Sunday, February 25, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ አንድ የካቢኔና የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ አባል የሆኑ ከፍተኛ አመራር የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያደመጡ ነው] 

 • ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት።
 • ጥሩ አደረግህ፣ ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው?
 • ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም ወሳኝ ያልናቸው ጉዳዮች በተቃራኒው ነው የሚፈጸሙት።
 • እህ…
 • በውስጣችን ሌላ መንግሥት አለ ወይ የሚል ጥያቄ እንዲፈጠርብኝ ጭምር እያደረገ ነው።
 • ምንድነው የተፈጠረው?
 • ክቡር ሚኒስትር እርስዎ፣ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ባሉበት ‹‹ኢትዮጵያ ታምርት›› የሚል ንቅናቄ ይፋ ማድረጋችንን ያስታውሳሉ አይደለም?
 • በትክክል።
 • በዚህ ንቅናቄ ጥሩ የሚባል ውጤት ማየት በጀመርንበት ወቅት ይህንን የሚያዛባ ተቃራኒ ተግባራት ውስጣችን ባሉ ባለሥልጣናት እየተፈጸመ ነው።
 • ለምን የተፈጠረውን ነገር መጀመሪያ አትነግረኝም?
 • ወደዚያ እየመጣሁ ነው ክቡር ሚኒስትር።
 • እሺ… ምን ተፈጠረ?
 • ‹‹ኢትዮጵያ ታምርት›› ስንል ከውጭ የምናስገባቸውን ዋና ዋና ምርቶች በአገር ውስጥ ለማምረት ነው።
 • አዎ።
 • በአገር ውስጥ የሚያመርቱ ባለሀብቶችን አስተባብረን ጥሩ ስኬት ማግኘት እንደጀመርን፣ እነዚህን ምርቶች ከውጭ በገፍ የሚያስገቡና ለዚህም ከመንግሥት ማበረታቻ የሚሰጣቸው ባለሀብቶች እንደ አሸን ፈልተዋል።
 • የምን ማበረታቻ ነው የሚሰጣቸው?
 • በማንና እንዴት እንደተወሰነ ሳይታወቅ ምርቱን የሚያስገቡ ባለሀብቶች ዶላር ቅድሚያ እንዲያገኙ ይደረጋል።
 • እሺ…?
 • ባንኮች ዶላር የለንም ካሉ ደግሞ ባለሀብቶቹ ውጭ አገር ያስቀመጡትን ዶላር ተጠቅመው ምርቱን እንዲያስገቡ ይፈቀዳል።
 • እንዴት?
 • በፍራንኮ ቫሉታ ማለት ነው።
 • ከተወሰኑ ምርቶች ውጪ ሌሎች በፍራንኮ ቫሉታ እንዳይስተናገዱ ወስነን አልነበር እንዴ?
 • ነበር።
 • እና እንዴት ይሆናል?
 • ይኼ ብቻ አይደለም እየሆነ ያለው ክቡር ሚኒስትር?
 • እ… ሌላ ምን ሆነ?
 • በፍራንኮ ቫሉታ የሚያስመጡት ባለሀብቶች ቀረጥና ታክስ ጭምር እየከፈሉ አይደሉም።
 • ይኼ እንዴት ይሆናል? በማን ውሳኔ?
 • በውሳኔ አይደለም ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ታዲያ እንዴት ነው የሆነው?
 • ባለሀብቶቹ የሚያስገቡትን ምርት በአነስተኛ ዋጋ እንደገዙት የሚገልጽ ሐሰተኛ ሰነድ እያቀረቡ ነው የሚስተናገዱት።
 • ምን?
 • ክቡር ሚኒስትር ምርቱን በነፃ ያገኙት እስኪመስል ድረስ በሳንቲም የሚገለጽ ዋጋ ነው የሚያቀርቡት፣ ግን ሐሰተኛ ደረሰኝ ነው ብሎ ውድቅ የሚያደርግባቸው የለም።
 • እንዴት?
 • ይኸው ነው ክቡር ሚኒስትር፣ በዚህ ደረጃ ነው ተናበው የሚሠሩት።
 • አንተ እንዴት ነው ይህንን ልትደርስበት የቻልከው?
 • ለምነን ያስገባናቸው ባለሀብቶች ቅሬታቸውን አቀረቡልኝ፣ በኋላም ሚዲያዎች ጭምር ሲዘግቡት ነገሩን ለማጣራት ወደ የሚመለከተው ተቋም በአካል ሄጄ ማብራሪያ ጠየቅኩኝ።
 • ምን ምላሽ አገኘህ?
 • በአንድ በኩል በፍራንኮ ቫሉታ ይስተናገዱ የሚል በመንግሥት ተቋም የተጻፈ ደብዳቤ ባለሀብቶቹ ይዘው በመቅረባቸው ነው ይላሉ።
 • እሺ…?
 • ምርቱን በሳንቲም ደረጃ እንደገዙት ገልጸው ያቀረቡት ሰነድ እንዴት ተቀባይነት እንዳገኘ ስጠይቅ ደግሞ አስገራሚ ምላሽ ነው የሰጡኝ።
 • ምን አሉ?
 • ታክስና ቀረጡ በዋናው መሥሪያ ቤት ሳይሆን በቅርንጫፍ እንደተስተናገደና ችግር ካለ እንደሚያጣሩት ነው የገለጹልኝ።
 • ጥሩ አድርገሃል።
 • ምኑን?
 • ችግሩን እንዲፈታ ያደረግከው ጥረት የሚበረታታ ነው።
 • ክቡር ሚኒስትር ችግሩ አልተፈታም እኮ?
 • ተፈታ አላልክም እንዴ?
 • ኧረ በጭራሽ፡፡
 • በፍራንኮ ቫሉታ የተስተናገዱት ደብዳቤ አቅርበው፣ ሐሰተኛ የግዥ ሰነዱንም እንደሚያጣሩት ነገረውኛል አላልክም?
 • አዎ፣ እሱን ብያለሁ።
 • ከማንም ትዕዛዝ ሳትጠብቅ ችግሩን ለመፍታት የሄድከው ርቀት የሚበረታታ ነው ያልኩህ ለዚያ ነው።
 • አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር።
 • እኔም በድጋሚ አመሠግናለሁ፣ የጀመርከውን ንቅናቄ አጠናክረህ ቀጥልበት።
 • የቱን ክቡር ሚኒስትር?
 • ‹‹ኢትዮጵያ ታምርት›› የሚለውን ንቅናቄ።
 • እሱ እንኳ የሚሆን አይመስለኝም ክቡር ሚኒስትር፣ ባይሆን ሌላ ብንጀምር ይሻላል።
 • ሌላ ንቅናቄ?
 • አይደለም።
 • እ…?
 • ግንባር፡፡
 • የምን ግንባር?
 • ኢትዮጵያ ታምርት ግንባር!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...

