Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ በመሸለም የተጠናቀቀው የዳሸን ከፍታ

ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ በመሸለም የተጠናቀቀው የዳሸን ከፍታ

ቀን:

በኢትዮጵያ አዳዲስ የሥራ ፈጠራ ውጤቶችን ይዘው ብቅ የሚሉ ወጣቶች በርካቶች መሆናቸው በተደጋጋሚ ይነገራል፡፡ ሆኖም የፈጠራ ሥራቸውን ወደ ምርትና አገልግሎት ለመቀየር ሲቸገሩ ይታያል፡፡

የፈጠራ ሥራ ለአንድ አገር ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፋይዳ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ቢሆንም፣ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች ጭላንጭል ተስፋ ከመታየት በዘለለ መሬት ላይ ጠብ ያለ ነገር እንደሌለ የዘርፉ ተዋናዮች ይናገራሉ፡፡

በዘርፉ የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ፣ ተዋናዮቹ ሥራቸው ዳር ደርሶ ራሳቸውንና ማኅበረሰባቸውን እንዲጠቅሙ፣ መንግሥትም ሆነ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሲሠሩ ይታያል፡፡ ከሥራዎቹ ደግሞ የፈጠራ ባለሙያዎችን አዋዳድሮ መሸለም ይገኝበታል፡፡  

- Advertisement -

ዳሸን ባንክም የሁለተኛ ዙር የ‹‹ዳሽን ከፍታ›› የሥራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊዎችን ማክሰኞ ኅዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ሸልሟል፡፡

በውድድሩ 2,500 የፈጠራ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ ተወዳዳሪዎቹም በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በቴክኖሎጂና በአገልግሎት ዘርፍ ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡ ሥራዎቻቸውን በጋራ አቅርበው የመጀመሪያ ደረጃ አሸናፊ ሆነው የአምስት መቶ ሺሕ ብር የገንዘብ ሽልማት ያገኙት እሱባለው ሰለሞን መገርሳና አህመድ ደሊል ናቸው፡፡

ወጣቶቹ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የኬሚካል ኢንጂነሪንግ ተማሪ እንደነበሩ የሚናገረው ወጣት እሱባለው፣ ዳሸን ባንክ ባዘጋጀው ውድድር አሸናፊ የሚያደርጋቸውን ፕሮጀክት የጀመሩት የሦስተኛ ዓመት ተማሪ እያሉ መሆኑን ለሪፖርተር ያስረዳል፡፡

ለውድድሩም ያቀረቡት የፈጠራ ውጤት ከእንሰት በቀላል ሁኔታ ለኬክ፣ ለኩኪስና ለሌሎች ምግቦች የሚውል ዱቄት ማግኘት መቻላቸውን ይናገራል፡፡

በዚህም መሠረት ዱቄቱን የሚያዘጋጁበትን ግብዓት በቀላሉ በመፍጠር ለውድድር ቀርበው ማሸነፋቸውን፣ ለዚህም ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን ‹ጂአይዜድ› የተባለ ተቋም  ድጋፍ እንዳደረገላቸው ይገልጻሉ፡፡

በመጀመሪያ ወደ ውድድሩ ከመግባታቸው በፊት ፕሮጀክቱን የጀመሩት እ.ኤ..አ. 2021 ላይ ሲሆን፣ የሦስተኛ ዓመት ተማሪ እያሉ ኢንቫይሮመንታል ኢምፓክት የተባለ የትምህርት ዓይነት እየወሰዱ ባሉበት ወቅት መሆኑን ያስረዳል፡፡

በወቅቱ ‹ችግር ፈቺ ሐሳብ አምጡ› ሲባሉ እዚህ ሥራ ውስጥ መግባታቸውንና በፍጥነትም የእናቶችን ችግር ይፈታል የተባለ ማሽነሪ ፕላን (ዲዛይን) ማድረግ መቻላቸውን ይናገራል፡፡

ከእንሰት የሚገኘውን ስታርች የተባለውን ዱቄት ለማዘጋጀት ጥናት ማድረጋቸውን፣ ከብዙ ትግል በኋላም ዱቄቱን በማምረት 20 ፓኬጅ ዱቄት ወደ ጀርመን መላካቸውን ያስታውሳል፡፡

በአሁኑ ወቅት እንደ አንድ ተቋም ለመሆን ፈቃድ አውጥተው ዝግጅት ማጠናቀቃቸውንና ምርቱንም ሐዋሳ ለሚገኙ ሱፐር ማርኬቶች እያከፋፈሉ መሆኑን ለሪፖርተር ያብራራል፡፡

