Thursday, November 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምየአፍሪካ አገሮች ብድር ያገኙበት የሳዑዲ ዓረቢያና አፍሪካ ጉባዔ

የአፍሪካ አገሮች ብድር ያገኙበት የሳዑዲ ዓረቢያና አፍሪካ ጉባዔ

ቀን:

የራሳቸውን ሀብት በአግባቡ መጠቀም ያልቻሉትና ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የማኅበራዊ መረጋጋቶችን በየአገራቸው ማስረፅ የተሳናቸው የአፍሪካ አገሮች፣ ከምዕራባውያኑ፣ ከምሥራቁና ከመካከለኛው ምሥራቅ ኃያላን አገሮች አየር ንብረት ለውጥን፣ ኢኮኖሚንና ሌሎች ዘርፎችን አስመልክተው የተለያዩ ጉባዔዎችን ያካሂዳሉ፡፡

የሩሲያ አፍሪካ ጉባዔ፣ የአሜሪካ አፍሪካ ጉባዔ፣ የቻይና አፍሪካ ጉባዔና የአፍሪካ አውሮፓ ኅብረት ጉባዔዎች በየወቅቱ ከሚከናወኑ ስብሰባዎች የሚጠቀሱ ሲሆን፣  ባለፈው ሳምንት ደግሞ የአፍሪካ አገሮች መሪዎች ከሳዑዲ ዓረቢያ አቻቸው ጋር በሳዑዲ ዓረቢያ ሪያድ በኢኮኖሚያዊ፣ በማኅበራዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

የሰሞኑ የሳዑዲ ዓረቢያ አፍሪካ ጉባዔም የፖለቲካና የኢኮኖሚ ግንኙነቶችን ለማጠናከር ያለመ እንደሆነ አፍሪካ ቢዝነስ በድረ ገጹ ሲያሠፍር፣ አፍሪካ የዓለም ሀብታም አገሮች የውድድር ሜዳ መሆኗንም ጠቁሟል፡፡

ጉባዔው ትኩረት ከሰጠበት አጀንዳዎች አንዱ፣ ለአፍሪካ አገሮች ለልማት የሚውል የገንዘብ ብድር ማግኘት ሲሆን፣ በዚህም 12 የአፍሪካ አገሮች የብድር ተጠቃሚ ለመሆን ስምምነት አድርገዋል፡፡

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ከሁለት ቢሊዮን ሪያል (ከ533 ሚሊዮን ዶላር) በላይ የብድር ስምምነትም ከአገሮቹ ጋር ተፈራርሟል፡፡

ዓረብ ኒውስ በድረ ገጹ እንዳሠፈረው፣ ከብድር ስምምነቱ በተጨማሪ የእስላማዊ ልማት ባንክና የነዳጅ ላኪ አገሮች ድርጅት እ.ኤ.አ. በ2030 ለአፍሪካ አገሮች ልማት የሚውል 50 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል፡፡

በሳዑዲ ዓረቢያ ልማት ፈንድ (ኤስኤፍዲ) በኩል ለአፍሪካ አገሮች የተሰጠው ብድር በኃይል፣ በትምህርት፣ በመንገድ በትራነስፖርትና በጤና ዘርፍ ለሚሠሩ የልማት ሥራዎች የሚውልም ይሆናል፡፡

ኤስኤፍዲ የብድር ስምምነት የፈጸመውም ከአንጎላ፣ ከቡርኪናፋሶ፣ ከቤኒን፣ ከብሩንዲ፣ ከኬፕቨርዲ፣ ከጊኒ፣ ከማላዊ፣ ከሞዛምቢክ፣ ከኒጀር፣ ከሩዋንዳ፣ ከሴራሊዮንና ከታንዛኒያ ጋር ነው፡፡

ጊኒ የእናቶችና የሕፃናት ሆስፒታል ለመገንባትና በቁሳቁስ ለማሟላት 75 ሚሊዮን ዶላር፣ በሴራሊዮን የሪያድ ሪፈራል ሆስፒታል ግንባታ 50 ሚሊዮን ዶላር፣ በኒጀር በተለያዩ አካባቢዎች ለሴቶች ለሚገነቡ ሁለተኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤቶች 28 ሚሊዮን ዶላር፣ በቤኒን ከፍተኛ የመምህራን ኮሌጅና የሳይንስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመገንባት 40 ሚሊዮን ዶላር ብድር አግኝተዋል፡፡

ቡሩንዲ ቡጁምቡራ የሚገኘውን የንጉሥ ካሊድ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል መልሶ ለማቋቋም 50 ሚሊዮን ዶላር፣ ቡርኪናፋሶ ማንጋ ሆስፒታል ሁለተኛ ዙር ግንባታ 17 ሚሊዮን ዶላር፣ ኬፕቨርዴ የውኃ ገብ ቦታዎችን ለማልማት 17 ሚሊዮን ዶላር ብድር አግኝተዋል፡፡

አንጎላ 100 ሚሊዮን ዶላር፣ ሩዋንዳ 20 ሚሊዮን ዶላር፣ ማላዊ 20 ሚሊዮን ዶላር፣ ሞዛምቢክ 50 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ታንዛኒያ 13 ሚሊዮን ዶላር ብድር ማግኘታቸውን ዓረብ ኒውስ አሥፍሯል፡፡

ብድር ካገኙ አገሮች በተጨማሪ በትብብር አብረው ለመሥራት የሚያስችሉ የመግባቢያ ሰነዶችም ተፈርመዋል፡፡ ናይጄሪያ በነዳጅና ጋዝ ዘርፍ፣ ኢትዮጵያ፣ ሴኔጋልና ቻድ በኃይል ዘርፍ፣ ግብፅ ገንዘብ ነክ ውይይት ለማድረግ፣ በጋምቢያ ተደራራቢ የግብር አከፋፈልንና ማጭበርበርን ለማስቀረትና በሩዋንዳ የነዳጅ ፕሮግራምን የተመለከቱ ፕሮጀክቶችን አስመልክቶ በትብብር ለመሥራት የሚያስችሉ የመግባቢያ ሰነዶች ፈርመዋል፡፡

ከመካከለኛው ምሥራቅና ከአፍሪካ የ50 አገሮች መሪዎች የመከሩበት ጉባዔ ዓላማ፣ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ከአፍሪካ ኅብረት ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ሲሆን፣ የሳዑዲ ዓረቢያ የገንዘብ ሚኒስትር መሐመድ ዓሊ ጃዳን እንዳሉትም፣ አገራቸው በአፍሪካ ለዲፕሎማሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ትኩረት ሰጥታለች፡፡

ሳዑዲ ዓረቢያ በአፍሪካ በተለያዩ ዘርፎች በ47 አገሮች 10.7 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ከ400 በላይ ፕሮጀክቶች ላይ በትብብር እየሠራች መሆኑን፣ ለወደፊቱም የዓለም ኢኮኖሚ ምኅዋር ከሚሆነው ከአፍሪካ አኅጉር ጋር ግንኙነታቸውን እንደሚያጠናክሩ አክለዋል፡፡ የሳዑዲ ዓረቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን በመሩት በዚሁ ጉባዔም፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አገራቸው በአፍሪካ አገሮች ጋር የተዋዋለችውን የሁለት ቢሊዮን ሪያል የብድር ስምምነት እንደ ማሳያ አንስተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...