Sunday, February 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜና‹‹የመመካከርና የመነጋገር ባህል ስለሌለን ሰላምን ውድ እያደረግናት ነው›› ሌተና ጄኔራል አለምሸት ደግፌ

‹‹የመመካከርና የመነጋገር ባህል ስለሌለን ሰላምን ውድ እያደረግናት ነው›› ሌተና ጄኔራል አለምሸት ደግፌ

ቀን:

  • 116 ዓመታትን ያስቆጠረው የአገር መከላከያ ሠራዊት ከ1900 እስከ 2016

የጦር ሠራዊት አባል ሆነው አገራቸውንና ሕዝባቸውን ማገልገል ከጀመሩ ግማሽ ክፍለ ዘመን ሊሞላቸው አንድ ዓመት ፈሪ መሆናቸውን የሚናገሩት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ወታደራዊ አማካሪና የተኩስ አመራር ኃላፊ ሌተና ጄኔራል ዓለምሸት ደግፌ፣ ‹‹የመመካከርና የመነጋገር ባህል ስለሌለን ሰላምን ውድ እያደረግናት ነው›› ሲሉ ተናገሩ፡፡

ሌተና ጄኔራሉ ከነገ ጥቅምት 12 እስከ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ለአምስት ቀናት የሚከበረውን 116ኛውን የአገር መከላከያ ሠራዊት ቀን አስመልክተው እንደተናገሩት፣ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች መመለስ ያለባቸው የሕዝብ ጥያቄዎች መኖራቸው ዕሙን ቢሆንም፣ ጥያቄዎቹን በአግባቡና ሕግን በተከተለ ሁኔታ ተመካክሮና ተነጋግሮ መመለስ ሲገባ፣ የፖለቲካ ሥልጣን ለመያዝ ወይም የጥቂቶችን ፍላጎት ለማሳካት እየተሄደበት ያለው መንገድ ተገቢ አለመሆኑን ነው፡፡

በአገሪቱ በሁሉም አካባቢ እየተታኮሰ ያለ ‹‹ለእኔ ሁሉም ጽንፈኛ ነው›› ያሉት ጄኔራሉ፣ ዓላማ ያለውና ዓላማው የሚያሻግር ከሆነ፣ ለሕዝብ ቀርቦ ሕዝብ ሊወስንበት እንደሚገባም አክለዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹ኢትዮጵያን እናስቀጥል፣ የወደቁትን እናስታውስ እንዘክር፣ ያሉትን እናመስግን›› ያሉት ሌተና ጄኔራል ዓለምሸት፣ እሳቸውን ጨምሮ በኢትዮ ሶማሌ (1970 ዓ.ም.)፣ በኢትዮ ኤርትራ፣ በትግራይና አሁንም ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ወታደሩ እየተዋደቀ ያለው አገር ለማስቀጠል በመሆኑ፣ በዓመት አንድ ቀን ማስታወስ ሲያንሰው እንጂ እንደማይበዛበት ተናግረዋል፡፡

ወታደር ብዙ ተከፍሎት ሳይሆን እየራበውና እየጠማው የሚዋደቀው አገር ለማስቀጠል በመሆኑ ‹‹ውትድርና ክብር የሚገባው ሙያ ነው›› ብለዋል፡፡

‹‹ወታደርነት አንዳንድ ሰው ዘበኝነት የሚመስለው አለ፡፡ ነገር ግን ሞቶ የሚያኖር ነው›› ያሉት ጄኔራሉ፣ መከላከያ (ወታደር) የፖለቲካ ሥልጣን ለመያዝ የሚፈልግ አካልም ቢኖር፣ ወታደር እንደሚያስፈልገው ጠቁመው፣ መከላከያን ለማፍረስ የሚደረገው መፍጨርጨር ኢትዮጵያን ማፍረስና እርስ በርስ መባላት መሆኑን በማወቅ መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡

በሁሉም አቅጣጫ መሣሪያ አንስቶ የሚንቀሳቀሰው ኢትዮጵያን አፍርሶ የራሱን ግዛት ለማስፋፋት ከሆነ ‹‹ያ በፍጹም አይሆንም›› የሥልጣን ጥያቄ የሚመለሰው ጽንፈኛ በመሆን ሳይሆን በካርድ ብቻ መሆን እንዳለበትም አስረድተዋል፡፡

በመከላከያ ላይ የሚደረገው ፕሮፖጋንዳ ስህተትና ተገቢ አለመሆኑን የተናገሩት ጄኔራሉ፣ ኢትዮጵያን ከጣሊያን ወረራ ጀምሮ ያቆያት ሠራዊቱ መሆኑ ታውቆ ማክበር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡

ሠራዊቱ የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ዓላማ አራማጅ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚያስከብርና ሕዝቡን የሚጠብቅ መሆኑን ጠቁመው፣ በብሔርና በሃይማኖት ለመከፋፈል የሚሞክሩ ከድርጊታቸው መቆጠብ እንዳለባቸው አስጠንቅቀዋል፡፡

‹‹በትግራይ ጦርነት ወቅት የተከበረ ሠራዊት፣ ለምን በአማራና በኦሮሚያ ሌላ ስም ይሰጠዋል?›› በማለት የጠየቁት ጄኔራሉ፣ ከየትም ይነሳ ከየት ከኦሮሞም ይሁን፣ ከአማራም ይሁን ከትግራይ ወይም ከሌላ አካባቢ ጽንፈኛ ጽንፈኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሕዝብ የሚራኮተው ለጥቂት የፖለቲካ ሥልጣን ናፋቂዎች መሆኑን ጠቁመው፣ አብሮ ያጨበጨበ ተጠቃሚ ሊሆን ከሚችል በስተቀር ሌላ ውጤት ስለማያመጣ፣ መጠንቀቅና ቆም ብሎ ማሰብ ጥቅም እንዳለው መክረዋል፡፡

ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ሕዝቡ በግዳጅ ገንዘብ እንዲሰጥ እየተደረገ መሆኑንና ኢትዮጵያ ውስጥ ሥርዓት አልበኝነት ሊመጣ ጫፍ ላይ መድረሱን ጠቁመው፣ ይህ ከመሆኑ በፊት ግን ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ሌተና ኮሎኔል ዓለምሸት ደግፌ መክረዋል፡፡

በንጉሥ አፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ የጦር ሠራዊት ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ ከ1900 ዓ.ም. ጀምሮ፣ በተለያዩ ስያሜዎች ቀጥሎ የሚገኘው የአገር መከላከያ፣ ዘንድሮ 116ኛ ዓመቱን ከጥቅምት 12 እስከ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. እንደሚያከብር የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ተናግረዋል፡፡ ያለማንም ጣልቃ ገብነት በተደረገ ጥናት፣ ሠራዊት የሚያስፈልገው ለጦርነት ቢሆንም፣ የሕዝብ አለኝታ መሆኑ በመረጋገጡና ቀኑ መከበር እንዳለበት ስምምነት ላይ በመደረሱ፣ ‹‹ጥቅምት 15 ቀን የአገር መከላከያ ሠራዊት ቀን›› ሆኖ እንዲከበር በአዋጅ መደንገጉንም ተናግረዋል፡፡ ቀኑ በፓናል ውይይቶች፣ ከሕዝብ ጋር በመወያየት፣ ዓውደ ርዕዮችን በማሳየትና በተለያዩ መርሐ ግብሮች እንደሚከበር ኮሎኔል ጌትነት ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...