የሁለተኛ ዙር የዳሸን ከፍታ የሥራ ፈጠራ ውድድር ተካፋይ የሆኑበት ምክንያት የድርጅታቸውን የሒሳብ ደብተር ለማውጣት ወደ ባንኩ በሄዱበት ወቅት እንደሆነ ይናገራል፡፡

አብዛኛው ማኅበረሰብም ሆነ አርሶ አደሩ የእንሰት ጥቅምን ብዙም እንደማይረዱ ገልጾ፣ ከተመራማሪዎችና ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመሆን በአጭር ጊዜ የሚደርሱ እንሰቶችን ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ ዕቅድ እንዳላቸው ያስረዳል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ አብዛኛውን አርሶ አደሮች የእንሰትን ጥቅም በደንብ እንደማያውቁ ጠቅሶ፣ በቀጣይም በአፍሪካ አገሮች ውስጥ ድርጅት አቋቁመው ለመሥራት ማሰባቸውን ይገልጻሉ፡፡

ደቡብ አፍሪካና ናይጄሪያ ውስጥ እንሰት በስፋት እንደሚገኝ ጠቅሰው፣ በኢትዮጵያም የሚገኙ አብዛኛው ማኅበረሰብ ከእንጀራ በተጨማሪ ሌሎች ምግቦችን እንዲላመዱ ፕሮጀክቱ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ብሏል፡፡

የሥራ ፈጠራ ውድድር ለአንድ አገር ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማኅበራዊ ዕድገት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ስለሆነ፣ ከግል ዘርፍ በተጨማሪ መንግሥት ለእንዲህ ዓይነት ፕሮጀክት ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ይላል፡፡

በሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የዳሸን ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ እንደገለጹት፣ ወጣቶች ከሥራ አጥነት ወጥተው የራሳቸውን ሥራ መፍጠር እንዲችሉ እንዲህ ዓይነት መድረክ ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡

የዳሸን ከፍታ የሥራ ፈጠራ ውድድር የዛሬ ሦስት ዓመት የተጀመረ መሆኑን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ተወዳዳሪዎቹ ባቀረቧቸው የፈጠራ ሐሳቦች መሠረት በመለየት የውድድር አሸናፊዎቹ ሊለዩ መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡

ውድድሩን በዳኝነት እንዲመሩ ብቃት ያላቸው ዳኞችን ከተለያዩ ተቋማት በመመልመልና በየውድድር ማዕከላቱ በመመደብ በተቀመጡ መሥፈርቶች ዙሪያ በቂ ገለጻ አግኝተው እንዲዳኙ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

በተለያዩ መገናገኛ ብዙኃን ለውድድር ተሳትፎ ጥሪ መደረጉን ተከትሎ፣ ከ6,000 በላይ ተወዳዳሪዎች በባንኩ ቅርጫፎችና ዋና መሥሪያ ቤት የውድድር ንድፈ ሐሳባቸውን በማቅረብ የተመዘገቡ ሲሆን፣ ከውድድሩ በፊትም በስድስት ከተሞች ማለትም በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ፣ በሐዋሳ፣ በባህር ዳርና በደሴ ከተሞች ሥልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል፡፡

ሠልጣኞችን ይበልጥ ለፈጠራ ለማነሳሳትና ልምድና ክህሎት እንዲቀስሙ ለማድረግ በየአቅራቢያቸውው የተመረጡ ኢንዱስትሪዎች እንዲጎበኙ፣ እንዲሁም ታዋቂ ባለሀብቶች የሥራ ልምዳቸውን እንዲያካፍሏቸው ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን አስረድተዋል፡፡

የሁለተኛ ዙር የዳሸን ከፍታ የሥራ ፈጠራ ውድድር ለአሥር አሸናፊዎች ከ500 ሺሕ ብር ጀምሮ የማበረታቻ ሽልማት መስጠቱን ባጠቃላይም 2.05 ሚሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን ገለጸዋል፡፡ በቀጣይም ለተወዳዳሪዎቹ ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ጠቁመዋል፡፡

በውድድሩ አሸናፊ ከሆኑ ተወዳዳሪዎች በተጨማሪ፣ ባንኩ ከመጀመሪያው ጀምሮ በዳኝነት ሲያገለግሉ ለነበሩ ዳኞች የምስክር  ወረቀት ተሰጥቷል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...