Thursday, November 30, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

[ጉባዔው በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ክቡር ሚኒስትሩን ለመጠየቅና ምላሽና ማብራሪያቸውን ለማድመጥ ተሰብስቧል። የጉባዔው አባላትም ማብራሪያ የሚሹ ጥያቄዎቻቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

 • ክቡር ሚኒስትር፣ ይህ ጉባዔ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ለመስጠት በመካከላችን ስለተገኙ አመሰግናለሁ።
 • ክቡር ሚኒስትር፣ ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት የብሪክስ አባል እንድትሆን የሰጡት በሳል አመራር የሚደነቅ ነው።
 • አገራችን የብሪክስ አባል ሆና የተመረጠችበት መንገድም ታሪክ የማይረሳው ነው።
 • ክቡር ሚኒስትር ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል እንድትሆን ለሰጡት በሳል አመራር ክብር ይገባዎታል።
 • በመሆኑም ይህ ጉባዔ ክቡር ሚኒስትሩ ለሰጡት በሳል አመራር ያለውን ክብር እንዲገልጽኝ እጠይቃለሁ።

[ጉባዔው አጨበጨበ]

 • ክቡር ሚኒስትር ለዚህም ክብር ይገባዎታል።
 • ጉባዔው ክቡር ሚኒስትሩ ለሰጡት በሳል አመራር ያለውን ክብር በደማቅ ሁኔታ ስለገለጸ አመሰግናለሁ።
 • በመቀጠልም ጥያቄዬን በቀጥታ ለክቡር ሚኒስትራችን አቀርባለሁ።
 • ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሆና መመረጧ የሚያስገኛቸው ፋይዳዎች ምንድናቸው? ማብራሪያ ቢሰጡበት።
 • ጥያቄ አቅራቢው እንደገለጹት አገራችን ብሪክስን መቀላቀሏ ትልቅ ድል ነው። ብሪክስን መቀላቀላችን የሚያስገኘውን ፋይዳ ደግሞ በጋራ የምናየው ይሆናል።

[ጉባዔውን የሚመሩት ሰብሳቢ ለሌላ ጥያቄ አቅራቢ ዕድል ሰጡ]

 • አመሠግናለሁ ክቡር ሰብሳቢ…
 • ክቡር ሚኒስትር ለዘመናት የበቀለው የነጠላ ትርክት የአገሪቱን የፖለቲካ ምኅዳር አጣሞታል። በዚህም ዜጎች ለመኖር ብቻ ሳይሆን ወጥቶ ለመግባት ጭምር እየተቸገሩ ነው።
 • ይህንን የተጣመመ የፖለቲካ ምኅዳር ለማስተካከል መንግሥት የብሔራዊነትና የአርበኝነት ትርክትን መገንባት ፍቱን መድኃኒት ነው ብሎ እንደሚያምን ተገልጿል።
 • ክቡር ሚኒስትር ለመሆኑ መንግሥት ብሔራዊነት ሲል ምን ማለቱ ነው?
 • ከብሔርተኝነት የተለየ ነው ወይስ ተመሳሳይ ትርጉም አለው?
 • ለቀረበው ጥያቄው አመሰግናለሁ።
 • ሁላችሁም እንደምታውቁት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 69 ላይ ፕሬዚዳንቷ ወይም ፕሬዚዳንቱ የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ነው ይላል። አይደለም?
 • ትክክል ነው።
 • ወይም ደግሞ እናንተ ራሳችሁ በዚሁ ጉባዔ ላይ ሌሎች የአገሪቱ ባንኮችን የሚቆጣጠር ብሔራዊ ባንክ በአዋጅ እንዲቋቋም ወስናችኋል። አይደለም?
 • ትክክል ነው።
 • ወይም ደግሞ ብሔራዊ ሎተሪ የሚባል ተቋም አቋቁማችኋል። አይደለም?
 • አዎ።
 • ብሔራዊነት ማለት እንደዚያ ነው። ብሔራዊ ሎተሪ ማለት ነው።
 • ብሔራዊ ሎተሪ የአንድ ብሔር ነው እንዴ?
 • አይደለም።
 • ስለዚህ እኛም ብሔራዊነት ስንል የአንድ ብሔር ማለታችን አይደለም።
 • ወይም እንደሚጠረጠረው ዘውዳዊ ማለታችን አይደለም።
 • ስለዚህ በዚሁ መንገድ ብትረዱት ጠቃሚ ይመስለኛል።

[የጉባዔው ሰብሳቢ ለሌላ ጥያቄ አቅራቢ ዕድል ሰጡ]

