Tuesday, November 28, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የነዳጅ ኩፖንንና ሦስተኛ ወገን ኢንሹራንስን ዲጂታል ማድረግ የሚያስችል አሠራር ይፋ ተደረገ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ኢትዮ ቴሌኮም የነዳጅ ኩፖን ሽያጭ አገልግሎት አሠራርን ወደ ወረቀት አልባ ለመቀየርና የሦስተኛ ወገን የመድኅን አገልግሎት ክፍያን በዲጂታል የታገዘ ለማድረግ የሚያስችል አሠራር ይፋ ማደረጉን አስታወቀ፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ዓርብ ኅዳር 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በስካይ ላይት ሆቴል የዲጂታል ቴክኖሎጂውን ይፋ ያደረገው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴርና ከመንገድ ደኅንነትና ኢንሹራንስ ፈንድ አገልግሎት ኃላፊዎች በተገኙበት ወቅት ነው፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ በነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ ያሉ የአሠራር ክፍተቶችን ለማዘመን፣ እንዲሁም ግልጽነት ያለው የነዳጅ አቅርቦትና ግብይት ለማስፈን የዲጂታል ቴክኖሎጂ አስፈላጊ መሆኑን፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ተናግረዋል፡፡

የኢንሹራንስ አገልግሎት አሰጣጥ ተግዳሮቶችን ለማስቀረት፣ በተለይም የተማከለ መረጃ እንዲኖር ለማስቻል፣ እንዲሁም ክፍያን በወቅቱና በዲጂታል መንገድ ለማከናወንና ሌሎች መሰል ጉዳዮችን ተፈጻሚ ለማድረግ ያለመ አሠራር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ይህ የዲጂታል ሶሉውሽን ለኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሥራ ማስኬጃ ወጪዎችን ለመቀነስ፣ ተገልጋዮች የሚያደርጉትን ምልልስና ውጣ ውረድ ለማስቀረት፣ ባሉበት ሆነው በቀጥታ እንዲስተናገዱ ለማድረግ፣ በኢንሹራንስ ሒደቶች ውስጥ የሚከሰቱ ተግዳሮቶችን ለመቀነስ፣ እንዲሁም የዕድሳትና ባለቤትነት ለውጥ አሠራርን ዲጂታላይዝድ ለማድረግ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል የማንዋል የነዳጅ ኩፖን ሽያጭ አገልግሎት አሠራር ወደ ወረቀት አልባ የዲጂታል ኩፖን በመቀየር፣ አዲስ አሠራር ያስተዋወቀ ሲሆን፣ ይህም ዘመናዊ አሠራር የነዳጅ ኩባንያዎች የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን፣ የነዳጅ ማደያዎችን የአገልግሎት አማራጭ ለማሳደግና ግብዓቶችን ለማሳለጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡

ተቋሙም የዲጂታል ቴክኖሎጂን ይፋ ባደረገበት ወቅት እንዳስታወቀው፣ እስካሁን 1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ በቴሌ ብር ግብይት መፈጸም መቻሉን አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች