Sunday, February 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየገናን ባዛር በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል

የገናን ባዛር በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል

ቀን:

በአዲስ አበባ ውስጥ ከትልልቅ እስከ ትንንሽ የንግድ ትርዒቶች የሚካሄድበት ቀደምት ማዕከል ነው፡፡ የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በየዓመቱ ከ44 በላይ የንግድ ትርዒቶችና ባዛሮች ይካሄዱበታል፡፡

የንግድ ትርዒቶች ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ቢታመንም፣ ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒቶች ማሳያነት የሚሆንና ደረጃውን የጠበቀ ምቹ ሥፍራ እንደሌላት በተደጋጋሚ ይነገራል፡፡

የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ለዓለም አቀፍ ንግድ ትርዒቶች ብቻ ሳይሆን፣ ለተራ ዝግጅትም አይመጥንም የሚሉ ትችቶችም በሰፊው ሲደመጡ ከርመዋል፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን ችግር ለመቅረፍና ማዕከሉንም ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ 25 ሚሊዮን ብር ወጪ በማውጣት የአስፋልት ዝርጋታ እያከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የኤግዚቢሽን ማዕከል አስታውቋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ማዕከሉ ይህንን ያስታወቀው፣ ለ33ኛ ጊዜ ከታኅስስ 6 እስከ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. የገና በዓል ንግድ ትርዒትን ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ባስታወቀበት ወቅት ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት የቴክኒክ መምርያ ባለሙያ አቶ ደረጄ አሥራት ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የኤግዚቢሽን ማዕከሉ ከዚህ በፊት የነበረውን የቦታ ይዞታ በማስፋፋት የደንበኞች ቁጥር እንዲጨምር ተደርጓል፡፡

ማዕከሉ ከዚህ በፊት ለደንበኞች አገልግሎት የሚውለው 5,310 ካሬ ሜትር መሆኑን ገልጸው፣ አሁን የደንበኞችን ፍላጎት ለማጣጣም 7,682 ካሬ ሜትር ድረስ እንዲኖረው መደረጉን አክለዋል፡፡

የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ መኮንን በበኩላቸው፣ የኤግዚቢሽን ማዕከሉ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ካለው የቦታ አቀማመጥና ከሕዝብ ተደራሽነት አንፃር የተሻለ ለማድረግ ማዕከሉን የማደስ ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ በፊት የተለያዩ ዕድሳቶችና ማስፋፊያዎች ያልተደረጉት የማስፋፊያ ሥራዎች ላይ በውጭ ባለሙያዎች በ300 ሺሕ ዩሮ ጥናት እንደተደረገበት፣ 10,000 ሔክታር ቦታ ለማደስ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩና የንግድ ምክር ቤቱ ባደረጉት ጥምረት መሠረት ይህ አሠራር ተግባራዊ እንደሚሆን ገልጸው፣ ፕሮጀክቱ ተግባራዊ እስከሚሆን በከፊል የማስፋፊያ ሥራ መከናወኑን አብራርተዋል፡፡

በዚህ መሠረት አሁን የተጀመረው ዕድሳት ሙሉ ለሙሉ ተጠናቅቆ ለገና በዓል ኤግዚቢሽንና ባዛር ዝግጁ እንደሚሆን የተናገሩት ኃላፊው፣ ከአስፋልት ዝርጋታ ውጪ ለሕፃናት መጫወቻ የሚሆን ቦታ እየተዘጋጀ መሆኑን አክለዋል፡፡

ከዚህ በፊት አቧራና ጭቃ የነበረውን ቦታ አስፋልት በማድረግ በኤግዚቢሽንና ባዛሩ የሚሳተፉ ነጋዴዎችም ሆኑ ሸማቶች እንደፈለጉ እንዲገበያዩ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ የአዳራሽ ሙቀቶችን ማስወገጃ፣ የራሱ የሆነ ከፍተኛ የሆነ አቅም ያለው ጄኔሬተር ለመሥራት በሒደት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

በተለይ ከዚህ በፊት ከ350 እስከ 400 ድረስ ብቻ የሚሆኑ ነጋዴዎች ይሳተፉ እንደነበር፣ የአስፋልት ዝርጋታው ተጠናቆ ሲያልቅ ከ500 እስከ 600 ነጋዴዎች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል፡፡

ለ22 ቀናት በሚካሄደው የገና በዓል ኤግዚቢሽን ደንበኖች በፈለጉት መንገድ እንዲንቀሳቀሱና እንዲሸምቱ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ያሉት የሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘውገ ጀማነህ ናቸው፡፡

አብዛኛውን ጊዜ በየዓመቱ ኤግዚቢሽን ሲካሄድ የቦታ ጥበት ይገጥማቸውና ከነጋዴዎችም ሆነ ከሸማቾች ቅሬታ ሲነሳ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

ይህንንም ቅሬታ ለመፍታት የአዲስ አበባ ከተማ ኤግዚቢሽን ማዕከል ትልቁን ድርሻ መወጣቱን ገልጸው፣ በዚህ መሠረት በገና በዓል ከ500 በላይ ነጋዴዎችን ለማሳተፍ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...