Sunday, February 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
የሳምንቱ ገጠመኝየ ሳ ም ን ቱ ገ ጠ መ ኝ

የ ሳ ም ን ቱ ገ ጠ መ ኝ

ቀን:

ድሮ ድሮ ተማሪ ሳለን በአማርኛ ክፍለ ጊዜ የምናነባትና ትምህርት አጠናቀን ከወጣን ከረጅም ጊዜያት በኋላ እንኳን የማንረሳት አንድ ምንባብ ነበረች፣ የ8ኛ ክፍሏ “ሽልንጌን”። ከረጅም ጊዚያት በኋላም ቢሆን ዶክተር ሆነውም ይሁን ኢንጂነር፣ ነጋዴም ይሁኑ ፕሮፌሰር ያኔ ያነበብናት ዛሬም ከአዕምሮአችን አትጠፋም። በ“ሽልንጌ” አጭር ልብ ወለድ ውስጥ የድሮ ባቡር ገጭገጭታና ጡሩምው፣ የሃሊማ የተሸበሸቡ የፊት ገጾችና የእንቅቧ ፓፓዬዎች በዓይነ ህሊናችን ይታዩናል። ኩሩውና ዘናጩ ተሳፋሪ ከሃሊማ ፓፓያ ገዝቶ በሃምሳ ሳንቲም ተጣልተው፣ ሃሊማ “ሽልንጌን” እያለች ስትከተለው አጭበርባሪ እያለ በጫማው ሲረግጣት፣ ሲያመናጭቃትና ቀኑን እንዳበላሸችበት እያሰበ ሲጓዝ እጁን ወደ ኪሱ በሚሰድበት ወቅት ያገኘው የሃሊማ ሽልንግ ፍንትው ብለው በዓይነ ህሊናችን ይመጣሉ።

አቤት ድንጋጤው… አቤት ፀፀት… አቤት ብሽቀት… ያቺ የ8ኛ ክፍሏ “ሽልንጌ” “ሥነ ጽሑፍ” የገሃዱ ዓለም ነፀብራቅ መሆኑን ፍንትው ወይም ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ድርሰት ነው። ያለማስተዋል የሐሳብ ዳመና ላይህ ላይ ሲያንጃብብና ስትዋጥ እንኳን የአካባቢህን የጨበጥከውንም ቢሆን ትዘነጋዋለህ። ለዛሬ በቅርቡ ጓደኛዬ የነገረኝን አስገራሚ ገጠመኝ እንደ ራሱ ሆኜ ላወጋችሁ ወደድኩ። በአንዱ ቀን ምሽት ከቢሮ እንደወጣሁ ስድስት ኪሎ አካባቢ አመሻሽቼ የፈረንሣይ ታክሲ ለመያዝ ከተኮለኮለው ሠልፈኛ መሀል ተቀላቀልኩ፡፡ ረጅሙን ሠልፍ አገባድጄ አንድ ታክሲ ላይ ተሳፈርኩ። ታክሲው መያዝ ከነበረበት በላይ ተሳፋሪ አጭቆና አጨናንቆ ጉዞውን ቀጠለ፡፡ እኔም እንደ ምንም ኪሴን ፈልጌ የአሥር ብር ኖት በማውጣት ለረዳቱ አቀበልኩት።

ከቆይታው በኋላ መልሴን ሰጠኝና ወደ ኪሴ ማስገባት ስላልቻልኩ በእጄ እያጣጠፍኩ፣ እየጠቀለልኩ በብሯ ቀለበት ነገር እየሠራሁና እያፍተለተልኩ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ታክሲው የፈረንሣይን ዳገት ሲያያዝ የሞተሩም ድምፅ ጨመረ በዚሁ ቅፅበት  አንድ ተሳፋሪ ከረዳቱ ጋር ከፍ ባለ ድምፅ መጨቃጨቅ ጀመረ፡፡ የጭቅጭቁ ምክንያት ደግሞ መቶ ብር ነው የሰጠሁህ፣ አይደለም የሰጠህኝ አሥር ብር ነው በሚል ነበር። ሁለቱም በእልህ ተያይዘው ሊጋደሉ ሆነ፣ እኔም ሆንኩ ሌሎች ተሳፋሪዎች ልናስማማቸው ብንሞክርም የሚሆን አልሆነም። ስለዚህ ተያይዘው ሕግ ፊት እንዲቀርቡ በመስማማታቸው ኬላ አካባቢ የሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ አደረስናቸውና አኛ ወርደን በየአቅጣጫችን ተበታተንን፡፡ እኔም ከኬላ ወደ ጉራራ የሚጓዘው ታክሲ ውስጥ ገብቼ ጉዞዬን ቀጠልኩ። በጉዞዬም ላይ የሁለቱ ሰዎች ጭቅጭቅና ክርክር ከአዕምሮዬ አልጠፋ አለ። ተሳፋሪው ሌባ አይመስልም፣ በንዴትና በእልህ በተሞላበት ንግግሩ በትክክል ገንዘቡን እንደከፈለ ነው የእኔ አዕምሮ ያሰበው። ረዳቱም ቢሆን በእልህና በሙሉ መተማመን ነው የሚናገረው፡፡ “ከሰጠኝ የት ወሰድኩት እጄ ላይ ከባለ አምስትና አሥር ብር ውጪ የለ…” እያለ በሚያሳዝን ፊቱ ሲነግረን ፊቴ ድቅን ይላል። ታድያ ምን ጉድ ተፈጠረ እያልኩ ሳሰላስል ነበር የተሳፈርኩበት የታክሲ ረዳት መልስ ብሎ የ95 ብር ኖት ያስጨበጠኝ።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ቀለል አድርጌ፣ ‹‹አምስት ብር ነው የሰጠሁህ…›› አልኩት፡፡ ረዳቱ ግን በጨዋ ደንብ፣ ‹‹አይደለም መቶ ብር ነው…›› ብሎ በእጄ ሳፍተለትለው የነበረውን የመቶ ብር ኖት አሳየኝ፣ ክው አልኩ፡፡ ድንጋጤዬ ቀላል አልነበረም፣ ያ ከባለመቶ ብሩ ጋር የሚጨቃጨቀው ረዳት አምስት ብር መስሎት ለእኔ የመቶ ብር ኖት አስጨብጦኝ ነው ለካስ። ተመልሼም ብሄድ አልደርስባቸው ከስድስት ኪሎ የጫነኝ ታክሲ የሚዞረው ኬላ፣ ተሳፋሪውም እስካሁን አይቆይ። ምን ይደረጋል፣ ምንም ማድረግ ሳልችል ወደ ቤቴ ገባሁ ነበር ያለኝ፡፡ ይህ አጋጣሚ በእውነት አስገራሚ ገጠመኝ ነው፡፡ ለዚህም ነው “ሽልንጌን” ያስታወሰኝ፡፡

ከላይ እንደ መንደርደሪያ ያቀረብኩት የ8ኛ ክፍሏ ገጠመኝ ከዚህ ታሪክ ጋር አልተቀራረባችሁም ታድያ፡፡ የሆነስ ሆነና ጥፋተኛው ማነው… ረዳቱ፣ ጓደኛዬ ወይስ ተሳፋሪው፡፡ ለእኔ ረዳቱና ጓደኛዬ ናቸው ባይ ነኝ። ድርጊቱ ልብ ብለን ካላስተዋልነው “ልብ ካላየ ዓይን አያይም” የሚለውን አባባልን አጉልቶ የሚያሳይ ቢሆንም፣ ቆጥሮ ያልሰጠና ቆጥሮ ያልተቀበለ ሁለቱም…” የሚለውን ብሂል ያስታውሰኛልና ነው።

       (ሚስባህ አወል፣ ከአዲስ አበባ)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...