Thursday, December 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአገር ውስጥ ምርቶች ብቻ የሚቀርቡበት ‹‹የእኛ ምርት›› አውደርዕይ

የአገር ውስጥ ምርቶች ብቻ የሚቀርቡበት ‹‹የእኛ ምርት›› አውደርዕይ

ቀን:

የአገሪቱን ኢኮኖሚ በዘላቂነት ሊደግፉ ከሚችሉ ዘርፎች መካከል አምራች ኢንተርፕራይዞች ይገኙበታል፡፡ ዘርፉን ለመደገፍም የተለያዩ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን የማሻሻልና የማዘጋጀት እንቅስቃሴዎች አሉ፡፡

በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አዘጋጅነት በዓመት ሁለቴ የሚከናወነው አውደርዕይ ዘርፉን ለማነቃቃት ከሚሠሩ ሥራዎች አንዱ ነው፡፡ በ2016 ዓ.ም. ከሚሰናዳው የመጀመርያው ዙርም ‹‹ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት›› በሚል መሪ ቃል ከታኅሳስ 3 እስከ 7 ቀን 2016 ዓ.ም. እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አስታውቋል፡፡

በአውደርዕዩ የአገር ውስጥ አምራች ኢንተርፕራይዞች፣ ዋና ዋና የመንግሥትና የልማት አጋር ድርጅቶች የሚሳተፉበት እንደሆነ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር አለባቸው ንጉሤ (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡

ዳይሬክተሩ ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም. በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት፣ ‹‹የእኛ ምርት›› የተሰኘው አውደርዕይ ዋና ዓላማ አምራች ኢንተርፕራይዞችን በምርት ትውውቅና ሽያጭ፣ በገበያ ትስስር፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በልምድና በመረጃ ልውውጥ የተሻለ አቅምን በመፍጠር የዘርፉን ፋይዳ አጉልቶ ማሳየት የሚያስችል መድረክ መፍጠር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡   

ለአምራች ዘርፉ ምቹ የአሠራር ሥርዓትን ለመዘርጋት፣ የአገር በቀል አምራቾችን ቁጥር ለማሳደግ፣ የነባሮችንም የማምረት አቅም ለማጠናከር እንዲሁም የአገር ውስጥ ምርቶችን ተፈላጊነት ለመጨመር የሚያስችል እንደሚሆን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ በአውደርዕዩ ከመላ አገሪቱ የተውጣጡ ከ100 በላይ አምራቾች እንደሚሳተፉ ተገልጿል፡፡

የጨርቃጨርቅና አልባሳት የፕላስቲክ፣ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች፣ የአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ የኬሚካል ውጤት አምራቾች፣ የማዕድንና ጌጣጌጥ ውጤቶች እንዲሁም የእንጨትና ብረታብረት ውጤት አምራቾች በአውደርዕዩ ከሚሳተፉ አምራች ድርጅቶች መካከል እንደሚገኙበት አለባቸው (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

‹‹የእኛ ምርት›› ኤግዚቢሽንና ባዛር ዘላቂ የንግድ ትስስርን ለመፍጠርና የምርት ዕድገትን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ማኅበረሰቡ በአገር ውስጥ ምርት እንዲኮራና ትኩረት ሰጥቶ እንዲሸምት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የሚያስችል መድረክ እንደሚሆን አብራርተዋል፡፡

የአገር ውስጥ አምራች ኢንተርፕራይዞችን በአንድ መድረክ በማሰባሰብ ከተጠቃሚው ኅብረተሰብ ጋር እንዲሁም ከአጋር ተቋማት ጋር የገበያ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል መድረክ ነው ያሉት አለባቸው (ዶ/ር)፣ ልምድና ተሞክሮዎችን ለመጋራትና አምራች ድርጅቶች የደረሱበት የቴክኖሎጂ ዕድገት ለመመልከት ያስችላል ብለዋል፡፡

በተጨማሪ በአምራች ዘርፉ የተሰማሩና ለመሰማራት በጥናት ላይ የሚገኙ የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በዘርፉ ስለሚታዩ ተግዳሮቶች እንዲሁም በቀጣይ የዕድገት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ይደረጋል ሲሉ አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...