 • አመሠግናለሁ ክቡር ሰብሳቢ፡፡
 • ክቡር ሚኒስትርም ለጥያቄዎቻችን ምላሽ ለመስጠት በመካከላችን ስለተገኙ እያመሠገንኩ ወደ ጥያቄዬ አልፋለሁ።
 • ክቡር ሚኒስትር ሰው ሠራሽ አስተውሎት ካለው ፋይዳ በተጨማሪ ዓለም አቀፋዊ ችግር እየሆነ መምጣቱን በቅርቡ የአመራሮች ሥልጠና ላይ ከሰጡት ማብራሪያ ለመረዳት ችለናል።
 • ክቡር ሚኒስትር ሰው ሠራሽ አስተውሎት በአገራችን ላይ ሊፈጥር የሚችለውን ችግር በመረዳት ለሰጡት በሳል አመራር ክብር ይገባዎታል።
 • ሰው ሠራሽ አስተውሎት የሚፈጥረውን ችግር የሚከላከል አገራዊ አቅም በእርስዎ መሪነት እየተገነባ መሆኑ ይታወቃል።
 • ክቡር ሚኒስትር ሰው ሠራሽ አስተውሎት የሚፈጥረውን ችግር ለመከላከል እየተደረገ ካለው ጥረት ጎን ለጎን መንግሥት ሰው ሠራሽ የኑሮ ውድነትን ለመፍታት ያሰበው ነገር ካለ ቢገለጽ?
 • ሰው ሠራሽ አስተውሎ በእንግሊዘኛ ስያሜው artificial intelligence ወይም በምኅፃረ ቃሉ AI ይባላል።
 • ሰው ሠራሽ የኑሮ ውድነት ማለትም Artificial Inflation በምኅፃረ ቃሉ AI መሆኑ ያመሳስላቸዋል።
 • ነገር ግን ሁለቱም AI ስለሆኑ አንድና ያው ናቸው ማለት አይደለም።
 • ሰው ሠራሽ አስተውሎት በጥንቃቄ ከተጠቀምንበት አገር የመቀየር ዕድል አለው።
 • ሰው ሠራሽ የኑሮ ውድንትም መጎሳቆልን የሚያስከትል ብቻ ሳይሆን ቁጭት የሚፈጥር በመሆኑ ይህንን ቁጭት ከተጠቀምንበት አገር የመለወጥ ዕድል አለው።
 • ለምሳሌ የስንዴ ምርት ዕጥረት የፈጠረው ቁጭት ዛሬ ላይ አገራችን በስንዴ ምርታማነት በአፍሪካ ደረጃ እንድትጠቀስ አድርጓታል።
 • ስለዚህ ሰው ሠራሽ የኑሮ ውድነት ቁጭት ሊፈጥርብን ይገባል።
 • የግብይት ሥርዓቱን ተደራሽ ማድረግ ሰው ሠራሽ የኑሮ ውድነት ችግር ለመቅረፍ ፍቱን መፍትሔው ነው ብሎ መንግሥት ያምናል።
 • በመሆኑም በየአካባቢዎቹ የእሑድ ገበያ እያቋቋመ ይገኛል።

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...

ሀብቱንና ትርፉን እያሳደገ የቀጠለው አዋሽ ባንክ

አዋሽ ባንክ በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ዋና መሥሪያ ቤት...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸማቸውን ለተከበረው ምክር ቤት ካቀረቡ በኋላ ከምክር ቤቱ አባላት የሚነሱ ጥያቄዎችን እየተቀበሉ ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው]

ክቡር ሚኒስትር መንግሥት ለሕዝብ ይፋ ያደረገው ነገር ከምን እንደደረሰ ቢያብራሩልን? ምንድነው ይፋ ያደረገው? ጥያቄውን ትንሽ ቢያብራሩት? ከአራት ዓመት በፊት በኦጋዴን አካባቢ ነዳጅ መገኘቱን ለሕዝብ በቴሌቪዥን አብስሮ...

[ክቡር ሚኒስትሩ አንድ የካቢኔና የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ አባል የሆኑ ከፍተኛ አመራር የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያደመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረግህ፣ ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...

[ክቡር ሚኒስትሩ ለሚመሩት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ተጠሪ የሆነው ተቋም የዋና ሥራ አስኪያጅና ለእሳቸውም የቅርብ ወዳጅ የሆኑትን ግለሰብ ቢሯቸው አስጠርተው ከበላይ አካል እንዲሰጡ የታዘዙትን ደብዳቤ...

የምን ደብዳቤ ነው ክቡር ሚኒስትር? ከበላይ አካል የተወሰነ ነው። የምን ውሳኔ ነው? እስኪ ተመልከተው። እሺ... አዋከብኩዎት አይደል .... ምን? ምንድነው ክቡር ሚኒስትር? ከሥራ መሰናበትዎን ስለማሳወቅ ነው እኮ የሚለው፡፡ እኔም...