Sunday, February 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የዕድገት ሚዛኑ…

ትኩስ ፅሁፎች

አንቺ ኢትዮጵያ

የሊቃውንት መፍለቅያ

የአክሱም የየሃ ታሪክ ባለ አሻራ

የላሊበላ ውቅር፣ የፋሲል ግንብ፣ ድንቅ ሥራ

ሲኖር እያበራ

በቅዱስ መጽሐፍ ያለሽ ሥፍራ

ከ40 በላይ የተጠራ

ተከብረሽ የኖርሽ

የፍቅር ተምሳል የነበርሽ

የአንድነት ምልክት፣ የነፃነት ቀንዲል

ለጥቁር ሕዝብ የተስፋ ደወል

መፅናኛው የነበርሽ

ዛሬ ተሽቆልቁለሽ

ከጥልቅ ጉርጓድ ገብተሽ

በሞት አፋፍ እያለሽ

በበላበት ጯሂ ሁሉ ሲዋሽ

ይልሻል ተመነደግሽ!!!

 

የዕድገት ውኃ ልኩ ምን ይሆን?

የመስፈሪያው ሚዛን…?

የሞተው ሰው ቁጥር?

እየተቆጠረ ዘር

ነው ወይስ የተሰደደው

በየዱሩ የታረደው

ተዘቅዝቆ የተሰቀለው

ያለፍርድ የታጎረው

ኑሮ ያማረረው…

ምን ይሆን መለኪያው

ለመሪዎች ብቻ የሚታየው

ለሕዝብ የተሰወረው?

የምትፈልጉትን እያያችሁ

ሕዝብ አሰቃይታችሁ

ዘርማንዘር ቆጥራችሁ

መርዝ እየረጫችሁ

ትውልድ እየተገደለ

የላሸቀ ሞራል እያዘለ

እንደሰው ከማሰብ

ዘር ቆጥሮ መሰብሰብ

ነውና መፍትሔው

መግባት ከዘር ጉያው

የዕድገት መመዘኛው

ብላችሁ አባልታችሁ

አድገናል፣ ከአፊሪካ አንደኛ

ማን አለ እንደኛ!!!

እያላችሁ፣ ቱሪ ናፋ ከመንፋት 

ዙሪያ ጥምጥም ከመዞር

ከንቱ ኑሮ ከመኖር

ቢዘገይም በድለናል ኢትዮጵያን

አዋርደናል ሰንደቋን

ዝቅ አርገናል ክብሯን

ማረን የኢትዮጵያ ሕዝብ

ዕድሉ ቢሰጠንም

የዘር ፖለቲካን ለማረም

ብንመከር እንድናርም

አልሰማንም!!!

ሠርተናል ሳናስብ

መስማት ትተን ይህን ሕዝብ

ብላችሁ ሱባኤ ግቡና

በጥሞና አስቡና

ወደ ሰውነት ተመለሱ

ሕዝብን ካሱ

የሃሰት ምላስን ሰብሰብ!!

ከአጉል ቲቢት ረገብ!!

ከእኛ ሌላ ላሳር

አልበጀም ለቄሳር

ይኼ ሕዝብ “ሆ” ያለ ዕለት

እንኳን ሰው ይፈልጣል አለት

ጭቃ ጅራፉ ሳይመጣ

የመጨረሻው “ጣጣ”

ባለቀ ሰዓትም ቢሆን

ለማስወገድ የዘር ፖለቲካን

ለዓመታት ያባላንን

ዕድሉ ተስጥቷችሁ

የልጅ ጫወታ አድርጋችሁ

ጊዜ ብታቃጥሉም

ይቅርታ ብሎ መታረም

ይበጃልና ለሁሉም

ማረን፣ ማሩን በሉ

የጩቡ እንጀራ ከምትበሉ

ዘረኝነት ይጥፋ፣ ይወገድ ከአገር

እንድንኖር በፍቅር

ይብቃ መገዳደል

ይደወል የሰላም ደወል!!!!!

ኢትዮጵያ የቃል ኪዳን አገር

ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!!

(ተስፋዬ መኮንን ዶ/ር)

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች