Wednesday, December 6, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜና‹‹ከሦስት የወለጋ ዞኖች ለተፈናቀሉ ዜጎች ለሦስት ዓመታት ከመንግሥትም ሆነ ከለጋሽ ድርጅቶች ምንም...

‹‹ከሦስት የወለጋ ዞኖች ለተፈናቀሉ ዜጎች ለሦስት ዓመታት ከመንግሥትም ሆነ ከለጋሽ ድርጅቶች ምንም ዓይነት ዕርዳታ አልቀረበም›› የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን

ቀን:

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ፣ ምሥራቅ ወለጋና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖችና በተለያዩ አካባቢዎች በግጭት ለተፈናቀሉ ዜጎች ላለፉት ሦስት ዓመታት በመንግሥትም ሆነ በለጋሽ ድርጅቶች ምንም ዓይነት ድጋፍ አለመቅረቡን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ፡፡

ኮሚሸኑ ከተፈናቃዮች አረጋገጥኩ ባለው መሠረት መፈናቀሉ በስፋት ከተከሰተበት ከ2013 ዓ.ም. እስከ 2015 ዓ.ም. መገባደጃ ድረስ በነበሩት ጊዜያት፣ ከመንግሥትም ሆነ መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የቀረበላቸው የምግብ ድጋፍ የለም፡፡

ኮሚሽኑ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ገለጹልኝ እንዳለው፣ ምንም እንኳን በተባለው ወቅት በመንግሥት በኩል ምግብ ነክና ሌሎች ድጋፎች ወደ አካባቢው ሲላክ የነበረ ቢሆንም፣ ድጋፉን በፀጥታ ችግር ምክንያት ማድረስ አለመቻሉንና በታጣቂዎች መንገድ ላይ መዘረፉን ጠቁሟል።

መጀመሪያ አካባቢ በዞኖቹና በወረዳ ደረጃ በሚገኙ የመንግሥት አስተዳደር አካላት፣ በአካባቢ ማኅበራት፣ በአገራዊና በዓለም አቀፍ በጎ አድራጊ ድርጅቶች በተወሰነ ደረጃ ሰብዓዊ ድጋፎች ለተፈናቃዮቹ ሲደረግላቸው የቆዩ ቢሆንም የሚቀርበው የምግብ ድጋፍ በቂ፣ ተደራሽና ወቅቱን የጠበቀ አለመሆኑን አክሎ ገልጿል፡፡

ከተቀባይ ማኅበረሰቦች ጋር የሚኖሩና በየከተማው የቀበሌ አዳራሽና ለማኅበራት የንግድ ሥራ አገልግሎት በተገነቡ የቆርቆሮ ጥላ ሥር ተጠልለው ለሚገኙ ተፈናቃዮች፣ ለዓመታት በአካባቢው በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎችና በታጣቂ ኃይሎች መካከል ሲከሰቱ በነበሩ ግጭቶች ምክንያት መቅረብ የነበረበት የሰብዓዊ ድጋፍ ተስተጓጉሎ መቆየቱን ኮሚሽኑ በመግለጫው አትቷል፡፡

በተጨማሪም በሰላም ዕጦት የተነሳ በየአካባቢው የሚገኙ ማኅበረሰቦችና ተፈናቃዮች የግብርና ሥራ ማከናወን ሳይችሉ በመቅረታቸው፣ ለከፋ የምግብ እጥረት መጋለጣቸውን ማረጋገጥ እንደቻለ አስታውቋል፡፡

በአፋር ክልል ከ800,000 በላይ የምግብ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች እንዳሉ የክልሉ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራርና ምግብ ዋስትና ለኮሚሽኑ መግለጹን ያስታወቀ ሲሆን፣ ከ120,000 በላይ የሚሆኑት በምግብ እጥረት የተጠቁ እናቶችና ሕፃናት ናቸው ብሏል፡፡

ኮሚሽኑ የትግራይ ክልል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ቢሮ ኃላፊዎች በደብዳቤ አሳወቁኝ እንዳለው፣ በአምስት ከተሞች በሚገኙት 53 የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያዎች እንደ ናሙና ተወስዶ በተደረገ ጥናት፣ በሌሎች ምክንያቶች የሞቱትን ሰዎች ሳያጨምር ቢያንስ 1,329 ተፈናቃዮች በምግብ እጥረት ብቻ መሞታቸውን አስታውቋል፡፡

ኢሰመኮ የፌዴራል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አሳወቀኝ ባለው መረጃ የተሟላና በቂ ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ቢኖርም፣ ባለፉት ወራት በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ላሉ ተፈናቃዮች በሁለት ዙር በአፋር 96 በመቶ፣ በጋምቤላ 96 በመቶ፣ በትግራይ 87 በመቶ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ 73 በመቶ፣ በሶማሌ 52 በመቶ፣ በአማራ 43 በመቶ የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎት መሸፈን መቻሉን ገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...