Thursday, February 29, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምበአፍሪካ ውስጥ የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ቦታዎች በጣም ጥቂት የሆኑት ለምንድን ነው?

በአፍሪካ ውስጥ የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ቦታዎች በጣም ጥቂት የሆኑት ለምንድን ነው?

ቀን:

በአፍሪካ የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ቦታዎች ሃቻምና ከዘጠኝ በመቶ በታች ይገኙ የነበረ ሲሆን፣ ዘንድሮ ግን ባለፈው መስከረም የኢትዮጵያ ሁለት ቅርሶችን ጨምሮ ከአፍሪካ ሰባት ቅርሶች በመመዝገባቸው ወደ 10 በመቶ አድጓል ተብሏል፡፡

ይሁን እንጂ አፍሪካ እንደ ብዝኃ ባህልና ብዝኃ ቅርስ ባለቤትነቷ አንፃር ተገቢ ቦታ አልተሰጣትም የሚሉ ባለሙያዎች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ የቅርስ አመራረጡ በጣም አውሮፓ ተኮር (ዩሮ ሴንትሪክ) ነው ይላሉ ባለሙያዎች። ነገር ግን በአፍሪካ የባህል እና የተፈጥሮ ቅርሶችን ለመጠበቅ የመዋቅርና ፖለቲካዊ ቁርጠኝነትም ሆነ ፍላጎት ይጎድላል።

በአፍሪካ ውስጥ የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ቦታዎች በጣም ጥቂት የሆኑት ለምንድን ነው? | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
የዩኔስኮ ኮንቬንሽን አውሮፓ ተኮር በመሆኑ በዓለም ከተመዘገቡት ቅርሶች ከአፍሪካ የተገኙት ከ10 በመቶ የዘለሉ አይደሉም

በባለሙያዎች አገላለጽ፣ በአኅጉር ደረጃ የቅርስ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ሲታይ የዩኔስኮ አሠራር የጂኦግራፊያዊ ሚዛን መዛባት ይታይበታል፡፡ ከ1199ኙ የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ቦታዎች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በአውሮፓ የሚገኙ ሲሆን በአፍሪካ 103 ብቻ ናቸው። ባለፈው መስከረም ዩኔስኮ ባወጣው መረጃ መሠረት፣ አኅጉሮችና በዩኔስኮ ያስመዘገቧቸው ቅርሶች ብዛት የአፍሪካ 103፣ የዓረብ አገሮች 93፣ እስያ-ፓስፊክ 288፣ አውሮፓ/ሰሜን-አሜሪካ 566 ንብረቶች፣ ላቲን አሜሪካ/ካሪቢያን 149 ነው፡፡ ከአጠቃላይ የዓለም ቅርሶች 1199ኙ ባህላዊዎቹ 993፣ ተፈጥሯዊዎቹ 227፣ ድብልቅ 39 ናቸው።አርኪዮሎጂስቱ ኬንያዊው ጆርጅ አቡንጉ ለዚህ ቀላል ማብራሪያ አለው፡- ‹‹ሒደቱ በጣም አውሮፓ ተኮር ነው።››የዩኔስኮ ኮንቬንሽንም እንዲሁ አውሮፓ ተኮር ነውበኬንያ የብሔራዊ ሙዚየም ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉት ጆርጅ አቡንጉ እ.ኤ.አ. በ1972 የዩኔስኮን  የቅርሶች ኮንቬንሽን ያወጡት በአብዛኛው ነጮች ናቸው፡፡ አቡንጉ ከዲደብሊው ጋር ከዓመት በፊት ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፣ ‹‹ኮንቬንሽኑ በተፈጥሮው አውሮፓ ተኮር ነው፡፡ የአፍሪካ አገሮች ወደ ቅርስ ዝርዝሩ ውስጥ ለመግባት ቅርሶቻቸው ለሰው ልጆች የሚኖራቸው ወይም ያላቸው ልዩ ጠቀሜታ በምዕራቡ ዓለም እይታ ማረጋገጥ አለባቸው።››በሃሌ የሚገኘው የማክስ ፕላንክ የማኅበራዊ አንትሮፖሎጂ ተቋም ባልደረባ ክሪስቶፍ ብሩማንም ተመሳሳይ አመለካከት አላቸው፡፡ ከዲደብሊው ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ‹‹በመጀመሪያ የዓለም ቅርስ በአውሮፓ ልዩና ሐውልታዊ ቅርሶች ዙሪያ በዘዴ የተፀነሰ ነበር። ትኩረቱም በካቴድራሎች፣ ቤተ መንግሥቶች፣ ቤተመቅደሶች፣ ታሪካዊ ጥንታዊ ከተሞች ላይ ነበር።›› በማለት ተናግረዋል።የይመዝገብልኝ ማመልከቻ መሥፈርትና ተግዳሮቱ      የይመዝገብልኝ ማመልከቻ መሥፈርቶች ውስብስብ መሆኑ አፍሪካን ፈትኗታል፡፡  የልምድና የገንዘብ እጥረትም አለባት፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ትችት መቅረብ የጀመረው ከሦስት አሠርታት በፊት ጀምሮ መሆኑ ብሩማን ይገልጻሉ፡፡ የአሁኑ ዘመን የሰውና የአካባቢ መስተጋብር በተለይ ትኩረት የሚስብበት ደረጃ ላይ በመድረሱ፣ ማሻሻያዎች በመደረጋቸው  የጋራ ቅርስና ባህላዊ መልክዓ ምድሮች ወደ ይፋዊው የዩኔስኮ ዝርዝር ውስጥ ሊገቡ መቻላቸው ከአፍሪካ የሚታጩትን ሊረዳ ይችላል፡፡ ችግሩ ግን አቡንጉም ሆኑ ብሩማን እንዳሉት ‹‹ከአፍሪካ አገሮች የዩኔስኮ ደጃፍ የሚረግጡት ማመልከቻዎች በጣም ጥቂት የሚሆኑት በተወሳሰቡ የመተግበሪያ መስፈርቶች ምክንያት ነው፡፡ በአያሌ መቶዎች የሚቆጠሩ ገጾች ያሏቸው ሰነዶች ለማመልከቻ ማጠናቀር አለባቸው፡፡›› ብሩማን አያይዘውም አሠራሩ ‹‹የተሻለ ዕውቀት ላላቸው፣ በቅርሶችና በተፈጥሮ ጥበቃ ላይ የበለጠ ልምድ ላላቸውና ከበርካታ የአፍሪካ አገሮች የበለጠ ገንዘብ ያላቸው አገሮች ለማከናወን በጣም ቀላል ነው፤›› ብለዋል።ዩኔስኮ ለአፍሪካ ብዙ ለመሥራት አስቧልየአፍሪካ አቅም ዝቅተኛ ቢሆንም ዩኔስኮ የአፍሪካ አገሮችን ከአፍሪካ የዓለም ቅርስ ፈንድ በተገኘ ስጦታ ይደግፋል ያሉት የባህላዊ ቅርስ ባለሙያዋ ሜችቲልድ ሮስለርም ናቸው። እ.ኤ.አ. ከ2015 ጀምሮ በፓሪስ የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ማዕከል ዳይሬክተር ሆነው ቆይተዋል።ቅርስን ለማስመዝገብ በቅድመ ዝግጅቱ ላይ ዩኒቨርሲቲዎች የበለጠ ጠቃሚ ሚና መጫወት አለባቸው በሚሉት ሮስለር ገለጻ፣ በተለይም በባህላዊ ቅርሶች ጥበቃ ላይ የበለጠ ተሳትፎ ማድረግ አለባቸው፡፡ ባለሙያዎቻቸው ለዩኔስኮ ለሚቀርበው ማመልከቻ የሚደግፉ ጥናቶችን እና ሰነዶችን ለማሰባሰብ ይረዳሉ። ይህም ሆኖ መንግሥታትም ድጋፍ የመስጠት ግዴታ አለባቸው ሲሉም አክለዋል።በአፍሪካ ያሉ መንግሥታት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ስላጋጠሟቸው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ይቀድማል የሚል አስተያየት አላቸው፡፡ ኢኮኖሚውን ማሳደግ፣ ክትባቶችን መግዛትና ሰዎች ቀለባቸውን ለማግኘት የሥራ ዕድል መፍጠር አለባቸው።-  ቅንብር በጋዜጣው ሪፖርተር

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...