Thursday, November 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናሐሰተኛ ሰነድ የያዙ የውጭ ዜጎችና ዕግድ የተጣለባቸው 560 ዜጎች መያዛቸው ተገለጸ

ሐሰተኛ ሰነድ የያዙ የውጭ ዜጎችና ዕግድ የተጣለባቸው 560 ዜጎች መያዛቸው ተገለጸ

ቀን:

ሐሰተኛ ሰነድ የያዙ የውጭ ዜጎችና ከአገር እንዳይወጡ ዕግድ የተጣለባቸው 560 ዜጎች በኬላ በኩል ሊወጡ ሲሉ መያዛቸውን፣ የኤሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት አስታወቀ፡፡

አገልግሎቱ ይህንን ያስታወቀው ዓርብ ኅዳር 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ከፓስፖርትና ከልዩ ልዩ አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ፣ ባለፉት ሦስት ወራት የተከናወኑ አፈጻጸሞችና የተወሰዱ ዕርምጃዎችን ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሲሰጥ ነው፡፡

የኤሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ በሦስት ወራት ውስጥ ሐሰተኛ ሰነድ የያዙ የውጭ አገር ዜጎችና ከአገር እንዳይወጡ ዕግድ የተጣለባቸው 560 ሰዎች በኬላ በኩል ሊወጡ ሲሉ መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡

አገልግሎቱ የማያውቃቸውና ተመሳስለው የተሠሩ ሰነዶችን ይዘው ከአገር ሊወጡ ሲሉ መያዛቸውን፣ ይህም የተከሰተው በሦስት ወራት ውስጥ በተደረገ ክትትልና ቁጥጥር መሆኑን ዋና ዳይሬክተሯ አስረድተዋል፡፡

ከተያዙት ውስጥ በርካታ የውጭ ዜጎች መሆናቸውን፣ ተቀባይነት የሌለው መታወቂያ (ሰነድ) ይዘው መገኘታቸው የተለመደ መሆኑንና ይህ አካሄድ አደገኛ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ የውጭ ዜጎች ሕጋዊነታቸው ሳይረጋገጥ እየሠሩ እንደሚቆዩ፣ ከአገር ሊወጡ ሲሉ ግን መኖራቸው እንደሚታወቅ ተናግረዋል፡፡

ከፍተኛ ቁጥጥር ሲደረግ በሕጉ መሠረት እየተቀጡ ሕጋዊ እንዲሆኑ ማድረግ፣ ከተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ጋር የተያዙት ደግሞ ከአገር እንዲወጡ እንደሚደረጉ ዋና ዳይሬክተሯ አስረድተዋል፡፡

በድንበር ኬላ ላይ የተያዙት 560 ግለሰቦች ሐሰተኛ ሰነድ የያዙ፣ ዕግድ ያለባቸውና በሌሎች ሕገወጥ ድርጊቶች ተሠማርተው የተገኙ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአገልግሎቱ በሦስት ወራት ውስጥ 531,800 ፓስፖርቶች ታትመው ወደ አገር ውስጥ መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡

በሦስት ወራት ውስጥ 350,000 ያህል ፓስፖርት ፈላጊዎች እንደነበሩ፣ አሁን  ግን 190,000 ያህሉን ፍላጎት ማሟላት መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

‹‹እስከ ታኅሳስ መጨረሻ የታቀደው የፓስፖርት ጥያቄዎችን ሙሉ በሙሉ መመለስ እንችላለን ተብሎ ነው፤›› ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ፣ እየገባ ያለው የፓስፖርት መጠን ከሚጠየቀው በላይ በመሆኑ ችግሩ እንደሚፈታ ተናግረዋል፡፡

የፓስፖርት ዕደላውን በቀን ከ7,000 እስከ 10,000 ለሚደርሱ ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ፣ የተለያዩ ማሽኖች ከውጭ እየገቡ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡  

ከውጭ ከገቡት ፓስፖርቶች የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚሰጣቸውና አገልግሎት ለማግኘት ከተመዘገቡ ረዥም ጊዜያት ላስቆጠሩ ፈላጊዎች የፓስፖርት ዕደላ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመጀመሪያው ዙር ቅድሚያ የተሰጣቸው የአዲስ አበባ ከተማ 45,365 ፓስፖርት ፈላጊዎች መሆናቸውን አክለዋል፡፡

ፓስፖርታቸው የተዘጋጀላቸው ደንበኞች በአጭር የጽሑፍ መልዕክት በስልካቸው እንደዲርሳቸው በማድረግ 29,442 (64 በመቶ) እንዲወስዱ መደረጉንና ይሁን እንጂ መልዕክት ደርሷቸው ያልወሰዱ 15,921 (35 በመቶ) መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

አስቸኳይ ፓስፖርት የፈለጉ 15,793 ሰዎች በሦስት ወራት ውስጥ ፓስፖርት አግኝተዋል ብለዋል፡፡

በአጠቃላይ በአገር ውስጥ ለ69,659 ፓስፖርት ፈላጊዎች አገልግሎት መሰጠቱን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ፣ በውጭ አገሮች ለሚኖሩ ዜጎች እስካሁን በዲኤችኤል በኩል 33,083 ፓስፖርት መላኩን ተናግረዋል፡፡

በበይነ መረብ ፓስፖርት ፈላጊዎች ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት 7,448 ዜጎች አገልግሎቱን እንዳገኙ፣ በአጠቃላይ በውጭ አገሮች ከሚኖሩ የተለያዩ የፓስፖርት ዓይነቶች ፈላጊ ተገልጋዮች ለ40,531 ያህሉ ተልኳል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...