የኮሜዲያን ጃዝ ሳምንትን መሠረት አድርጎ እ.ኤ.አ. በ1992 የተጀመረው የኢኤፍጂ ጃዝ ፌስቲቫል በእንግሊዝ በሚገኙ 70 ሥፍራዎች ተከናውኗል፡፡
ከ100 ሺሕ በላይ ቀጥታ ተመልካቾች በሚገኙበትና ከወርኃ ጥቅምት ማብቂያ ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው የለንደን ጃዝ ፌስቲቫል፣ የዘርፉ ባለሙያዎች ከተለያዩ አገሮች ተሰባስበው ሥራቸውን የሚያቀርቡበትም ነው፡፡
ከዚህ ቀደም በተዘጋጁ ፌስቲቫሎች በመሳተፍ የኢትዮጵያን ጃዝ በማስተዋወቅ ‹‹የኢትዮጵያ የጃዝ አባት›› የሚል ስያሜን ያገኘው ሙላቱ አስታጥቄም፣ ዓርብ ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. በለንደን ላስ ፓልማስ፣ ማላጋንና ማድሪድ ሥራዎቹን አቅርቧል፡፡
(ፎቶ ከሙላቱ አስታትቄ ማኅበራዊ ትስስር ገጽ፣ ጀምስ አርበን)