Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየድሮን ቴክኖሎጂ የአንበሳውን ድርሻ የያዘበት ‹‹ፈጠራ ለአቪዬሽን ልህቀት››

የድሮን ቴክኖሎጂ የአንበሳውን ድርሻ የያዘበት ‹‹ፈጠራ ለአቪዬሽን ልህቀት››

ቀን:

በዓመት በኢትዮጵያ የአየር ክልል ውስጥ ከ200 ሺሕ በላይ አውሮፕላኖች ይተላለፋሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ወደ 60 ሺሕ የሚጠጉት በኢትዮጵያ አየር ማረፊያ ሳያርፉ አቋርጠው የሚሄዱ ናቸው።

በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ዓለም አቀፋዊና አኅጉራዊ ስብሰባዎች ሲኖሩ፣ በዚያው ልክ ከየአቅጣጫው ያሉ በረራዎችም ይበዛሉ፡፡ አውሮኘላኖች እርስ በርሳቸው እንዳይጋጩና አደጋ እንዳይፈጠር የሚከታተለው ደግሞ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ነው፡፡

የድሮን ቴክኖሎጂ የአንበሳውን ድርሻ የያዘበት ‹‹ፈጠራ ለአቪዬሽን ልህቀት›› | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

- Advertisement -

የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ከፍተኛ ቴክኖሎጂና ካቲታል የሚጠይቅ፣ በዓለም አቀፍ  ሕጎችና መመሪያዎች የሚመራ፣ ጠንካራ ውድድር የሚታይበት እንዲሁም ተለዋዋጭና ውስብስብ የቴክኖሎጂ ዘርፍ በመሆኑ፣ ከፍተኛ ጥንቃቄና አስተውሎት በተሞላበት  መምራትና ማስፋፋት አስፈላጊ ነው።

በተለይ ደግሞ አሁን ቴክኖሎጂ በተራቀቀበት ዘመን ዘርፉን በተለመደው መንገድ ብቻ በመምራት ዘለቄታዊ ለውጥ ማምጣትና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቀጠል የማይቻል ብቻ ሳይሆን የማይታሰብም እየሆነ መጥቷል።

ከዚህ አኳያ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን፣ ኢትዮጵያን ዋነኛ የአፍሪካ ማዕከል በማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ አቪዬሽን ለመገንባት፣ መሠረት ናቸው ብሎ ካስቀመጣቸው ዓበይት ጉዳዮች ውስጥ አሁን ያለውንና መጪውን የአቪዬሽን ቴክኖሎጂ የመጠቀም አቅምን መገንባት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር ማድረግና በቀጣይም የራስ የአቪዬሽን ቴክኖሎጂ ባለቤት መሆን የሚሉ ዋና ዋና ነጥቦች እንደሚገኙበት አቶ ጌታቸው መንግሥቴ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ተናግረዋል።

እነዚህን ንድፈ ሐሳቦች ዕውን ይሆኑ ዘንድ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ብሔራዊ አቪዬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኙ አቶ ጌታቸው አክለዋል።

ለአቪዬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ማሳያ ከሆኑት ‹‹ፈጠራ ለአቪዬሽን ልህቀት›› በሚል መሪ ቃል ታኅሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም. በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተው የአቪዬሽን ኢኖቬሽን ኤክስፖ ይገኝበታል።

ኤክስፖው እስከ ዓርብ ታኅሣሥ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚቆይ ሲሆን፣ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ ሥራ ፈጣሪዎች በአንድ ተሰባስበው የሠሩትን፣ የለፉበትን፣ የደከሙበትንና ከኪሳቸው አውጥተው ገንዘብ ያፈሰሱበትን የፈጠራ ውጤት ለዕይታ ክፍት አድርገዋል፡፡

የኤክስፖው ዓላማው ያለበቂ የመንግሥት ድጋፍ በራሳቸው ተነሳሽነት በአቪዬሽን መስክ በፈጠራ ሥራ የተሰማሩ፣ የወደፊቱን የኢትዮጵያ የአቪዬሽን መልከዓ ምድር በመቀየር ረገድ የበኩላቸውን አዎንታዊ አስተዋፅኦ ለማድረግ አቅም ያላቸውን ወጣቶች በማበረታታትና በመደገፍ በዘርፉ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን እንዲስፋፋ ለማድረግ መሆኑንም አቶ ጌታቸው ተናግረዋል።

በኤክስፖው 95 ወጣቶች በጋራና በተናጠል 90 የፈጠራ ውጤቶቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ 34 የግልና የመንግሥት ተቋማትም በአቪዬሽን ዘርፍ ሥራዎቻቸውንና የፈጠራ ውጤታቸውን አሳይተዋል፡፡

ለዕይታ ከቀረቡት የፈጠራ ሥራዎች ውስጥ 90 በመቶ የሚሆኑት ድሮኖች ናቸው።

ከኤግዚቢሽኑ በተጨማሪ የፈጠራ ባለሙያዎች ውድድር እንዳለ የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ፣ በፕሮግራሙ ማጠቃለያ በሚደረግ ውድድር የተሻለ የፈጠራ ውጤቶችን ለሚያቀርቡ ከአሥራ አምስት የማያንሱ አሸናፊዎች ዘላቂ ድጋፍ የሚያገኙበት ሁኔታ መመቻቸቱን አብራርተዋል።

የአገራችን የአቪዬሽን ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ያለበትን ደረጃ በመቃኘት፣ በቀጣይ መከተል ስላለበት አቅጣጫ ውይይት የሚደረግበትና ግብዓት የሚገኝበት የአንድ ቀን ሲንፖዚየም እንደሚኖርም ተመላክቷል።

የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ውስጥ ካስቆጠረው ዕድሜ አንፃር እምብዛም ዕድገት ያልታየበትና በውጭ አገሮች የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ ጥገኛ ሆኖ ያለፉትን 80 ዓመታት ማስቆጠሩን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትሩ አቶ ዓለሙ ስሜ ተናግረዋል።

አቶ ዓለሙ እንዳሉት፣ በኢትዮጵያ የፈጠራ ክህሎት ያላቸው ወጣቶች በተለይ ከ2010 በፊት ትኩረት አግኝተው አያውቁም።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለፈጠራ ሥራዎች ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑ በርካታ ወጣቶች የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ወደ አደባባይ ይዘው ለመውጣት አስችሏቸዋል፡፡

በራሳቸው ጥረት ከኪሳቸው ገንዘብ አውጥተው ልዩ ልዩ የፈጠራ ሥራዎችን የሠሩ የፈጠራ ባለሙያዎች፣ ከመንግሥትም ሆነ ከሌሎች አካላት ድጋፍ ያገኙ ዘንድ ኤክስፖው የራሱ አስተዋፅኦ እንዳለው የተናገሩት በሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን  የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መንግሥቱ ንጉሤ ናቸው።

እንደ እሳቸው፣ የፈጠራ ባለሙያዎች ወደፊት ከመንግሥት ድጋፍ ካላገኙ  የጀመሩት ሥራ ዘላቂና ወጤታማ የመሆን ዕድሉ ጠባብ ነው።

ብዙ ባለሙያዎች ትኩረት አድርገው እየሠሩበት ያለው ድሮንና የበረራ ሥርዓቱ በደንብ ካልተመራ ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ሊያመዝን ይችላል የሚሉት አቶ መንግሥቱ፣ ድሮኖቹ የሚመሩበት የምዝገባና አጠቃላይ እንቅስቃሴ መመሪያና ሕግ አስፈላጊ በመሆኑ ቀደም ሲል መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...