Monday, February 26, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

 • አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው?
 • ጠፋሁ አይደል?
 • ጠፋሁ ብቻ?!
 • ምን ላድርግ ብለሽ ነው?
 • እንዴት?
 • አለቃዬ ዕረፍት የለው፣ እኔንም አላፈናፍን ብሎኛል።
 • ታድለሽ።
 • ታድለሽ? ሥራ ገደለኝ ዕረፍት አጣሁ እኮ ነው ያልኩሽ?
 • ገብቶኛል። ምነው እኔንም እንደ አንቺ ባደረገኝ ማለቴ ነው።
 • አለቃሽ የሉም፣ ዕረፍት በዕረፍት ሆነሻል ማለት ነው።
 • ኧረ አሉ።
 • ከምርሽ ነው፣ አሉ?
 • አዎ።
 • እንዴ!? እኔ እኮ አንዱ የደወልኩበት ምክንያት ይህን ልጠይቅሽ ነበር።
 • ምን ልትጠይቂኝ?
 • እንደ ቀድሞው በካቢኔ ስብሰባ ላይም ሆነ ባለሥልጣናት በተገኙባቸው መድረኮች ላይ አይቻቸው አላውቅም።
 • አዎ። እኔም የትም ሲሄዱ አይቻቸው አላውቅም።
 • ቀብር ላይ ወይም ለቅሶዎችን ሲደርሱ ግን በተደጋጋሚ አያቸዋለሁ።
 • ልክ ነሽ።
 • እንዲያውም በቅርቡ በቴሌቪዥን አንድ የውጭ ኤምባሲ ተገኝተው ተመልክቼ፣ አይ ሥራ ላይ ናቸው ብዬ ገምቼ ነበር ግን…
 • ግን ምን?
 • በኤምባሲው የተገኙት የሐዘን መግለጫ ለማድረስ መሆኑን ስረዳ ይሄ ነገር ምንድነው ብዬ ስገረም ነበር።
 • እኔም እንደ አንቺው እንቆቅልሽ ሆኖብኛል።
 • እንዴት?
 • ምክንያቱም እንደ ቀድሞው የካቢኔ ስብሰባ አለብኝ ሲሉ ከሰማሁኝ ቆየሁ።
 • እና ሁሌ ቢሮ ነው የሚውሉት?
 • አብዛኛውን ጊዜ ቢሮ ናቸው። አንዳንዴ ግን ወጣ ይላሉ።
 • ወዴት?
 • ወይ ቀብር አለብኝ፣ ካልሆነ ደግሞ ለቅሶ ልደርስ ነው ብለው ነው የሚወጡት።
 • ከምርሽ ነው?
 • የምሬን ነው።
 • ብቻ በመንግሥት ተወስኖ ተደርገው እንዳይሆን?
 • ምን ተደርገው?
 • ደራሽ።
 • ምን ደራሽ?

 

 • የመንግሥት ለቅሶ ደራሽ!

[ክቡር ሚኒስትሩ ለሦስት ቀናት ከቆዩበት ስብሰባ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲመለሱ ባለቤታቸው ምን ዓይነት አሳሳቢ ጉዳይ ስልክ አዘግቶ እንደሰወራቸው ለማወቅ መጠየቅ ጀመሩ]

 • ፓርቲያችን ባቀረበው ሰነድ ላይ እየተወያየን ነበር።
 • የምን ሰነድ?
 • የጋራ ትርክት መፍጠር በስኬት የሚል ሰነድ ላይ ነበር።
 • ታዲያ እንዴት ነበር ውይይቱ?
 • በስኬት ተጠናቋል!
 • መቼም የዚህ አገር ችግርና ችግሩን ለመፍታት የሚደረግ ስብሰባ ማለቂያ የለውም።
 • እንዴት?
 • አንድ ችግር ሲመጣ እናንተ ችግሩን ለመፍታት ስትሰበሰቡ፡፡
 • ሌላ ችግር ሲመጣ እናንተ ስትሰበሰቡ…
 • ምን ለማለት ፈልገሽ ነው?
 • መከራና ስብሰባ እየተፈራረቁብን ጊዜያችንን ፈጀነው ማለቴ ነው።
 • አትሳሳቺ!
 • ምን ተሳሳትኩ?
 • ችግርና ፈተና እኛ ላይ ሥጋት አይፈጥሩብንም።
 • ታዲያ ምንድነው የሚፈጥሩባችሁ?
 • ብርታት!
 • ምን አለ እንደ እናንተ ለሁላችንም ደንዳና ልብ ቢሰጠን!
 • አትሳሳቺ!

 

 • እንዴት?
 • ልባችን ደንዳና ሆኖ አይደለም።
 • እና?
 • ችግሮችን የምንተነትንበት መንገድ ውጤት ነው።
 • እ… ታዲያ ትንታኔያችሁ ለምን ችግሮችን ሊፈታ አልቻለም?
 • እንደነገርኩሽ ነው።
 • እንዴት?
 • የእኛ ትንታኔ ችግርና ፈተናዎችን መፍታት ላይ አያተኩርም።
 • ታዲያ ምን ላይ ነው የሚያተኩረው?
 • ትንታኔያችን?
 • እህ …?
 • ፈተናዎችን ወደ ዕድል መቀየር ላይ ነው የምናተኩረው።
 • ፈተናዎችን ወደ ምን መቀየር ነው ያልከው?
 • ወደ ዕድል።
 • ብቻ እንዳይሰሟችሁ?
 • እነ ማን?
 • ማትሪክ ተፈታኞች!
 • ቢሰሙስ?
 • ወደ ዕድል ቀይሩልን እንዳይሏቹሁ?
 • ምኑን?
 • ፈተናውን!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...

ሕወሓት በትግራይ ጦርነት ወቅት በፌዴራል መንግሥት ተይዘው ከነበሩት አባላቱ መካከል ሁለቱን አሰናበተ

በሕወሓት አባላት ላይ የዓቃቤ ሕግ ምስክር የነበሩት ወ/ሮ ኬሪያ...

የኤሌክትሪክ ኃይል ለታንዛኒያ ለመሸጥ የሚያስችል ስምምነት ለመፈጸም የመንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ለማከናወን የሚያስችለውን...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረክ። ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሞባይል ስልካቸው ላይ አተኩረው ሲመለከቱ ቆይተው፣ በድንገት ካቀረቀሩበት ቀና ብለው ባቤታቸውን ጠየቁ]

ምን ጉድ ነው የማየው? ምን ገጠመሽ? የመንግሥት ሚዲያዎች የሚያሠራጩት ምንድነው? ምን አሠራጩ? አልሰማህም? አልሰማሁም፣ ምንድነው? ዳግማዊ አፄ ምኒልክ መልዕከት አስተላለፉ እያሉ ነው እኮ። እ... እሱን ነው እንዴ? አዎ። የምታውቀው ነገር አለ? አዎ። የዓድዋ...

[ክቡር ሚኒስትሩ  የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላትን በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች እያዞሩ እያስጎበኙ ከአንድ ዲያስፖራ ጋር እየተወያዩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር የዛሬ ሁለት ዓመታት ገደማ ወደ አዲስ አበባ መጥቼ ከተማዋን ጎብኝቼ ነበር። እውነት? አዎ። ታዲያ ልዩነቱን እንዴት አዩት? በጣም ይደንቃል። ሌላ ከተማ እኮ ነው የመሰለችው። አይደል? አዎ። እንዴት ነው...