Thursday, November 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምፖለቲካን ያላካተተው የሱዳናውያኑ የሰላም ንግግር

ፖለቲካን ያላካተተው የሱዳናውያኑ የሰላም ንግግር

ቀን:

በጦርነት እየተናጠ በሚገኝ አገር የሰላም ውይይት ማካሄድ እንዲህ በአንዴ የሚሳካ አይደለም፡፡ በተለይ በአፍሪካ አገሮች ውስጥ የሚነሱ የእርስ በርስ ጦርነቶችን በድርድር መፍታት በጥቂት ወራት የሚሳካ አይደለም፡፡ ለዚህም ደቡብ ሱዳን ጥሩ ማሳያ ናት፡፡

ደቡብ ሱዳን ከሱዳን ካርቱም ነጻ ከወጣች በኋላ ጥቂት ዓመታትም ሳትዘልቅ በመሪዎቹ መካከል የተፈጠረው የሥልጣን ሽኩቻ የአሪቱን ንፁኃን አርግፏል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2011 ከሱዳን ነፃ የወጣችው ደቡብ ሱዳን፣ ነፃነቷን ሳታጣጥም በ2013 ለገባችበት የእርስ በርስ ጦርነት መነሻ በፕሬዚዳንቱ ሳልቫ ኪርና በምክትላቸው ሪክ ማቻር መካከል የተፈጠረ አለመግባባት ቢሆንም፣ ሞቱ፣ ረሃቡና ስደቱ የረፈው ለሕዝባቸው ነው፡፡

ፖለቲካን ያላካተተው የሱዳናውያኑ የሰላም ንግግር | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
በበሱዳን ከ30 በላይ ሆስፒታሎች በጦርነቱ ተጎድተዋል
(አሶሽየትድ ፕሬስ)

 

በአገሪቱ ሰላም ለማምጣት መሪዎቹን በተለያዩ ጊዜያት ለማደራደር፣ ተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደርሱ ለማስቻል ተደጋጋሚ ውይይቶች ተደርገው ነበር፡፡ ሆኖም አልተሳኩም፡፡ ለስድስት ዓመታት ያህል ዛሬ የተደረሰ ስምምነት ነገ ሲፈርስ፣ ሲካካዱና ሲጠቋቆሙ፣ በጎሳ ለይተው ሕዝባቸውን ሲያጫርሱም ከርመው ከስምምነት ደርሰዋል፡፡

በዚህ መሀል ደግሞ ከ383 ሺሕ በላይ ደቡብ ሱዳናውያን መሞታቸውን የሄልዝ ኢን ሂዩማኒተሪያን ክሪያሲስ ሴንተር እ.ኤ.አ. በ2018 ያወጣው መረጃ ያሳያል፡፡

በሱዳኑ የሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ጄኔራል አብዱል ፈታህ አልቡረሃንና ፈጥኖ ደራሽ ሃይሉን በሚመሩት ጄኔራል መሐመድ ሃምደን ዳጋሎ መካከል ዓምና በሚያዝያ የተጀመረው ጦርነትም፣ በድርድር እንዲፈታ ጥረት ቢደረግም፣ ገና መቋጫ አላገኘም፡፡

ሰባት ወራት ባስቆጠረው ጦርነት ደግሞ ከዘጠኝ ሺሕ በላይ ሱዳናውያን ተገድለዋል፡፡ 5.6 ሚሊዮን ከቀያቸው ሲፈናቀሉ፣ ከ12 ሺሕ በላይ ዜጎቻቸው ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ እንመራቸዋለን የሚሉት ደግሞ እያዋጉም እየተደራደሩም ነው፡፡

የሱዳን አንዳንድ አካባቢዎች በጦርነቱ የወደሙ ሲሆን፣ አገሪቷ በኢኮኖሚም ሆነ በፖለቲካው ከባድ ቀውስ ውስጥ ገብታለች፡፡

አልጀዚራ እንደሚለውም፣ ሁለቱ በጦርነት የተጠመዱ ጄኔራሎች ሱዳንን አውድመዋታል፡፡

የሱዳንን የእርስ በርስ ጦርነት ለመቀልበስ አሜሪካና ሳዑዲ ዓረቢያ ዓምና በግንቦት በሁለቱ ተፃራሪዎች መካከል ውይይት ያስጀመሩ ቢሆንም፣ ሰላምን አላመጣም፡፡

ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ከአሜሪካና ከሳዑዲ ዓረቢያ በተጨማ እንደ አፍሪካ ኅብረት ሆነው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) ተወካዮች በተገኙበት ውይይት የተደረገ ቢሆንም፣ ሰላም ለማምጣት ብዙም ተስፋ የማይጣልበት እንደሆነም የአልጀዚራ ዘገባ ያሳያል፡፡

ጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በጅዳ የተደረገው ውይይት፣ በዋናነት ተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲመቻችና ሰፋ ያለ የሰላም ውይይት እንዲደረግ በሚሉት ላይ ያተኮረም ነበር፡፡

ይህ የሰው ሞትን ለጊዜው ገታ ያስደርግ እንደሆነ እንጂ ሁለቱም ጎራዎች ለሚመኙት ሥልጣን ሲሉ የገቡበትን ጦርነት፣ በዘላቂነት የሚያስቆም አይደለም፡፡ ምክንያቱም አሜሪካ በሱዳን የሲቪል አመራር ወደ ሥልጣን መምጣት አለበት ለሚለው ሐሳብ ስለምታደላ፣ የፖለቲካ ውይይት ወደ ጠረጴዛ ሳይመጣ ቀርቷል፡፡

ከዚህ ቀደም ለሳምንት የዘለቀ ውይይት ተደርጎ የሰብዓዊ ዕርዳታ ለማድረስ በሚል የተኩስ አቁም እንዲደረግ የተደረሰው ስምምነት መፍረሱ ይታወሳል፡፡

ሱዳንን ለሠላሳ ዓመታት የመሯት የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አል በሽር በሚያዝያ 2011 ዓ.ም. በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ሱዳናውያን ሰላም አላገኙም፡፡

በሽር ከሥልጣን እንዲወርዱ ምሁራንን ጨምሮ የተለያዩ የሲቪል ማኅበረሰብ አባላት፣ የዴሞክራሲ አቀንቃኞች፣ ፖለቲከኞችና መከላከያው የተሳተፉበት አብዮት ቢካሄድም፣ ዛሬም ሱዳናውያን በሲቪል መንግሥት እንተዳደር የሚለው ጥያቄያቸው አልተመለሰም፡፡

በሽር ከሥልጣን ከተነሱ ማግሥት ጀምሮ በሱዳን መከላከያና በሲቪሎች በኩል የነበረው ሽኩቻ፣ ሱዳን በሁለቱ ጥምረት እንድትመራ፣ ጥምር የሽግግር መንግሥቱም አጠቃላይ ምርጫ አድርጎ በሱዳን የሲቪል መንግሥት ሥልጣን እንዲቆጣጠር እንዲያደርግ ከስምምነት ተደርሶ የነበረ ቢሆንም፣ አልተሳካም፡፡

‹‹የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት አልበሽርን በመገርሰስ የተጀመረው አብዮታችን ግቡን እስኪመታ ድረስ ተቃውሟችን ይቀጥላል፤›› የሚሉት ሲቪሎች፣ ነፃነትና ሰላም፣ ፍትሕ፣ ሲቪል አገዛዝ እንዲሰፍንና መከላከያው ወደ ካምፑ እንዲገባ እንደሚፈልጉ ሲወተውቱ ቢከርሙም፣ ይህ ምላሽ ሳያገኝ ቀርቶ ሱዳን ዘሬ ላይ የርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ትገኛለች፡፡

የሱዳን መከላከያን በሚመሩት የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃንና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን በሚመሩትና ሄሜቲ በሚል ስማቸው በሚታወቁት ጄኔራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ መካከል ሚያዝያ 7 ቀን 2015 ዓ.ም. የተጀመረው ጦርነት ሱዳንን የጦር አውድማ አድርጓታል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...