Sunday, April 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜና‹‹ዜጎችን በሚያፈናቀሉና ሕይወት በሚያጠፉ ላይ ዕርምጃ አለመውሰድ ፍትሕ የማግኘት መብትን መጣስ ነው››...

‹‹ዜጎችን በሚያፈናቀሉና ሕይወት በሚያጠፉ ላይ ዕርምጃ አለመውሰድ ፍትሕ የማግኘት መብትን መጣስ ነው›› የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)

ቀን:

ዜጎችን ከመደበኛ የመኖሪያ ቦታቸው ያፈናቀሉ፣ የሰው ሕይወት ያጠፉ፣ ሀብት ያወደሙ፣ አካላዊ ጉዳት ያደረሱ ቡድኖችና ግለሰቦች በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ በቂ ዕርምጃዎች ባለመወሰዳቸው የሕግ በላይነት፣ ተጠያቂነትንና የተፈናቃዮችን ፍትሕ የማግኘት መብት የሚነፍግ ነው ሲል፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ሁለተኛውን በአገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ የሚያተኩር ዓመታዊ ሪፖርት ዓርብ ጥቅምት 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ አድርጓል፡፡ ሪፖርቱ እንደሚያመላክተው በዘፈቀደ ለሚደረጉ የማፈናቀል ድርጊቶች አስተማሪ ዕርምጃዎች እየተወሰዱ አለመሆኑን ገልጿል፡፡

ዘላቂ የመፍትሔ አማራጮች አተገባበርም የመፈናቀል ምክንያት የሆኑትን የደኅንነት ሥጋቶች ባስወገደ፣ ተፈናቃዮችንና ተቀባይ ማኅበረሰብን ባሳተፈ፣ የተፈናቃዮችን ፍላጎት ባገናዘበ፣ እንዲሁም ተፈናቃዮችን በዘላቂነት በሚያቋቁም ሁኔታ ባለመሆኑ፣ ለዳግም መፈናቀል የሚያጋልጥ ስለመሆኑም አስታውቋል፡፡ አብዛኛዎቹ ተፈናቃዮች ዘላቂ መፍትሔ ሳያገኙ በመጠለያ ጣቢያዎችና ከተቀባይ ማኅበረሰብ ጋር ተቀላቅለው መኖር ከጀመሩ በትንሹ ሦስት ዓመታት እንዳለፋቸውም ገልጿል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በሌላ በኩል ተገቢው ጥበቃ የማይደረግላቸው፣ እንዲሁም የሲቪልነት ባህሪን ያልጠበቁ በወታደራዊ ካምፖች አካባቢ የሚኖሩ ተፈናቃዮች የሚገኙባቸው መጠለያ ጣቢያዎች መኖራቸው፣ የተፈናቃዮች የደኅነነት ሁኔታ አደጋ ላይ መሆኑን እንደሚያሳይ፣ በተጨማሪም መንግሥት በካምፓላ ስምምነት መሠረት የተጣለበትን ግዴታ በአግባቡ አለመወጣቱን የሚጠቁም ነው ብሏል፡፡

መንግሥት ፈርሞ የተቀበለውን አኅጉራዊ የካምፓላ ስምምነትን ለማስፈጸም የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ፀድቆ ሥራ ላይ አለመዋሉና የተፈናቃዮችን ጉዳይ በባለቤትነት የሚያስተዳድር ተቋማዊ አደረጃጀት አለመኖሩ በመግለጫው ተገልጿል፡፡

በዚህም መፈናቀልን ለመከላከል ለተፈናቃዮች የሚደረጉ የጥበቃና ድጋፍ ሥራዎች፣ እንዲሁም የዘላቂ መፍትሔ ማፈላለግ ሒደቶች ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶች አሁንም አሳሳቢነታቸው መቀጠሉን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

የተፈናቃዮች ምዝገባና ሰነድ የማግኘት ሥርዓቱ ላይ ያለው ክፍተት ለተፈናቃዮች የሚደረገው ድጋፍ በአግባቡ እንዳይከናወን አሉታዊ ተፅዕኖ ከማሳደሩ በተጨማሪ፣ ተፈናቃዮች ሌሎች የመንቀሳቀስና የማኅበራዊ አገልግሎት የማግኘት መብቶቻቸውን ለመጠቀም እንዳይችሉ ስለማድረጉም በመግለጫው አስታውቋል፡፡

መግጫው የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለን ጠቅሶ እንዳመላከተው፣ በኢትዮጵያ 80 በመቶ የሚሆነው መፈናቀል ኃይል በተቀላቀለባቸው ግጭቶች ምክንያት የሚከሰት በመሆኑ መፈናቀልን ለመከላከልና በዘላቂነት መፍትሔ ለመስጠት፣ በዋናነት ግጭቶችን ወቅታዊ በሆነ ሁኔታ በሰላማዊ መንገድ መፍታት ያስፈልጋል፡፡

የተፈናቃዮችን የተሟላ ጥበቃ ማረጋገጥ የሁሉንም መንግሥታዊ ተቋማት ትኩረትና ትግበራ የሚፈልግ ቢሆንም፣ የሚመለከታቸውን ተቋማት ተግባራትና በዘርፉ የተሰማሩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላትን ሥራዎች ለማስተባበርና ለመምራት ቅንጅታዊ አሠራር አለመዘርጋቱን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡ በዚህም ይህን የሚያስተባብር በሕግ ግልጽ ሥልጣን የተሰጠው አካል አለመኖሩ፣ ለአገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚደረግ ጥበቃና ድጋፍ ላይ ክፍተት እንዲኖር ካደረጉ ምክንያቶች መካከል ዋነኛው ነው ብሏል፡፡

የተፈናቃዮችን ጥበቃ በተመለከተ የሚሠሩ ሥራዎች የትኛው የመንግሥት ተቋም በበላይነት የመምራትና የማስተባበር ኃላፊነት እንዳለው አለመታወቁ፣ የጥበቃና የድጋፍ ሥራዎች በተቀናጀ ሁኔታና በአግባቡ እንዳይታቀዱና እንዳይከናወኑ ስለማድረጉም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

የኮሚሽኑ ሪፖርት በስምንት ክልሎች ውስጥ በሚገኙ ወደ 350,000 የሚገመቱ ተፈናቃዮችና 18,637 ተመላሾች፣ እንዲሁም ወደ ሌላ ቦታ የተዘዋወሩ ተፈናቃዮች በ44 የመጠለያ ጣቢያዎች፣ 11 ተቀባይ ማኅበረሰቦች፣ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቀዬአቸው የተመለሱባቸውን አራት አካባቢዎች፣ እንዲሁም ተፈናቃዮች በዘላቂነት ሰፍረው የሚኖሩባቸውን ሦስት አካባቢዎች ሰብዓዊ መብቶች አያያዝን መፈተሹን ኢሰመኮ አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

‹‹ደስታ›› የተባለችው አማርኛ ተናጋሪ ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም

‹‹እንደ ሮቦት ዋነኛው አገልግሎቴ ውስብስብ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና አሠራሮችን...