Sunday, February 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበትግራይ ክልል በሰሜኑ ጦርነት 76 አትሌቶች ሕይወታቸው ማለፉ ተገለጸ

በትግራይ ክልል በሰሜኑ ጦርነት 76 አትሌቶች ሕይወታቸው ማለፉ ተገለጸ

ቀን:

በትግራይ ክልል በሰሜኑ ጦርነት 76 አትሌቶች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከኅዳር 15 እስከ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. በመቀሌ ከተማ ያደረገ ሲሆን የክልሎችን ሪፖርት አዳምጧል፡፡

የትግራይ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባቀረበው ሪፖርት መሠረት ሁለት ዳኞች፣ ሁለት አሠልጣኞች እንዲሁም 76 አትሌቶች በድምሩ 80 የአትሌቲክስ ማኅበረሰብ በጦርነቱ ወቅት ሕይወታቸውን ማጣታቸውን የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ኪዳነ ተክለሃይማኖት ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ፣ በክልሉ የሚገኙ ስድስት ክለቦች፣ የስፖርት ማሠልጠኛ ማዕከላት እንዲሁም የወረዳ ፕሮጀክቶች ላይ ከፍተኛ ውድመት እንደገጠመ አብራርተዋል፡፡ በክልሉ የሚገኘው የማይጨው አትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከል በመድፍ በመመታቱ የነበሩት የስፖርት መገልገያዎች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ጠቅሰዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከዚህም ባሻገር በክልሉ የነበሩት ክለቦች የነበራቸው ሀብት ከትጥቅ ጀምሮ አጠቃላይ መውደሙን በሪፖርቱ አቅርበዋል፡፡ በክልሉ የሚገኙ የወረዳ አትሌቶች ማሠልጠኛ ማዕከላት በደረሰው ጉዳት 12,62,725 ብር በላይ እንደወደመ የተጠቀሰ ሲሆን፣ በአጠቃላይ የክለቦችን ውድመት ተመን ሳይጨምር 43,309,979 ብር ውድመት እንደደረሰ አቶ ኪዳነ በሪፖርቱ አቅርበዋል፡፡

ከ2013 ዓ.ም. በፊት መቀሌ ስታዲየምን ጨምሮ የተለያዩ የስፖርት ማዕከላት የነበረው ክልሉ፣ አዲስ ፕሮጀክት ኮረም ላይ ለማቋቋም በሒደት ላይ እንደነበረና፣ በሽሬ ከተማ የአጭርና መካከለኛ ርቀት እንዲሁም የሜዳ ተግባር አትሌቲክስ ለማስፋፋት እንቅስቃሴ በጀመረ ማግስት ጦርነቱ መቀስቀሱን ጠቅሰዋል፡፡ ሆኖም የስፖርት መሠረተ ልማት በጦርነቱ በአጠቃላይ ወድሟል፡፡

በተለያዩ ወረዳዎች ስምንት ፕሮጀክቶች ቢኖሩም ባለው አቅም ግን ስድስቱን ብቻ ማስተናገድ መቻሉ ተጠቁሟል። በክልሉ   ስድስት ክለቦች የነበሩ ሲሆን እያንዳንዱ ክለብ 40 እና 50 አትሌቶች አቅፎ እንቅስቃሴ ሲያደርግ መቆየቱን፣ በአንፃሩ ግን አሁን አንድም ክለብ አለመኖሩ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

ከጦርነቱ አስቀድሞ ከክልሉ የሚመጡ አትሌቶች በአገር አቀፍ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ውድድሮች ጎልተው ይወጡ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም ጦርነቱ እየተካሄደ በነበረበት ወቅት የክልሉ አትሌቶች በዓለም አቀፍ ውድድሮች ደምቀው መታየታቸው የተጠቀሰ ሲሆን፣ ይኼም ቀድሞ በተሠራው ሥራ እንደሆነ ተነስቷል፡፡

ከምሩፅ ይፍጠር ጀምሮ ከክልሉ የወጡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአገሪቱን ስም ማስጠራት የቻሉ አትሌቶች በአጠቃላይ  33 አትሌቶች ማፍራት መቻሉ ተጠቁሟል፡፡ ክልሉ ከማዕከላዊ መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት ላይ ከደረሰ በኋላ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች መደረጋቸው የተነሳ ሲሆን፣ በተለይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ መቀሌ አምርቶ የሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ካደረገ በኋላ በ2015 ዓ.ም. ሊተገበሩ የሚገባቸው ሥራዎች እንዲለዩ መደረጉ ተነስቷል።

በሌላ በኩል መቀመጫውን በመቀሌ ያደረገው የትግራይ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ላይ ስርቆት እንደደረሰበት የተገለጸ ሲሆን፣ በዚህም 702,254 ብር ያህል ሀብት ማጣቱን ተጠቁሟል፡፡

ፌዴሬሽኑ የክልሉን ስፖርት ዳግም ለማነቃቃትና መጠነኛ የገቢ ምንጭ ለመፍጠር ከተለያዩ አዘጋጆች ጋር በጋራ በመሆን በመቀሌ አራት የጎዳና ላይ ውድድሮች እንዲሁም አንዴ በአክሱም የጎዳና ላይ ውድድር መሰናዳቱ ተጠቅሷል፡፡

በአንፃሩ ወደ መደበኛ ውድድር ለመግባትና ክለቦችን ለማንቀሳቀስና ስፖንሰር ለማሰባሰብ የተደረገው ጥረት አለመሳካቱን አቶ ኪዳነ አስረድተዋል፡፡ በሌላ በኩል በመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሪፖርቱን ያቀረበ ሲሆን፣ በጦርነቱ ሳቢያ ሁለት ሰው እንደሞተበት ተገልጿል፡፡ ሌላኛው የጦርነቱ ገፈት ቀማሽ የነበረው የአማራ ብሔራዊ ክልል ሲሆን፣ ምንም እንኳ በሰው ሕይወት ላይ የደረሰበት አደጋ ባይኖርም ውድድሮች በመሰረዛቸው እንዲሁም በበጀት እጥረት ምክንያት አትሌቲክሱን በተፈለገው መንግድ ማካሄድ አለመቻሉን በሪፖርቱ ገልጿል፡፡

በመቀሌ ጠቅላላ ጉባዔውን ያደረገው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለክልሎች፣ ለከተማ አስተዳደሮች፣ እንዲሁም ለክለቦች ማበረታቻ የ2,100,000 ብር ሽልማት ያበረከተ ሲሆን፣ ለትግራይ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 150 ሺሕ ብር እንዲሁም በትግራይ ከተማና ለተፈናቃሉ ወገኖች የሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበርክቷል

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...