Wednesday, May 29, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊኢትዮጵያ የቤት ሠራተኞችን በሚመለከት የተዘጋጀውን የቃል ኪዳን ሰነድ ስምምነት እንድታፀድቅ ኢሠማኮ ጠየቀ

ኢትዮጵያ የቤት ሠራተኞችን በሚመለከት የተዘጋጀውን የቃል ኪዳን ሰነድ ስምምነት እንድታፀድቅ ኢሠማኮ ጠየቀ

ቀን:

ከአሥር ዓመታት በፊት በዓለም የሥራ ድርጅት የተደነገገውን የቤት ሠራተኞች መብቶችና ምቹ የሥራ ሁኔታን በሚመለከት የተዘጋጀውን የቃል ኪዳን ስምምነት ሰነድ፣ ኢትዮጵያም እንድታፀድቅ፣ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ጥያቄ አቀረበ፡፡

ኢሠማኮ ጥያቄውን ያቀረበው ዓርብ ኅዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ለዓለም አቀፍ በጎ አገልግሎት የቆመ ክርስቲያናዊ ድርጅት የተሰኘ ተቋም፣ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ከአንድነት የቤት ሠራተኞች ኅብረት፣ እንዲሁም ከተለያዩ ተቋማት ከመጡ ባለድርሻ አካላት ጋር የቤት ሠራተኞችን በተመለከተ ውይይት ሲያካሂድ ነው፡፡

የቤት ሠራተኞች እንደ ሌሎች ሠራተኞች መብታቸው እንዲከበር፣ የሳምንት እረፍት እንዲኖራቸው፣ የሚሠሩበት ሰዓት ወሰን እንዲኖረው፣ የደመወዝ ጣሪያቸው እንዲታወቅ፣ እንዲሁም ማኅበራዊ ደኅንነታቸው እንዲጠበቅ የዓለም የሥራ ድርጅት ባወጣው ድንጋጌ ተመልክቷል፡፡

- Advertisement -

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ፕሬዚዳንት አማካሪ አቶ ገዛኸኝ ዘሪሁን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ የቤት ሠራተኞችን መብቶች ማስበጠቅ ሥራዎችን አስመልክቶ፣ መንግሥት የሕግ ማዕቀፎችን እንዲያወጣና አስፈላጊውን ክትትል እንዲያደርግ ኢሠማኮ እየወተወተ ነው፡፡

የቤት ሠራተኞች ያሉባቸውን ችግሮች ለመቅረፍ እንዲቻል ተገቢ የሆኑ ደንብና መመርያዎች እንዲወጡ፣ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቢደነግግም፣ እንደ ማንኛውም ሠራተኛ የጋራ ችግራቸውን የሚመመክሩበት አሠራር ስለሌለ ኢሠማኮ ያልተቋረጡ ጥረቶች ሲያደርግ መቆየቱን አስረድተዋል፡፡

በዓለም የሥራ ድርጅት ድንጋጌ ቁጥር 189 ላይ እንደተመለከተው፣ የቤት ሠራተኞች መብቶችን ኢትዮጵያ በሕግ እንድትመራ ኢሠማኮ መንግሥትን እየጠየቀ መሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡

በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156 የተደነገገው የቤት ሠራተኞች ደንብ እስካሁን ተፈጻሚ አለመሆኑን የገለጹት አማካሪው፣ ደንቡ ተፈጻሚነት እንዲኖረውና የቤት ሠራተኞች መብት በአግባቡ እንዲከበር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መጠየቁን አብራርተዋል፡፡

የቤት ሠራተኞች መብቶችና ምቹ የሥራ ሁኔታ በሚመለከት የተዘጋጀውን የቃል ኪዳን ስምምነት ኢትዮጵያ እንድታፀድቅና የአገሪቱ ሕጎች አካል እንዲሆን ለማስቻል፣ በሕጉ ላይ በቂ ዕውቀት ያላቸው የአዲስ አበባ ዩኒቪርሲቲ ባለሙያዎችን፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና ሌሎች ተቋማትን ያካተተ ውይይት በተደጋጋሚ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ ውጤት ላይ ባለመደረሱ የቃል ኪዳን ስምምነት መፀድቅ በወጡ ሕጎች ላይ ተጨማሪ ሕግ ስለሚሆን፣ ሌሎች ተጨማሪ ሕጎችንም ለማውጣት ምቹ ሁኔታ ስለሚፈጥር፣ አሁንም ከተለያዩ ተቋማት ጋር በዚህ ጉዳይ ላይ ውይይት የሚደረግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ከሁሉም በላይ የቤት ሠራተኞች የሥራ ሁኔታቸው በሕግ ጥበቃ ባለመደረጉ እየደረሰባቸው ያለውን የመብት ጥሰት፣ አካላዊና ሥነ ልቦና ጉዳት ለማስቀረት፣ በአሠሪና በሠራተኛ አዋጅ የተቀመጠው ደንብ እንዲወጣ መንግሥትን ጫና ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በተለያዩ አገሮች ለሥራ የሚሄዱ የቤት ሠራተኞች መብቶቻቸው እንዲከበር የሁለትዮሽ ስምምነት እንደሚፈራረሙ፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ደኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ተናግረዋል፡፡

በሁለትዮሽ ስምምነት የሚካተቱ ጉዳዮች የቤት ሠራተኞች መብቶቻቸው እንዲጠበቅ ከማስቻላቸውም በተጨማሪ፣ የደመወዛቸው ምጣኔ ምን ይመስላል የሚለው የሚለይ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

የቤት ሠራተኞች በውጭ አገር መብቶቻቸው እንዲከበርላቸው የሚሠራውን ያህል በአገር ውስጥም ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፣ በአሠሪና በሠራተኛ አዋጅ በተደነገገው መሠረት ደንብ እንዲወጣ በግልጽ ቢሰፍርም፣ እስካሁን ተግባራዊ አልሆነም ብለዋል፡፡   

በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ የተደነገገው ደንብ ተግባራዊ ያልሆነው ከዚህ በፊት ጉዳዩን የያዘው ሌላ ተቋም ስለነበር እንደሆነ ገልጸው፣  አሁን ግን ደንቡ ተፈጻሚ እንዲሆን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መሆኑን አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን...

የኢትዮ ኤርትራ ሰሞነኛ ሁኔታና ቀጣናዊ ሥጋቱ

“ግንቡን እናፍርስ ድልድዩን እንገንባ” የሚል ፖለቲካዊ መፈክር ጎልቶ በሚሰማበት፣...

ኦሮሚያ ባንክ ከተበዳሪ ደንበኞቼ ውስጥ 92 በመቶ የሚሆኑት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ናቸው አለ

ኦሮሚያ ባንክ ለደንበኞቹ ከሰጠው ብድር ውስጥ ለአነስተኛና ለመካከለኛ ኢንተርፕራይዞች...

ሽቅብና ቁልቁል!

ጉዞ ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ ጀምረናል። ተሳፋሪዎች የዕለት ጉርሳቸውን መሸፈን...