱ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ በማሻሻል ረገድ አስተዋጽኦ አድርጓል መባሉ ነው።
  • እንዴት? ይኼ ምኑ ያስገርማል?
  • የዜጎች ኑሮ ደረጃ ተሻሻለ የሚባለው የበዓል ቀን ሲበሉ ነው?
  • ለማለት የፈለጉት እንደዛ አይደለም።
  • እኔ እሳቸው የተናገሩትን አዳምጫለሁ፣ እናንተ የፈለጋችሁትን ማለት ትችላላችሁ።
  • የፈለጋችሁትን ማለት ትችላላችሁ ስትይ ምን ማለትሽ ነው?
  • እናንተ እሳቸው የተናገሩትን ሳይሆን ለማለት የፈለጉትን በሉ ማለቴ ነው፣ ቆይ …ቆይ እስኪ … እንዴ…?
  • ምንድነው?
  • አትሰማም እንዴ የሚሉትን?
  • አልሰማሁም ምንድነው ያሉት?
  • በመንግሥት የምገባ ፕሮግራም9 ሚሊዮን ተማሪዎች ቁርስና ምሣ እየበሉና ቀጥለው ደግሞ…
  • እ… ቀጥለው ምን አሉ?
  • የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም ድህነትን ከመቀነስ ባሻገር አምራች ዜጋ ለመፍጠርና ትውልድ ለመገንባት የሚያስችል ለውጥ አምጥቷል አሉ፡፡
  • እና ምነው ተገረምሽ?
  • እንዴት አልገረምም?
  • ለምን?
  • ድህነት በምገባ ፕሮግራም ይቀንሳል እንዴ?
  • ለምን አይቀንስም?
  • በምገባ ፕሮግራም ሊቀንስ የሚችለው ድህነት አይመስለኝም።
  • እና ምንድነው የሚቀንስ የሚመስልሽ?
  • በምገባ የሚቀንስው?
  • እ…?
  • ረሃብ ነዋ፡፡
  • አትሳሳቺ፣ ድህነትንም ለመቀነስ ይጠቅማል።
  • እኮ እንዴት?
  • የምግባ ፕሮግራሙ የተማሪ ቤተሰቦችን እያገዘ ነዋ፡፡
  • እና ድህነት በቁርስና በምሣ ይቀንሳል ልትለኝ ነው?
  • ለምን አይቀንስም?
  • ኧረ ዛሬ ምንድነው የምሰማው?
  • ምን ሰማሽ?
  • አትሰማም እንዴ የሚሉትን?
  • ምን አሉ?
  • በየማዕከላቱ የሚመገበው የሕዝብ ብዛት እንደ አገር ቢቆጠር በአፍሪካ በ35ኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ ነው እያሉ እኮ ነው?
  • እሱማ እውነት ነው፣ እንዲያውም እሳቸው በደረጃ አስቀመጡት እንጂ ከአገሮች ጋር ቢያነፃፅሩት ይሻል ነበር።
  • እንዴት? ምን ማለትህ ነው?
  • በማዕከላቱ የሚመገበው የሕዝብ ብዛት የኢኳቶሪያል ጊኒ፣ የጋቦንና የቦትስዋና ሕዝቦች ተደምረው ማለት እኮ ነው።
  • አሃ… እንዲህም ማሰቀመጥ ይችሉ ነበር?
  • ታዲያስ?
  • ይገርማል፡፡
  • የሚያስደንቅ ነው እንጂ፡፡
  • ሰማሁ እኮ፡፡
  • ምን?
  • መጨረሻ ላይ ያሉትን።
  • ምን አሉ?
  • በየምገባ ማዕከላቱ የሚመገበው በሕዝብ ብዛት ደረጃ ቢታይ በአፍሪካ 35 ደረጃ ላይ የሚቀመጥ ነው፣ ይህም የአገራችንን ኢኮኖሚ ጥንካሬ የሚያሳይ ትልቅ ስኬት ነው አሉ።
  • ትክክል ነው።
  • ይገርማል።
  • ምኑ ነው የሚገርመው?
  • ይህን የሚያህል ሕዝብ በመንግሥት ምገባ ሥር መሆኑ ለእኔ የሚሰጠኝ ትርጉም ሌላ ነው።
  • ምንድነው?
  • ያለው ድህነት ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ።
  • እኛ ግን እንደዚያ ብለን አንወስድም።
  • የገረመኝ በእሳቸው መነገሩ እንጂ፣ እናንተማ የምትኩራሩበት መሆኑን አውቃለሁ።
  • መንግሥት እኮ ነው የሚያዘጋጀው፡፡
  • ምኑን?
  • የእሳቸውን ንግግር።
  • እንደዚያ ነው እንዴ?
  • አዎ።
  • ታዲያ ቀድመህ አትነግረኝም ነበር!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...

ኦሮሚያ ኢንሹራንስ በግሉ ኢንሹራንስ ዘርፍ ሁለተኛውን የገበያ ድርሻ ለመያዝ ያስቻለውን ውጤት ማስመዝገቡን ገለጸ

ኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ የባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት፣ የመለዋወጫ ዕቃዎች...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ ነው? እንዴት? አለቃዬ ዕረፍት የለው፣ እኔንም አላፈናፍን ብሎኛል። ታድለሽ። ታድለሽ? ሥራ ገደለኝ ዕረፍት አጣሁ እኮ ነው ያልኩሽ? ገብቶኛል። ምነው እኔንም...

[ክቡር ሚኒስትሩ የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸማቸውን ለተከበረው ምክር ቤት ካቀረቡ በኋላ ከምክር ቤቱ አባላት የሚነሱ ጥያቄዎችን እየተቀበሉ ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው]

ክቡር ሚኒስትር መንግሥት ለሕዝብ ይፋ ያደረገው ነገር ከምን እንደደረሰ ቢያብራሩልን? ምንድነው ይፋ ያደረገው? ጥያቄውን ትንሽ ቢያብራሩት? ከአራት ዓመት በፊት በኦጋዴን አካባቢ ነዳጅ መገኘቱን ለሕዝብ በቴሌቪዥን አብስሮ...

[ክቡር ሚኒስትሩ አንድ የካቢኔና የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ አባል የሆኑ ከፍተኛ አመራር የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያደመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረግህ፣ ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...