Thursday, December 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየቱሪዝም ጠቀሜታ እስከ ምን?

የቱሪዝም ጠቀሜታ እስከ ምን?

ቀን:

ኢትዮጵያ በርካታ ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ የቱሪስት መስህቦች ያሏት አገር ነች፡፡ ያሏትን የተፈጥሮ ሀብቶች፣ ታሪካዊ ቅርሶች እንዲሁም የማይዳሰሱ ትውፊቶች በአግባቡ ለመጠቀም ፖሊሲዎች እንደ አዲስ ቢከለሱም የተፈለገውን ያህል ለውጥ ማምጣት አልተቻለም፡፡

በተለይ ቱሪዝም ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለው ዘርፍ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ደግሞ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተፅዕኖ ሳያገግም በጦርነትና በግጭቶች ምክንያት ጉዳት እያስተናገደ መሆኑ በተደጋጋሚ ይነገራል፡፡

ጦርነቱ የቱሪዝም እንቅስቃሴ በሰፊው እንዲቋረጥ ከማድረጉ በተጨማሪ፣ የቱሪዝም መዳረሻዎችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መውደማቸው ችግሩን ‹‹በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ›› አድርጎታል፡፡ ይሁን እንጂ ቱሪዝም ዘርፉን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግና ያሉትን ችግሮች ለመፍታት የአዲስ አበባ ከተማ ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ እየሠራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ቢሮው ‹‹ቱሪዝም ለአረንጓዴ ልማት፣ አረንጓዴ ልማት ለቱሪዝም›› በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 20 እስከ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበረውን የዓለም የቱሪዝም ቀን ምክንያት በማድረግ፣ መሪ ቃሉን መነሻ ያደረገ ጥናታዊ ጽሐፉ ዓርብ ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም. የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ለውይይት ቀርቦ ነበር፡፡

ለውይይት የቀረበውን ጥናታዊ ጽሑፉ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአገር ልማት ጥናት ኮሌጅ ዲን ተስፋዬ ዘለቀ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ በዓለም ላይ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች በአረንጓዴ ልማት የታገዙ ናቸው፡፡

በያዝነው ዓመት የሚከበረው የቱሪዝም ቀን መሪ ቃል ሊመረጥ የቻለበት ምክንያት፣ የአካባቢ ልማት ጥበቃን ለማስተዋወቅ እንዲሁም ዘላቂ የሆነ የልማት ግቦችን ወደ ተሻለ ነገር ለማምጣት በማሰብ መሆኑን ተስፋዬ (ዶር) አስረድተዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ በርካታ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች ያላት አገር ናት፤›› የሚሉት ዲኑ፣ እነዚህን መዳረሻ ቦታዎች በአግባቡ በማልማት ከዘርፉ የሚፈለገውን ያህል ኢኮኖሚዊ ጥቅም ማግኘት እንደሚያስፈልግ አክለው ገልጸዋል፡፡

በአረንጓዴ ልማት ተደግፈው የሚሠሩ አብዛኛውን የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች ማራኪና ውብ መሆናቸውን ገልጸው፣ እነዚህ ቦታዎች ጎብኚዎች የሚፈልጓቸውና የሚመርጧቸው ናቸው ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሒሩት ካሳው (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ የዓለም የቱሪዝም ድርጅት መሥራችና አባል መሆኗ በቱሪዝም የዳበረች አገር እንድትሆን አድርጓታል፡፡

በተለይ አገሪቱ የዓለም የቱሪዝም መዳረሻ ብቻ ሳትሆን፣ ወደ መስህብነት እየተለወጠች በመሆኗ፣ በከተማችን ከአምስት ዓመታት ወዲህ እየተሠሩ ያሉ መዳረሻዎች የዓለም ቱሪስቶችን ቀልብ ስቧል ሲሉ አብራርተዋል፡፡

በዘንድሮ ዓመት የሚከበረው የዓለም የቱሪዝም ቀን ከሌሎች ቀናቶች ለየት የሚያደርገው የጌዴኦ የባህላዊ መልክዓ ምድርና የባሌ ተራሮች በዓለም ቅርስነት በማስመዝገብ በአፍሪካ ቀዳሚ እንድትሆን ያደርጋታል ያሉት የቢሮው ምክትል ኃላፊና የቱሪዝም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኃፍታይ ገብረ እግዚአብሔር ናቸው፡፡

የቱሪዝም ዘርፉ ከማኅበራዊ ፋይዳው ይልቅ ወደ ኢኮኖሚዊ ዕድገት ሽግግር ያደገበት ሁኔታ መፈጠሩን የተናገሩት ኃላፊው፣ ይህንንም ዘርፍ በአግባቡ መጠቀምና በመንከባከብ የተሻለ ዕድገት ማስመዝገብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ከተማ የዓለም ቱሪዝም ከተሞች ፌዴሬሽን አባል መሆን እንደቻለች ገልጸው፣ ዘንድሮም የሚከበረው የዓለም የቱሪዝም ቀን ከመሠረተ ልማት፣ ከአካባቢ ጥበቃ እንዲሁም ከብዝኃ ሕይወት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ጉዳዮችን እንዲካተቱ በማድረግ መሥራት አንደሚያስፈልግ አስታውሰዋል፡፡

አዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝምም ቢሮ በዓለም ለ44ኛ በኢትዮጵያ ደግም ለ36ኛ ጊዜ ‹‹አረንጓዴ ልማት ለቱሪዝም፣ ቱሪዝም ለአረንጓዴ ልማት›› በሚል መሪ ቃል ከተማ አቀፍ የቱሪዝም ሳምንት ከጥቅምት 20 እሰከ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ለማክበር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

ቢሮው የዓለም የቱሪዝም ቀንን ለማክበር በርካታ ዝግጅቶችን ያጠናቀቀ ሲሆን፣ በወቅቱም የንግድና ሥራ ዕድል ፈጠራ ትርዒት፣ የጎዳና ላይ ትርዒት፣ የጥያቄና መልስ ውድድር፣ የበጎ አድራጎት ተግባርና ሌሎች ፕሮግሞች የሚከናወኑ መሆናቸውን  ተገልጿል፡፡         

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...