Sunday, February 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊሰላሳ በመቶ የገጠር መዳረሻዎች ከዋና መንገዶች ጋር አለመገናኘታቸው ተነገረ

ሰላሳ በመቶ የገጠር መዳረሻዎች ከዋና መንገዶች ጋር አለመገናኘታቸው ተነገረ

ቀን:

በኢትዮጵያ 30 በመቶ የገጠር መንገዶች ከዋና አውራ መንገዶች ጋር አለመገናኘታቸውን፣ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡  

ሚኒስቴሩ ይህንን ያስታወቀው ኅዳር 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ከሁሉም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮችና የከተማ አስተዳደሮች ጋር የገጠር ትስስር ተደራሽነት ፕሮግራም ላይ በነበረው የጋራ ውይይት ነው፡፡

ከዚህ ቀደም የገጠር ትስስር ተደራሽነት መንገድ ዝርጋታና ሁሉንም የገጠር ማዕከላት ከዋና አውራ መንገዶች ጋር ማገናኘት ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ ሲሠራ መቆየቱን፣ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ደኤታ ወንድሙ ሴታ (ኢንጂነር) ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ይሁን እንጂ የገጠር መንገዶች ትስስር ለመፍጠር የተለያዩ ሥራዎች ቢከናወኑም፣ 30 በመቶ የሚሆኑት አሁንም ከዋናው መንገዶች ጋር ትስስር እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡

እንደ ወንድሙ (ኢንጂነር) ገለጻ፣ የገጠር ትስስርና ተደራሽነት ፕሮግራም ከዚህ ቀደም ተግባራዊ ሲደረግ ትኩረት የተደረገው ተደራሽነት ላይ ብቻ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ዓላማ ሁሉንም የገጠር ማዕከላትን ከዋና መንገዶች ጋር ማገናኘት ቢሆንም፣ ከዚያም ባለፈ በርካታ ሥራዎች ተሠርተውም 30 በመቶ የሚሆኑት የገጠር ማዕከላት አሁንም ከዋና መንገዶች ጋር እንዳልተገኛኙ ሚኒስትር ደኤታው አስረድተዋል፡፡

በቅርቡ ተግባራዊ የሚደረገው የገጠር ትስስርና ተደራሽነት ፕሮግራም ዋናው ዓላማው፣ እስካሁን ተደራሽ ያልሆኑ ማዕከላትን ተደራሽ ማድረግና በዕቅድ የተያዙ 1,200 ስትራክቸሮችን (መሻገሪያዎች) መገንባት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በመጀመሪያው ፕሮግራም ለመገንባት ታቅደው ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ያልተገነቡ መንገዶች በአሁኑ ዕቅድ ለመገንባት መታሰቡን ወንድሙ (ኢንጂነር) ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ለፕሮግራሙ ክልሎች በጀት እንደማይመድቡና የተበጀተው ሀብት ለተለያዩ ጉዳዮች ይውል እንደነበር አስታውሰዋው፣ ይህም ፕሮግራሙን በታሰበለት ደረጃ ተፈጻሚ እንዲሆን አድርጓል ብለዋል፡፡

በገጠር የመንገድ ተደራሽነት ላይ በተከናወኑ ሥራዎች ምክንያት አገር አቀፍ የመንገድ ሽፋን ከፍ ማለቱን፣ ዜጎች ከሚኖሩበት አካባቢ ከዋና መንገዶች ያለውን ርቀት መቀነስ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ፕሮግራሙ የገጠር ማዕከላትን የሚያገናኝ ብቻ ሳይሆን፣ የግብርና ምርቶችና ማዕድናት ያሉባቸውን አካባቢዎችንና ሌሎች ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፋይዳ ያላቸውን ሥፍራዎች ተደራሽ ማድረግ ትልቅ ዓላማ ይዟል ብለዋል፡፡

ፕሮግራሙ ሁሉንም የገጠር አካባቢዎች ሳይሆን ከተመረጡ ወረዳዎች በተጨማሪ፣ እስካሁን መዳረሻ የሌላቸውን ለመገንባት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ለፕሮጀክቱ የገንዘብ ድጋፍ ያደረገው የዓለም ባንክ መሆኑን፣ የፌዴራል መንግሥትም በተለይ የግብርና ምርት መሠረተ ልማት ሎጂስቲክስን ለማቀላጠፍ ዕገዛ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ክልሎች የፌዴራል በጀትን ከመጠበቅ በዘለለ ለፕሮጀክቱ የሚሆነው 30 በመቶ ወጪ እንደሚሸፈን፣ ክልሎች የገንዘብ ወጪ ብቻ ሳይሆን ማኅበረሰቡን በማስተባበርና በሌሎች ሥራዎች ፕሮጀክቱን እንዲደግፉ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ፕሮግራሙ አራት ዓመታት የሚወስድ መሆኑንና 60 ቢሊዮን ብር በጀት እንደሚያስፈልግ ገልጸው፣ በጀቱ ከዓለም ባንክ፣ ከፌዴራል መንግሥትና ከክልል መንግሥታት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ሲከናወን የነበረው የገጠር ትስስር ተደራሽነት ፕሮግራም ተገምግመው የታዩ ችግሮች በአዲሱ ፕሮግራም ላይ እንቅፋት እንዳይሆኑ ውይይት ይደረግባቸዋል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ቀድሞ በነበረው አሠራር በጀት ከተለቀቀ በኋላ መንገድ ይሠራ ወይም አይሠራ የሚገመገምበትና የሚታይበት አሠራር እንዳልነበረ ጠቁመው፣ ለአራት ዓመታት በሚተገበረው ፕሮጀክት ግን ወረዳዎች በሠሩት ልክ ገንዘብ እንደሚለቀቅላቸው ሚኒስትር ደኤታው አስታውቀዋል፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...