ሕወሓት በትግራይ ጦርነት ወቅት በፌዴራል መንግሥት ተይዘው ከነበሩት አባላቱ መካከል ሁለቱን አሰናበተ

በሕወሓት አባላት ላይ የዓቃቤ ሕግ ምስክር የነበሩት ወ/ሮ ኬሪያ...

የኤሌክትሪክ ኃይል ለታንዛኒያ ለመሸጥ የሚያስችል ስምምነት ለመፈጸም የመንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ለማከናወን የሚያስችለውን...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረክ። ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሞባይል ስልካቸው ላይ አተኩረው ሲመለከቱ ቆይተው፣ በድንገት ካቀረቀሩበት ቀና ብለው ባቤታቸውን ጠየቁ]

ምን ጉድ ነው የማየው? ምን ገጠመሽ? የመንግሥት ሚዲያዎች የሚያሠራጩት ምንድነው? ምን አሠራጩ? አልሰማህም? አልሰማሁም፣ ምንድነው? ዳግማዊ አፄ ምኒልክ መልዕከት አስተላለፉ እያሉ ነው እኮ። እ... እሱን ነው እንዴ? አዎ። የምታውቀው ነገር አለ? አዎ። የዓድዋ...

[ክቡር ሚኒስትሩ  የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላትን በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች እያዞሩ እያስጎበኙ ከአንድ ዲያስፖራ ጋር እየተወያዩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር የዛሬ ሁለት ዓመታት ገደማ ወደ አዲስ አበባ መጥቼ ከተማዋን ጎብኝቼ ነበር። እውነት? አዎ። ታዲያ ልዩነቱን እንዴት አዩት? በጣም ይደንቃል። ሌላ ከተማ እኮ ነው የመሰለችው። አይደል? አዎ። እንዴት ነው...