Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ለተጠራቀመበት ዕዳ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲሰጥ ተጠየቀ

ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ለተጠራቀመበት ዕዳ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲሰጥ ተጠየቀ

ቀን:

  • ኢትዮ ጂቡቲን ለሚያስተዳድረው አካል በዓመት 60 ሚሊዮን ዶላር እየተከፈለ መሆኑ ተገልጿል

የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የተጠራቀመበት ዕዳ በአፋጣኝ ፖለቲካዊ መፍትሔ ካላገኘ፣ በመጪዎቹ አምስት ዓመታት የዕዳ መጠኑ ወደ 250 ቢሊዮን ብር እንደሚያሻቅብ፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት አቀረበ፡፡

በቢሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ዕዳ አለበት የተባለው ኮርፖሬሽኑ፣ በአሁኑ ጊዜ ምንም ዓይነት ገቢ እንደሌለው ተገልጿል፡፡ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ህሊና በላቸው (ኢንጂነር) ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ኮርፖሬሽኑ ያለበት ዕዳ ምን ያህል እንደሆነ በግልጽ ባይናገሩም፣ ለውጭ አበዳሪዎች የሚከፈለው ገንዘብ በውጭ ምንዛሪና ከፍተኛ መጠን ያለው በመሆኑ የመንግሥት ውሳኔ ይፈለጋል ብለዋል፡፡ የአገር ውስጥ ብድር ግን ለዕዳና ለሀብት አስተዳደር እንደሚተላለፍ ተናግረዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ያለበት ዕዳ ከመጀመሪያው የሀዲድ ዝርጋታ የግንባታ ብድር ጋር ሲነፃፀር የብር ምንዛሪ አቅም መዳከም፣ በየጊዜው የሚጨመረው ወለድና የመሠረተ ልማት እርጅና ከመጀመሪያው ዋና ብድር ጋር ተዳምሮ የተጠራቀመውን የዕዳ መጠን እያሻቀበው ነው ብለዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ክፍያውን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እየተበደረ ይከፍል የነበረ ቢሆንም፣ ብድሩ በታሰበው ጊዜ እየተከፈለ ባለመሆኑ የዕዳውን መጠን ከፍ እንዳደረገው አስረድተዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ፣ የመንግሥት የልማት ድርጀቶችና ይዞታ አስተዳደርን ሩብ ዓመት አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት፣ የቋሚ ኮሚቴው አባል ወ/ሮ አዲስ ዓለማየሁ በኮሚቴው የመስክ ምልከታ ከተሠራ ጥናት አረጋገጥን እንዳሉት፣ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አሁን ባለበት የዕዳ ሁኔታ ከቀጠለ በመጪዎቹ አምስት ዓመታት የዕዳ መጠኑ ወደ 250 ቢሊዮን ብር ይደርሳል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በ2016 ዓ.ም የመጀመሪያዎቹ አራት ወራት ብቻ 34 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ማስመዝገቡ በሪፖርቱ የተገለጸ ሲሆን፣ የባቡር መስመሩ ሥራ ከጀመረ ዓመታት ያስቆጠረ ቢሆንም አሁን በግንባታ ላይ ያሉ የባቡር መስመሮች ወደ ሥራ እስኪገቡ ድረስ ምንም ዓይነት የገቢ ምንጭ አይኖረውም ተብሏል፡፡

በግንባታ ላይ ያለውና አፈጻጸሙ 93 በመቶ እንደደረሰ የተገለጸው የአዋሽ ኮምቦልቻ – ሃራ – ገበያ – ወልድያ – መቀሌ መስመር ወደ ሥራ እስኪገባ ምንም የገቢ ምንጭ ስለሌለው የኮርፖሬሽኑ ዕዳ ተጨማሪ ምክክር እንደሚያስፈልገው ጠቅሰው ትኩረት የሚያሻው ጉዳይና ዘለቄታዊ መፍትሔ ያስፈልገዋል ያሉት፣ የመንግሥት የልማት ድርጀቶችና ይዞታ አስተዳደር አማካሪ አደራጀው ሹመት (ዶ/ር) ናቸው፡፡ ይህ መስመር በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ወቅት ውድመትና ዝርፊያ የደረሰበት ሲሆን፣ የሥራ ተቋራጩ የቱርክ ኩባንያ ደረሰብኝ ባለው ኪሳራ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እየተካሰሰ ነው፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዕዳ የውጭ ምንዛሪ በመሆኑ ጫናውን የሚያቃልል ባይሆንም፣ በቅርቡ ከግሉ ዘርፍ ጋር በመሆን የሎጂስቲክስ ኩባንያ በማቋቋም ወደ ሥራ እንደሚገባና ባለው መሬት ላይ ሁለገብ ሕንፃና የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ላይ በመሰማራት የገቢ ምንጭ አማራጮች ላይ ይሰማራል ተብሏል፡፡

ይሁንና በውጭ ምንዛሪ መከፈል ያለበትን ዕዳ ጫና መክፈል የሚያስችል ሀብት የሌለ በመሆኑና ከጅምሩ በፖለቲካ ብልሽት የመጣ ችግር በመሆኑ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንደሚያሻ ተገልጿል። ኮርፖሬሽኑ የአዲስ አበባ ጂቡቲ የባቡር መስመርን ለሚያስተዳድረው ድርጅት በየዓመቱ 60 ሚሊዮን ዶላር እንደሚከፍል አደራጀው (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ የኮርፖሬሽኑ ዕዳ በወቅቱ ባለመከፈሉ እየተጠራቀመና ወለዱ እያደገ መሆኑን፣ ተጠራቀመው ዕዳ በውጭ ምንዛሪ የሚከፈል በመሆኑ ችግሩ የፖለቲካ መፍትሔ ስለሚያስፈልገው የምክር ቤቱ ዕገዛ እንደሚስፈልግ አክለዋል፡፡

ከአዲስ አበባ ጂቡቲ 754 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የባቡር መስመር ወደ ሥራ ከገባ ከአምስት ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን፣ የሚተዳደረው በቻይና ኩባንያ ነው፡፡

የመንግሥት የልማት ድርጀቶችና ይዞታ አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ኃይለ ሚካኤል በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ በራሱ አቅም ዕዳውን መክፈል የሚችልባቸው የቢዝነስ አማራጮች እንደተቀረፁለት፣ ሀብት የሚያገኝባቸው የሥራ አማራጮች ላይ እንዲሰማራ ሰነዶች ተቀርፀው መገምገማቸውን ተናግረዋል። የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ህሊና (ኢንጂነር) እንደገለጹት፣ ኮርፖሬሽኑ የፋይናንስ ሞዴል ተቀርፆ ከግል ዘርፉ ጋር በመተባበር ባቡር በሚያልፍባቸው መስመሮች በሚገኙ ክፍት ቦታዎች፣ ከባቡር መስመሩ ጋር አብረው ሊሄዱ የሚችሉ ኢንቨስትመንቶችን ለማልማት ጥናት ተደርጎ የፋይናንስ አማራጮችና አልሚ የግል ባለሀብቶች እየተፈለጉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...