Monday, February 26, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ንግድ ባንኮች የተጣለባቸው የብድር ገደብ ላይ ላቀረቡት አቤቱታ ምላሽ እየጠበቁ መሆኑ ተጠቆመ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ባንኮች የብድር ዕድገት ምጣኔ ከ14 በመቶ መብለጥ እንደሌለበት ያወጣው መመርያ ከፍተኛ ጉዳት ያደርስብናል ያሉ አሥራ አንድ ባንኮች፣ መመርያው ተፈጻሚ እንዳይሆንባቸው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ላቀረቡት አቤቱታ ምላሽ እየጠበቁ መሆኑ ተጠቆመ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ባወጣው የገንዘብ ፖሊሲ ተግባራዊ ካደረጋቸው ውሳኔዎች መካከል አንዱ፣ የባንኮች የብድር የዕድገት ምጣኔ ከ14 በመቶ መብለጥ የለበትም የሚል መሆኑ አይዘነጋም፡፡

ንግድ ባንኮች የተጣለባቸው የብድር ገደብ ላይ ላቀረቡት አቤቱታ ምላሽ እየጠበቁ መሆኑ ተጠቆመ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

ነገር ግን ይህ መመርያ አነስተኛ የብድር ምጣኔ የነበራቸውን በተለይም ኢንዱስትሪውን ዘግይተው የተቀላቀሉ ባንኮች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያሳርፍ በመሆኑና ተጨማሪ መረጃዎችን በማያያዝ፣ ብሔራዊ ባንክ መፍትሔ እንዲሰጣቸው አቤት ለማለት ተገደዋል፡፡

መመርያው የሚፈጥርባቸውን ችግር በዝርዝር በማብራራት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፒቲሺን በመፈራረም አቤት ያሉ ባንኮች ቁጥር አሥራ አንድ መሆናቸውን የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ይህንን አቤቱታ ካቀረቡ ባንኮች መካከል ፀሐይ ባንክ፣ ሲንቄ ባንክ፣ ፀደይ ባንክ፣ ገዳ ባንክ፣ አሃዱ ባንክ፣ ጎህ ባንክ፣ ራሚስ ባንክ፣ ዘምዘም ባንክና እናት ባንክ ይገኙበታል፡፡

እነዚህ ባንኮች ዓመታዊ የብድር መጠናቸው አነስተኛ ከመሆኑ አንፃር፣ ብድራቸውን በ14 በመቶ ብቻ መገደቡ የሚሰጡት አዲስ ተጨማሪ ብድር እጅግ የተመጠነ ስለሚያደርገው፣ ባንኮቹ ብድር በማቅረብ ሊያገኙ የሚችሉትን ጥቅም በእጅጉ የሚጎዳ በመሆኑ፣ መመርያው እነሱን እንዳይመለከት በማድረግ ካልተሻሻለ ተጎጂ እንደሚሆኑም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባቀረቡት አቤቱታ ማስታወቃቸውንም እኚሁ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

አቤቱታው ከቀረበ በኋላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጉዳዩን ተመልክቶ በቶሎ ምላሽ የማይሰጣቸው ከሆነ፣ የጉዳታቸው መጠን የሚጨምር በመሆኑ በቶሎ ምላሽ የሚሹ ስለመሆኑም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔዊ ባንክ ፒቲሽን ተፈራርመው በመመርያው ተጎጂ እን’ሆናለን ካሉት ባንኮች መካከል አብዛኞቹን ጉዳይ እንደሚመለከታቸው ተናግሮ እንደነበር እነዚሁ ምንጮች ሳይጠቁሙ አላለፉም፡፡

አሁንም ባንኮቹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጉዳያቸውን በተለየ ተልክቶ ውሳኔ እንዲሰጣቸው እየተጠባበቁ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህ መመርያ ከነባር ባንኮች አንፃር ሲታይ የበለጠ ተጎጂ ይሆናሉ ቢባልም ትልልቅ የብድር መጠን ያላቸው ባንኮችም የብድር ገደቡ ተፅዕኖ የሚያሳርፍባቸው ስለመሆኑ በተለያየ መንገድ ሲገለጽ መቆየቱ አይዘነጋም፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአገሪቱ ያለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት እተገብረዋለሁ ባለው የገንዘብ ፖሊሲ ከብድር ገደቡ ሌላ ለመንግሥት የሚሰጠውን ቀጥታ የብድር መጠንም ከቀዳሚው ዓመት ከአንድ ሦስተኛ እንዳይበልጥ የፖሊሲ ውሳኔ የተላለፈበትም ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች