Thursday, December 7, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

[የሚኒስትሩ ባለቤት ልጃቸውን ከሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት ተደውሎላቸው ቤተሰብ ለልጁ ድጋፍና ክትትል ማድረግ አለበት የተባሉትን ለክቡር ሚኒስትሩ እየነገሯቸው ነው]

 • ለምንድነው እንደዚያ ያሉት? አስቸግሮ ነው?
 • እንደዚያ እንኳን አይደለም።
 • በምን ምክንያት ነው ታዲያ?
 • በሲቪክ ትምህርት ላይ ጥሩ አይደለም ነው የሚሉት።
 • በሲቪክ ትምህርት ብቻ ነው?
 • እንደዚያ ነው ያሉኝ።
 • እንዴት?
 • በክፍል ውስጥም፣ እንዲሁም ሰሞኑን በነበረው ፈተና ላይ ጥሩ እንዳልነበር ነው የነገሩኝ።
 • ስለፈተናው የነገሩሽ ነገር አለ?
 • አዎ። ስለ ገዥ ፓርቲ ተግባርና ኃላፊነት አስረዳ ተብሎ የሰጠው ምላሽ ቤተሰብ ድጋፍና ክትትል እንደማያደርግለት ያሳያል ነው የሚሉት።
 • እንዴት?
 • አንተም አልፎ አልፎ እንኳን ልታስጠናው አትሞክርም።
 • ና እስኪ ወዲህ አንተ፡፡ ስለገዥ ፓርቲ ተግባርና ኃላፊነት አታውቅም።
 • ኧረ አውቃለሁ።
 • በዚህ ትምህርት ላይማ ጎበዝ መሆን አለብህ፣ እኔን እንዳታሳፍረኝ።
 • እሺ።
 • በል ና ወዲህ ላስረዳህ፡፡
 • እሺ ዳድ፡፡
 • ይኸውልህ …የአንድ ገዥ ፓርቲ ተግባርና ኃላፊነት ምንድነው ከተባልክ አገር መምራት ብለህ ነው መመለስ ያለብህ።
 • አውቃለሁ።
 • ታዲያ ለምን እንደዚያ ብለህ አልመለስክም?
 • ብያለሁ።
 • ታዲያ ምን አድርግ ነው የሚሉት? ትክክለኛ መልስ እኮ ነው የሰጠው?
 • ግን ጥያቄው በዝርዝር አስረዳ የሚል ስለነበር ሌሎች መልሶችንም ጽፌያለሁ።
 • አገር መምራት ከሚለው ሌላ መልስ ጽፈሃል?
 • አዎ።
 • ምን ምን አልክ?
 • ምን ነበር ያልኩት … አዎ አስታወስኩት።
 • እስኪ ንገረኝ?
 • ሥልጠና መስጠት።
 • ምን! … ሥልጠና መስጠት ነው ያልከው?
 • አዎ!
 • ወይ ጉድ…
 • ተሳስቻለሁ እንዴ ዳድ?
 • ቆይ እስኪ ሌላስ ምል አልክ?
 • * ስለጠና ከሚለው ሌላ …?
 • እ…. ሌላ ያልከው የለም?
 • አለ።
 • ምን አልክ?
 • ምን ነበር ያልኩት …አዎ አስታወስኩት።
 • ምን አልክ?
 • ማጥናት።
 • እ…?
 • ተሳስቻለሁ እንዴ ዳድ?
 • ስለ ገዥ ፓርቲ ሥልጣንና ተግባር እኮ ነው የተጠየቅከው?
 • እኮ!
 • ታዲያ ማጥናት እንዴት ይሆናል?
 • ለምን አይሆንም ዳድ?
 • እንዴት ይሆናል? እሺ ስለምንድነው የሚያጠናው አልክ?
 • ስለ ተፈጥሮ።
 • ምን…?
 • ስለተፈጥሮና የሰውነት አካላት፡፡
 • እ…?
 • እንዴት እንደዚህ ልትል ቻልክ?
 • ምነው? ተሳስቻለሁ እንዴ ዳድ?
 • ቆይ… ማን ሲል ሰምተህ ነው?
 • ማንም?
 • ታዲያ ከየት አመጣኸው?
 • ቴሌቪዥን ላይ አይቼ ነው።
 • ምንድነው ያየኸው?
 • ሥልጠና ሲሰጥ።
 • እ…?
 • ማሚ …ትላንት በቴሌቪዥን ሥልጠና ሲሰጥ ተላልፎ የለ?
 • አዎ።
 • እና እዚያ ላይ ሲወራ አልሰማሽም?
 • ምን ሲወራ?
 • ስለ ውኃና ስለ የሰውነት አካላት?
 • በይ ይህንን ቴሌቪዥን ዝጊልኝ።

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...

ኦሮሚያ ኢንሹራንስ በግሉ ኢንሹራንስ ዘርፍ ሁለተኛውን የገበያ ድርሻ ለመያዝ ያስቻለውን ውጤት ማስመዝገቡን ገለጸ

ኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ የባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት፣ የመለዋወጫ ዕቃዎች...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ ነው? እንዴት? አለቃዬ ዕረፍት የለው፣ እኔንም አላፈናፍን ብሎኛል። ታድለሽ። ታድለሽ? ሥራ ገደለኝ ዕረፍት አጣሁ እኮ ነው ያልኩሽ? ገብቶኛል። ምነው እኔንም...

[ክቡር ሚኒስትሩ የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸማቸውን ለተከበረው ምክር ቤት ካቀረቡ በኋላ ከምክር ቤቱ አባላት የሚነሱ ጥያቄዎችን እየተቀበሉ ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው]

ክቡር ሚኒስትር መንግሥት ለሕዝብ ይፋ ያደረገው ነገር ከምን እንደደረሰ ቢያብራሩልን? ምንድነው ይፋ ያደረገው? ጥያቄውን ትንሽ ቢያብራሩት? ከአራት ዓመት በፊት በኦጋዴን አካባቢ ነዳጅ መገኘቱን ለሕዝብ በቴሌቪዥን አብስሮ...

[ክቡር ሚኒስትሩ አንድ የካቢኔና የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ አባል የሆኑ ከፍተኛ አመራር የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያደመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረግህ፣ ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...